ዘፀአት 9:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 አሁንም በመስክ የተሰማሩት እንስሶችህና በዚያ ያለው ንብረትህ ሁሉ ወደ መጠለያ እንዲጠጋ ትእዛዝ ስጥ፤ ወደ ቤት ያልገቡ ሰዎችም ሆኑ እንስሶች ቢኖሩ ግን በበረዶው ስለሚመቱ ሁሉም ያልቃሉ።’ ” Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 ከብቶችህና በመስክ ላይ ያለህ ማንኛውም ነገር ወደ መጠለያ ይገቡ ዘንድ አሁን ትእዛዝ ስጥ፤ ምክንያቱም በረዶው ወደ መጠለያ ባልገቡትና በመስክ ላይ በቀሩት በማንኛውም ሰውና እንስሳት ላይ ወርዶባቸው ስለሚሞቱ ነው።’ ” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 ስለዚህም ልከህ ከብቶችህንና በሜዳ ያለ የአንተ የሆነውን ሁሉ አምጣ፤ በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ ላይ በረዶ ይወርዳል እነርሱም ይሞታሉ።’” Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 አሁን እንግዲህ ፥ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ ፈጥነህ ሰብስብ። በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንስሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና።” Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 በሜዳ የተገኘ ወደ ቤት ያልገባ ሰውና እንሰሳ ሁሉ በረዶ ወርዶበት ይሞታልና አሁን እንግዲህ ላክ፤ ከብቶችህንም በሜዳም ያለህን ሁሉ አስቸኵል።’” Ver Capítulo |