ዘፀአት 23:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ለማድረግ የተሰባሰቡ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድን ለማጣመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ክፉ በማድረግ ብዙዎችን አትከተል፤ በሕግ ፊት ምስክርነት ስትሰጥ፣ ከብዙዎቹ ጋራ ተባብረህ ፍትሕ አታጣምም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ክፉ ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዐመፅ ከብዙ ሰው ጋር አንድ አትሁን፤ ፍርድንም ለማጣመም ከብዙ ሰው ጋር አትጨመር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ክፉውን ለማድረግ ብዙ ሰዎችን አትከተል፤ ፍርድንም ለማጥመም ከብዙ ሰዎች ጋር ተስማምተህ አትመስክር። |
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
እነርሱም በብርቱ ተቈጥተው ካስደበደቡኝ በኋላ የእስር ቤት እንዲሆን አድርገውት ወደነበረው ወደ ጸሐፊው ወደ ዮናታን ቤት ውስጥ አስገብተው ዘጉብኝ፤
ስለዚህም ንጉሥ ሴዴቅያስ በቤተ መንግሥቱ ግቢ በሚገኘው በዘብ ጠባቂዎች ክፍል ውስጥ እንዲዘጋብኝ አዘዘ፤ እኔም በዚያ ቈየሁ፤ ዳቦ ከከተማይቱ ጨርሶ እስከ ጠፋም ድረስ ከዳቦ መጋገሪያዎች አንድ ዳቦ በየቀኑ ይሰጠኝ ነበር።
“ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”
እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ እጅግ የከፋ ኃጢአት በመሥራት በድለዋል፤ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ግድያ ፈጽመዋል፤ ከተማይቱንም በዐመፅ የተሞላች አድርገዋታል፤ ‘እግዚአብሔር አገራችንን ትቶአታል፤ እኛንም አይመለከተንም’ ይላሉ፤
“የፍርድ ውሳኔ በምትሰጡበት ጊዜ ታማኞችና ትክክለኞች ሁኑ፤ ለሁሉም በትክክል ፍረዱ እንጂ ለድኻው ስለ ድኽነቱ አድልዎ አታድርጉለት፤ ባለጸጋውንም ስለ ሀብቱ ብዛት አትፍሩት።
ፊስጦስ ግን አይሁድን ደስ ለማሰኘት ፈልጎ ጳውሎስን “ወደ ኢየሩሳሌም ሄደህ ስለዚህ ጉዳይ እዚያ በእኔ ፊት ልትፋረድ ትፈልጋለህን?” አለው።
“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሁሉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን የእግዚአብሔርን ሕግ እያወቁ ይህን ሁሉ ያደርጋሉ፤ ማድረግ ብቻም ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ሰዎች ያበረታታሉ።
በምትሰጡትም ውሳኔ አድልዎ አታድርጉ፤ ስለ ማንኛውም ታላቅም ሆነ ታናሽ ሰው ያለ አድልዎ በእኩልነት ፍረዱ። ፍርድ የእግዚአብሔር ስለ ሆነ ማንንም አትፍሩ፤ ለእናንተ የሚከብድባችሁ ነገር ቢኖር ወደ እኔ አምጡት፤ እኔም ውሳኔ እሰጥበታለሁ፤’
እርሱን ማምለክ መልካም መስሎ ካልታያችሁ ግን የቀድሞ አባቶቻችሁ ከኤፍራጥስ ወንዝ ማዶ በነበሩበት ጊዜ ያመልኩአቸው የነበሩትን ወይም አሁን በምድራቸው የምትኖሩባቸውን የአሞራውያንን አማልክት ታመልኩ እንደሆን የምታመልኩትን ዛሬውኑ ምረጡ፤ እኔና ቤተሰቤ ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን።”
ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አዎ፤ እኔ ኃጢአት ሠርቼአለሁ፤ የእግዚአብሔርን ትእዛዝና አንተ የሰጠኸኝን መመሪያ አልጠበቅሁም፤ ወታደሮቼን በመፍራት እነርሱ የፈለጉትን ሁሉ አደረግሁ፤
ነገር ግን ሳኦልና ሠራዊቱ የአጋግን ሕይወት አተረፉ፤ እንዲሁም ምርጥ ምርጥ የሆኑትን በጎችና የቀንድ ከብቶች፥ የሰቡ ሰንጋዎችንና ጠቦቶችን ከዚህም ጋር መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ አላጠፉም፤ እነርሱም ያጠፉት የማይረባውንና የማይጠቅመውን ነገር ብቻ ነበር።