Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 11:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 በዚያን ጊዜ ጌታ እንደገና የኀይል ሥራ ይሠራል፤ ይኸውም በአሦር፥ በግብጽ፥ በጳጥሮስ አገሮች፥ በኢትዮጵያ፥ በዔላም፥ በባቢሎንና በሐማት እንዲሁም በባሕር ጠረፍ አገሮችና በደሴቶች ሁሉ የሚኖሩትን የቀሩት ወገኖቹን ወደ አገራቸው ይመልሳቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ የቀረውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦርና ከግብፅ፥ ከጳትሮስና ከኢትዮጵያ፥ ከኤላምና ከሰናዖር ከሐማትም፥ ከባሕርም ደሴቶች ይመልስ ዘንድ ጌታ እንደገና እጁን ይገልጣል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 11:11
69 Referencias Cruzadas  

በዚያን ጊዜ ሕዝባችሁ ወደ እናንተ ይመለሳል፤ ይኸውም በስተ ምሥራቅ ከአሦር፥ በስተ ደቡብ ከግብጽ፥ ከኤፍራጥስ ወንዝ አካባቢ፥ እንዲሁም ከሩቅ ባሕሮችንና ተራራዎችን አቋርጠው ይመጣሉ።


እንግዲህ በዚህ ዐይነት እስራኤላውያን ሁሉ ይድናሉ። ስለዚህም እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል፦ “አዳኝ ከጽዮን ይመጣል፤ ከያዕቆብም ዘር ሁሉ ክፋትን ያስወግዳል፤


በዚያን ጊዜ ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ፥ ጥቃት ባደረሱባቸው በአሦራውያን ላይ አይተማመኑም፤ በዚህ ፈንታ በእስራኤል ቅዱስ በእግዚአብሔር ላይ በእውነት ይተማመናሉ።


እንደ ወፍ ከግብጽ፥ እንደ ርግብም ከአሦር እየበረሩ ይመጣሉ፤ ወደ መኖሪያቸው እመልሳቸዋለሁ፤ ይህን የምናገር እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።”


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፤ ከሞት ከተረፉት መካከል ስለ እኔ ወዳልሰሙትና ክብሬንም ወዳላዩት ወደ ተለያዩ ሕዝቦች ወደ ተርሴስ፥ ወደ ሊብያውያን ቀስት ወደሚያስፈነጥሩ ወደ ሊድያውያን፥ ወደ ቱባል፥ ወደ ግሪክ፥ ራቅ ብለው ወደሚገኙት ደሴቶችም እልካቸዋለሁ፤ እነርሱም በሕዝቦች መካከል ክብሬን ይገልጣሉ።


በምድር ላይ ፍትሕን እስኪመሠርት ድረስ እርሱ አይታክትም፤ ተስፋም አይቈርጥም፤ በሩቅ ያሉ ሕዝቦችም የእርሱን ትምህርት ለመስማት ይናፍቃሉ።”


ስለዚህ በምሥራቅ ያሉት ለእግዚአብሔር ክብር ይሰጣሉ፤ በደሴቶች ያሉ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።


የካልኖን፥ የካርከሚሽን፥ የሐማትንና የአርፋድን ከተሞች ድል አድርጌአለሁ፤ ሰማርያንና ደማስቆንም በቊጥጥሬ ሥር አድርጌአለሁ።


ሰዎች ከምሥራቅ ተነሥተው በተጓዙ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።


የሴም ልጆች፦ ዔላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድና አራም ናቸው።


በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር።


ነገር ግን ሰው ወደ ጌታ ሲመለስ “መሸፈኛው ይወገዳል።”


እግዚአብሔር እነርሱን በጣላቸው ጊዜ ሌላው የዓለም ሕዝብ ከእግዚአብሔር ጋር ከታረቀ እግዚአብሔር እነርሱን በሚቀበላቸው ጊዜ ምን የሚሆን ይመስላችኋል? ይህማ ከሞት እንደ መነሣት ያኽል ነው!


ይህም የፍርድ ቃል የሐድራክ አዋሳኝ በሆነችው ሐማትና፥ ብዙ ጥበብ ባላቸው በጢሮስና በሲዶና ከተሞችም ይደርስባቸዋል።


እርሱም “ወደ ሰናዖር ወስደው ቤት ሊሠሩለት ነው፤ ቤቱ ተሠርቶ ካለቀ በኋላ ቅርጫቱን በዚያ ያኖሩታል” አለኝ።


በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።


በዚያን ጊዜ የይሁዳና የእስራኤል ሕዝብ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱንም የሚያስተዳድር አንድ መሪ ይመርጣሉ፤ እንደገናም በገዛ ምድራቸው ላይ በዕድገትና በብልጽግና ይኖራሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናል።


ከዚያ በኋላ በባሕር ጠረፍ ባሉት አገሮች ላይ አደጋ ጥሎ ከእነርሱ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ የጦር መሪ ድል ስለሚነሣው የትዕቢቱ ፍጻሜ ይሆናል፤ በእርግጥም በትዕቢት የተናገረው ስድብ ሁሉ በእርሱ ላይ ይፈጸማል።


በዔላም አውራጃ በግንብ በታጠረው በሱሳ ከተማ ሆኜ ራሴን በራሴ በራእይ አየሁ፤ በኡላይ ወንዝ አጠገብም ቆሜ ነበር።


በደቡባዊ ግብጽ ጳጥሮስ የተባለውን ከተማ ባድማ አደርጋለሁ፤ በሰሜን በኩል በምትገኘው በጾዓን ከተማ ላይም እሳት አቀጣጥላለሁ፤ የቴብስንም ከተማ በፍርድ እቀጣለሁ።


መቅዘፊያዎችሽ የተሠሩት ከባሳን በተገኘ የወርካ ዛፍ ነው፤ ወለልሽም የተሠራው ከቆጵሮስ በተገኘ ልዩ በሆነ የጥድ ሳንቃ ነው፤ ዙሪያውም በዝሆን ጥርስ ተለብጦአል።


“የሐማትና የአርፋድ ከተማ ነዋሪዎች የደማስቆን የጥፋት ወሬ ስለ ሰሙ ግራ ተጋቡ፤ ወደ ላይና ወደ ታች እንደሚናወጥ ባሕር የእነርሱም ልብ ተሸበረ።


በሰሜን ግብጽ ውስጥ ሚግዶል፥ ጣፍናስና ሜምፊስ ተብለው በሚጠሩት ከተሞችና በአገሪቱም ደቡባዊ ክፍል ተበታትነው ስለሚኖሩት እስራኤላውያን ሁሉ እግዚአብሔር ተናገረኝ፤


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የግብጽ ሀብትና የኢትዮጵያ ሸቀጥ ለእናንተ ተላልፎ ይሰጣል፤ ቁመታቸው ረጃጅም የሆነ የሳባ ሰዎችም በሰንሰለት ታስረው በመምጣት ይከተሉአችኋል፤ እጅ ነሥተውም፦ ‘እግዚአብሔር የሚገኘው በእናንተ ዘንድ ብቻ ነው፤ በሌላ አይደለም፤ ከእርሱም በቀር ሌላ አምላክ የለም’ ይላሉ።”


እነርሱም እግዚአብሔርን ያክብሩ፤ በጠረፍ አገሮችም ላይ ምስጋናውን ያውጁ።


ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! የዓለም ሕዝቦች ሁሉ የምስጋና መዝሙር አቅርቡ! በባሕሩ ውስጥ ያሉት ሁሉ፥ የጠረፍ አገሮችና በእነርሱም የሚኖሩ ሁሉ ያመስግኑ!


እግዚአብሔር የቀድሞ አባቶቻቸው ከግብጽ በወጡ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም ከጥፋት የተረፉት የእስራኤል ሕዝብ ከአሦር የሚወጡበትን መንገድ ያዘጋጅላቸዋል።


ጌታ እንዲህ ይላል፤ “ጠላቶችህን ከባሳንና ከጥልቅ ባሕር መልሼ አመጣቸዋለሁ።


በዚያን ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ አምራፌል፥ የኤላሳር ንጉሥ አርዮክ፥ የዔላም ንጉሥ ከዶርላዖሜር፥ የጎይም ንጉሥ ቲድዓል ነበሩ፤


