Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 10:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የእሱም ግዛት መነሻ፥ ሁሉም በሰናዖር አገር የነበሩት፥ ባቢሎን፥ ኤሬክን፥ አካድ፥ እና ካልኔ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የግዛቱም የመጀመሪያ ከተሞች፦ ባቢሎን፣ ኦሬክ፣ አርካድና ካልኔ ናቸው፤ እነዚህ በሰናዖር ምድር ነበሩ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በመጀመሪያ የናምሩድ መንግሥት በሰናዖር የነበሩትን የሦስት ከተሞች ግዛት ማለትም ባቢሎን፥ ኤሬክንና አካድን ያጠቃልል ነበር።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የግ​ዛ​ቱም መጀ​መ​ሪያ በሰ​ና​ዖር ሀገር ባቢ​ሎን፥ ኦሬክ፥ አር​ካድ፥ ካሌ​ድን ናቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን ኦሬክ አርካድ ካልኔ ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 10:10
16 Referencias Cruzadas  

በጌታ ፊት ናምሩድ ኃያል አዳኝ ነበረ፥ ስለዚህም፦ “እንደ ናምሩድ በጌታ ፊት ኃያል አዳኝ” ይባላል።


ሰዎች ከምሥራቅ ተነሥተው በተጓዙ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፥ በዚያም ተቀመጡ።


ስለዚህም፥ ጌታ በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደበላልቆ እነርሱንም ጌታ በምድር ሁሉ ላይ በትኖአቸዋልና፥ ስምዋ ባቢሎን ተባለ።


በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፥ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፥ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፥ በአሕዛብ ንጉሥ በቲድዓል ዘመን እንዲህ ሆነ


ካልኖ እንደ ከርከሚሽ፤ ሐማት እንደ አርፋድ፤ ሰማርያስ እንደ ደማስቆ አይደሉምን?


በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


በዚያም ጊዜ የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻ ላከለት።


“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ይወጋናልና ስለ እኛ፥ እባክህ፥ ጌታን ጠይቅ፤ ምናልባትም ጌታ ለእኛ እንደ ተአምራቱ ሁሉ አድርጐ ከእኛ እንዲመለስ ያደርገዋልና።”


ጌታ ስለ ከለዳውያን ምድር ስለ ባቢሎን በነቢዩ በኤርምያስ የተናገረው ቃል ይህ ነው።


በምራታይም ምድር ላይ በፋቁድም በሚኖሩት ላይ ውጣ፤ ግደላቸው ፈጽመህም አጥፋቸው፥ ይላል ጌታ፥ እንዳዘዝሁህም ሁሉ አድርግ።


ሐራን፥ ካኔ፥ ዔድን፥ የሳባ ነጋዴዎች፥ አሦርና ኪልማድ ነጋዴዎችሽ ነበሩ።


ወደ ካልኔ እለፉና ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ታላቂቱ ሐማት ሂዱ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይሻላሉን? ወይስ ድንበራቸው ከድንበራችሁ ይሰፋልን?


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እንደምትወልድ ሴት አምጪ፥ ተጨነቂ፤ አሁን ከከተማ ወጥተሽ በሜዳ ትቀመጫለሽና፥ ወደ ባቢሎንም ትሄጃለሽ፤ በዚያ ትድኛለሽ፥ በዚያም ጌታ ከጠላቶችሽ እጅ ይቤዥሻል።


የያዕቆብ ትሩፍ በብዙ ሕዝቦች መካከል ከጌታ ዘንድ እንደሚመጣ ጠል፥ በሣር ላይ እንደሚወርድ ካፊያ፥ ሰውን እንደማይጠብቅ፥ የሰውን ልጆች በመጠበቅ እንደማይዘገይ ይሆናል።


እርሱም፦ “በሰናዖር ምድር ቤት ሊሠሩለት ይወስዱታል፤ መቅደሱም በተዘጋጀ ጊዜ፥ እዚያ በስፍራው ይኖራል” አለኝ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos