ዘፍጥረት 15:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም እግዚአብሔር አብራምን “ይህችን አገር በውርስ ለአንተ እንድሰጥህ ዑር ከምትባለው ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም እግዚአብሔር፣ “ይህችን ምድር ላወርስህ፣ ከከለዳውያን ምድር፣ ከዑር ያወጣሁህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ምድር ያወጣሁህ አምላክህ እግዚአብሔር እኔ ነኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው። |
እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
አብርሃምን እንደ ባረከ አንተንና ዘርህን ይባርክ! ይህንንም ለአብርሃም ሰጥቶት የነበረውንና አንተም ስደተኛ ሆነህ የኖርክበትን ምድር ርስት አድርጎ ይስጥህ!”
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
አገልጋዮችህን አብርሃምን፥ ይስሐቅንና ያዕቆብን አስብ፤ ዘራቸውን እንደ ሰማይ ከዋክብት ልታበዛውና የተስፋይቱንም ምድር ርስት ለዘለዓለም አድርገህ ልትሰጣቸው በመሐላ የገባህላቸውንም ቃል ኪዳን አስብ።”
“በዚህም ጊዜ የሚከተለውን መመሪያ ሰጠኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር አምላካችን ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ ያለውን ይህን ምድር ትወርሱ ዘንድ ሰጥቶአችኋል፤ እንግዲህ የጦር ሰዎቻችሁን አስታጥቃችሁ ሌሎቹ የእስራኤል ነገዶች ምድራቸውን እስኪወርሱ ድረስ እነርሱን ለመርዳት ግንባር ቀደም ሆነው እንዲዘምቱ አድርጉ።
እግዚአብሔር የእነርሱን ምድር እንድትወርስ የፈቀደልህ አንተ ደግ በመሆንህና ትክክለኛውን ነገር በማድረግህ አይደለም፤ እርሱ እነርሱን ነቃቅሎ የሚያባርርበት ምክንያት እነርሱ ክፉዎች ስለ ሆኑና እንዲሁም ለቀድሞ አባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ለመጠበቅ ሲል ነው።