ዘፀአት 9:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከንጉሡ ባለሟሎች አንዳንዶቹ እግዚአብሔር ስለ ተናገረው ነገር በፍርሃት ተጨነቁ፤ ስለዚህም አገልጋዮቻቸውና እንስሶቻቸው ወደ ቤት ተሰብስበው እንዲጠለሉ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግዚአብሔርን ቃል የፈሩት የፈርዖን ሹማምት፣ ባሮቻቸውንና ከብቶቻቸውን ለማስገባት ተጣደፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፈርዖን አገልጋዮች የጌታን ቃል የፈራ አገልጋዮቹንና ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ አሸሸ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈርዖን ሹሞች የእግዚአብሔርን ቃል የፈራ ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ ሰበሰበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈርዖንም ባሪያዎች የእግዚአብሔርን ቃል የፈራ ባሪያዎቹንና ከብቶቹን ወደ ቤቶቹ አሸሸ፤ |
እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት በማግስቱ ይህንኑ አደረገ፤ የግብጻውያን እንስሶች ሁሉ አለቁ፤ ነገር ግን ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አልሞተም።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።