Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 9:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት በማግስቱ ይህንኑ አደረገ፤ የግብጻውያን እንስሶች ሁሉ አለቁ፤ ነገር ግን ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አልሞተም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በማግስቱም እግዚአብሔር ነገሩን ፈጸመው፤ የግብጻውያን እንስሳት በሙሉ ዐለቁ፤ ነገር ግን የእስራኤላውያን ከሆኑት እንስሳት አንድም አልሞተም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታም ያንን ነገር በማግስቱ አደረገ፥ የግብጽም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አልሞተም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 የግ​ብ​ፅም ከብት ሁሉ ሞተ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አል​ሞ​ተም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔርም ያንን ነገር በነጋው አደረገ፤ የግብፅም ከብት ሁሉ ሞቱ፤ ከእስራኤል ልጆች ከብት ግን አንድ ስንኳ አልሞተም።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 9:6
10 Referencias Cruzadas  

ከብቶቻቸውን በበረዶ፥ በጎቻቸውንም በመብረቅ ገደለ።


ለቊጣው መንገድን አዘጋጀ፤ ከሞትም አላዳናቸውም፤ ነገር ግን ለመቅሠፍት አሳልፎ ሰጣቸው።


“በዚያችም ሌሊት እኔ በግብጽ ምድር ሁሉ እየተላለፍኩ እያንዳንዱን የሰውም ሆነ የእንስሳ ዘር የሆነውን የበኲር ልጅ ሁሉ እገድላለሁ፤ የግብጽንም አማልክት ሁሉ እቀጣለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


እኩለ ሌሊት ሲሆን እግዚአብሔር ከንጉሡ አልጋ ወራሽ ጀምሮ ከምድር በታች ባለ እስር ቤት ውስጥ እስከ ተጣለው የእስረኛ ልጅ ድረስ በግብጽ ምድር በኲር የሆነውን ወንድ ልጅ ሁሉ በሞት ቀጣ፤ በኲር ሆነው የተወለዱ እንስሶችም ተገደሉ።


ነገር ግን በዚህ ምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር መገኘቴን ታውቅ ዘንድ በዚያን ቀን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሴምን ምድር ከዝንቦቹ መንጋ ነጻ አድርጌ እለያታለሁ።


በረዶው በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ሕዝቡንና እንስሶቹን ጭምር ጨፈጨፈ፤ በሜዳ ላይ ያለውን አትክልት ሁሉ መታ፤ ዛፎችንም ሁሉ ሰባበረ።


እስራኤላውያን በሚኖሩባት በጌሴም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም።


እግዚአብሔር ግን በእስራኤላውያንና በግብጻውያን እንስሶች መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አይሞትም።


እግዚአብሔር ይህን ነገር ነገ አደርጋለሁ ብሎ ጊዜውን ወሰነ።’ ”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos