Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 14:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ አምራፌል፥ የኤላሳር ንጉሥ አርዮክ፥ የዔላም ንጉሥ ከዶርላዖሜር፥ የጎይም ንጉሥ ቲድዓል ነበሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አምራፌል የሰናዖር ንጉሥ፣ አርዮክ የእላሳር ንጉሥ፣ ኮሎዶጎምር የኤላም ንጉሥ፣ ቲድዓል የጎይም ንጉሥ በነበሩበት ዘመን፣

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቲድዓል ዘመን እንዲህ ሆነ

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቲድዓል ዘመን

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 14:1
15 Referencias Cruzadas  

በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር።


ሰዎች ከምሥራቅ ተነሥተው በተጓዙ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው።


የቀድሞ አባቶቼ የጎዛንን፥ የካራንና የሬጼፍን ከተሞች አጥፍተዋል፤ በተላሳር ይኖሩ የነበሩትን የዔደንን ሕዝብ ገድለዋል፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ከአማልክታቸው አንዳቸው እንኳ ሊያድኑአቸው ችለዋልን?


በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።


እርሱም “ወደ ሰናዖር ወስደው ቤት ሊሠሩለት ነው፤ ቤቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ቅርጫቱን በዚያ ያኖሩታል” አለኝ።


እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።


“ብዛት ያለው የዔላም ሕዝብ መቃብርም በዚያ ነበር፤ እነርሱም የሕያዋንን ዓለም ያሸብሩ የነበሩ፥ በጦርነት የተገደሉና በእግዚአብሔር ሳያምኑ የወደቁ ናቸው። ኀፍረታቸውንም ተከናንበው ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር አብረው ይወርዳሉ።


የዔላም አገር ወታደሮች በሠረገላና በፈረስ ተቀምጠው ቀስትና ፍላጻ አንግበው መጡ፤ የቂር ወታደሮች ጋሻቸውን አዘጋጅተዋል።


አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።


የተዋጉትም ከዔላም፥ ከጎይም፥ ከባቢሎንና ከኤላሳር ነገሥታት ጋር ነበር፤ አምስቱ ነገሥታት ከአራቱ ነገሥታት ጋር የተዋጉት በዚህ ዐይነት ነበር።


በባሕር ጠረፍ የሚገኘው ዶር፥ በጌልገላ የሚገኘው ጎይምና


በዔላም አውራጃ በግንብ በታጠረው በሱሳ ከተማ ሆኜ ራሴን በራሴ በራእይ አየሁ፤ በኡላይ ወንዝ አጠገብም ቆሜ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios