ዘፍጥረት 10:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በሰናዖር ምድር ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእሱም ግዛት መነሻ፥ ሁሉም በሰናዖር አገር የነበሩት፥ ባቢሎን፥ ኤሬክን፥ አካድ፥ እና ካልኔ ናቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር ሀገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካሌድን ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን ኦሬክ አርካድ ካልኔ ናቸው። |
በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።
በዚያን ዘመን የባቢሎን ንጉሥ የባላዳን ልጅ መሮዳክ ባላዳን ንጉሥ ሕዝቅያስ ታሞ መዳኑን ሰማ፤ ስለዚህም ከገጸ በረከት ጋር ደብዳቤ ላከለት።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከነሠራዊቱ ከተማይቱን ለመውጋት በመክበብ ላይ ይገኛል፤ ስለዚህ ምናልባት በረድኤት ከእኛ ጋር ሆኖ ድንቅ ሥራውን በመግለጥ ናቡከደነፆርን እንዲመለስ ያደርግልን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠይቅልን።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በምራታይምና በፈቆድ ሕዝብ ላይ አደጋ ጣሉ፤ ግደሉ፤ አጥፉአቸውም፤ እኔ የማዛችሁን ሁሉ አድርጉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።
እስቲ ወደ ካልኔ ከተማ ሄዳችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም አልፋችሁ “ሐማት” ተብላ ወደምትጠራው ታላቂቱ ከተማና የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋት ውረዱ፤ እናንተ ከእነርሱ ትበልጣላችሁን? ግዛታችሁስ ከእነርሱ ግዛት ይበልጣልን?
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየቃተታችሁ ተንፈራፈሩ፤ ከከተማ ተባራችሁ በሜዳ ላይ ትሰፍራላችሁ ወደ ባቢሎንም ትሄዳላችሁ፤ ይሁን እንጂ በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም እጅ ይታደጋችኋል።
የናምሩድ ግዛት የነበረችውንም በሠራዊታቸው ኀይል አሦርን ድል ነሥተው ይይዛሉ፤ አሦራውያን አገራችንን ቢወሩና ድንበራችንን ቢረግጡ እርሱ ከእጃቸው ያድነናል።