ንጉሥ አርጤክስስ በንጉሠ ነገሥት መንግሥት ግዛቱ ክልል ከጠረፍ እስከ ጠረፍ በሚኖሩ ሕዝብ ላይ ግብር ጣለ።


የሠራዊት አምላክ ከጥፋት የሚተርፍ ዘር ባያስቀርልንማ ኖሮ እንደ ሰዶም በሆንን፥ እንደ ገሞራም በመሰልን ነበር።


እግዚአብሔር ለግብጽ ሕዝብ ራሱን ይገልጥላቸዋል፤ በዚያን ጊዜ እነርሱም አምላክነቱን ዐውቀው ይሰግዱለታል፤ መሥዋዕትና መባም ያቀርቡለታል፤ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ፤ ስእለታቸውንም ሁሉ ይፈጽማሉ።


እግዚአብሔር ግብጻውያንን ይቀጣል፤ ነገር ግን መልሶ ይፈውሳቸዋል፤ ወደ እርሱ ይመለሳሉ፤ እርሱም ጸሎታቸውን ሰምቶ ይፈውሳቸዋል።


በይሁዳ ከጥፋት የተረፉት ሁሉ ወደ መሬት ሥር ሰዶ እንደሚያድግና እንደሚያፈራ ተክል ይሆናሉ።


በቀድሞ መኖሪያቸው በደቡብ ግብጽ በጳጥሮስ እንዲኖሩ እፈቅድላቸዋለሁ፤ በዚያም ደካማ መንግሥት ይሆናሉ፤


“ብዛት ያለው የዔላም ሕዝብ መቃብርም በዚያ ነበር፤ እነርሱም የሕያዋንን ዓለም ያሸብሩ የነበሩ፥ በጦርነት የተገደሉና በእግዚአብሔር ሳያምኑ የወደቁ ናቸው። ኀፍረታቸውንም ተከናንበው ወደ ጥልቁ ከሚወርዱት ጋር አብረው ይወርዳሉ።


መዘጋጀትም ያለበት ከብዙ ጊዜ በኋላ በጦርነት ወድማ የነበረችውን የእስራኤልን ምድር እንዲወር ስለማዘው ነው፤ ለብዙ ጊዜ ባድማ ሆና ነበር፤ ሕዝብዋ ይኖሩባቸው ከነበሩት አገሮች ተመልሰዋል፤ አሁን እስራኤላውያን በሀገራቸው ውስጥ በሚገኙ ተራራዎች ላይ በሰላም ይኖራሉ።


እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።


ሁለተኛው ወንዝ ግዮን ይባላል፤ እርሱም ኢትዮጵያ በምትባል አገር ዙሪያ ይፈስሳል።


ከዚህም ሁሉ በላይ ይህ ሕዝብ ለራስህ ወገን እንዲሆን የመረጥከውና በታላቁ ኀይልህና ብርታትህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸው ነው።”


የአሦር ንጉሠ ነገሥት በባቢሎን፥ ኩታ፥ ዓዋ፥ ሐማትና ሰፋርዋይም ተብለው በሚጠሩት ከተሞች ይኖሩ የነበሩትን አሕዛብ አምጥቶ ተሰደው በሄዱት በእስራኤላውያን እግር በመተካት በሰማርያ ከተሞች እንዲሰፍሩ አደረገ፤ እነርሱም እነዚህን ከተሞች ወርሰው በዚያ መኖር ጀመሩ።


አስፈሪ የሆነ ራእይ ተገልጦልኛል፤ ይኸውም አንዱ ሌላውን አሳልፎ ይሰጣል፤ ከዳተኛው ይከዳል፤ ዘራፊውም ይዘርፋል። የዔላም ሠራዊት ሆይ! አደጋ ለመጣል ውጡ! የሜዶን ሠራዊት ሆይ! ከተሞችን ክበቡ! እግዚአብሔር በባቢሎን ምክንያት የደረሰውን ሥቃይ ሁሉ ያስወግዳል።


የዔላም አገር ወታደሮች በሠረገላና በፈረስ ተቀምጠው ቀስትና ፍላጻ አንግበው መጡ፤ የቂር ወታደሮች ጋሻቸውን አዘጋጅተዋል።


ሕዝቦቼ ከሩቅ አገሮች ይመጣሉ፤ ከሰሜንና ከምዕራብ እንዲሁም ከሲኒም።”


“እኔ እግዚአብሔር እነርሱን ለማዳን እንደሚያገሣ አንበሳ ድምፄን ሳሰማ እነርሱ ይከተሉኛል፤ ልጆቼም እየተንቀጠቀጡ ከወደ ምዕራብ ይመጣሉ።


እኔ ሕዝቤን በስደት ከሚኖሩበት ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋቸዋለሁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios