በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።
ዘፀአት 20:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አትስገድላቸው ወይም አታምልካቸውም፤ እኔ አምላክህ እግዚአብሔር የሚጠሉኝን ስለ አባቶቻቸው ኀጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆቻቸውን የምቀጣ ቀናተኛ አምላክ ነኝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውም፤ እኔ ጌታ አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና። በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኀጢአት በልጆች ላይ የማመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም፤ በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢያት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ |
በዳዊት ዘመነ መንግሥት ሦስት ዓመት ሙሉ ጽኑ ራብ ነበር፤ ዳዊትም ስለዚህ ጉዳይ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጠየቀ ጊዜ እግዚአብሔር “ሳኦልና ቤተሰቡ ግድያ በመፈጸም በደል ሠርተዋል፤ ሳኦልም የገባዖንን ሰዎች ፈጅቶአል” ሲል መለሰለት።
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
“አክዓብ በእኔ ፊት ራሱን እንዴት እንዳዋረደ ተመልክተሃልን? ይህን ስላደረገ በሕይወቱ ሳለ መቅሠፍትን አላመጣበትም፤ የተባለውን መቅሠፍት በአክዓብ ቤተሰብ ላይ የማመጣው በልጁ የሕይወት ዘመን ይሆናል።”
እግዚአብሔርም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በመግባት እስራኤላውያንን እንዲህ ሲል አዞአቸው ነበር፤ “ባዕዳን አማልክትን አታምልኩ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች በመሆን አትስገዱላቸው፤ መሥዋዕትንም አታቅርቡላቸው፤
እነዚያ ሕዝቦች በዚሁ ዐይነት እግዚአብሔርን ማምለክ ጀመሩ፤ በሌላ በኩል ግን ለጣዖቶቻቸው ይሰግዱ ነበር፤ ዘሮቻቸውም እስከ ዛሬ ድረስ ይህንኑ ዐይነት አምልኮ እንደ ቀጠሉ ናቸው።
ነገር ግን ይህም ሁሉ ሆኖ ንጉሥ ምናሴ ባደረገው ክፉ ነገር ምክንያት በይሁዳ ላይ የነደደው አስፈሪ የእግዚአብሔር ቊጣ እስከ አሁን ድረስ ገና አልበረደም ነበር።
ስለዚህም የሀገሬን ንጉሥ በማጀብ ሪሞን የተባለ የሶርያ አምላክ ወደሚመለክበት መቅደስ ብገባና ብሰግድም እንኳ እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለኝ ተስፋ አደርጋለሁ፤ በእርግጥም ይቅር ይለኛል።”
ከዚህም የተነሣ እነሆ፥ የንዕማን የቆዳ በሽታ ወደ አንተ ይተላለፋል፤ አንተና ዘሮችህ ለዘለዓለም ከዚያ በሽታ አትነጹም!” አለው። ግያዝም ወጥቶ ሲሄድ፥ ያ የቆዳ በሽታ ስለ ተጋባበት ገላው እንደ በረዶ ነጭ ሆነ።
“እናንተ ‘እግዚአብሔር በአባቶች በደል ልጆችን ይቀጣል’ ትላላችሁ፤ እስቲ እግዚአብሔር ኃጢአተኞችን ራሳቸውን ይቅጣቸው፤ ይህ ከሆነ በደለኛነታቸውን ሊገነዘቡት ይችላሉ።
ለእነርሱ አማልክት በመንበርከክ አትስገድ፤ አታምልካቸው፤ ሃይማኖታዊ ልማዶቻቸውንም አትከተል፤ አማልክታቸውን አጥፋ፤ ለእነርሱ ቅዱሳን የሆኑትን የድንጋይ ዐምዶቻቸውንም አፈራርስ፤
ሰው ከአንድ ዛፍ ግማሹን ለማገዶ፥ ግማሹንም ጣዖት ለመሥራት ይጠቀምበታል፤ ግማሹን እሳት አንድዶ ለመሞቅና እንጀራ ለመጋገር ይጠቀምበታል፤ በሌላው ጒማጅ ጣዖት ሠርቶ በፊቱ እየሰገደ ያመልከዋል።
“የዚህን እንጨት ግማሹን አነደድኩት፤ በፍሙም ዳቦ ጋገርኩበት፤ ሥጋም ጠብሼበት በላሁ፤ አሁን እንግዲህ ቀሪውን ቊራጭ እንጨት ለጣዖት ላውለውን? በአንድ ቊራጭ እንጨት ፊት ወድቄ ልስገድን?” ብሎ የሚያስብ ዕውቀት ወይም ማስተዋል ያለው አንድም ሰው የለም።
ለብዙ ሺህ ሕዝብ ዘለዓለማዊ ፍቅርህን አሳይተሃል፤ ይሁን እንጂ አባቶቻቸው በሠሩት ኃጢአት ምክንያት ልጆቻቸውን ትቀጣለህ፤ አንተ ታላቅና ኀያል አምላክ ነህ፤ አንተ ሁሉን ቻይና ስምህም የሠራዊት ጌታ ነው፤
“ ‘ታዲያ ልጁ በአባቱ ኃጢአት ምክንያት ያልተቀጣው ስለምንድን ነው?’ ትሉ ይሆናል፤ ልጁ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር አድርጎአል፤ ሕጌን አክብሮአል፤ ስለዚህ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤
“በእስራኤል ምድር ተደጋግሞ የሚነገር ይህ ምሳሌ ምንድን ነው? ‘ወላጆች ጐምዛዛ የወይን ፍሬ በሉ፤ ነገር ግን የልጆቻቸውን ጥርስ አጠረሰ’ ይላሉ፤
እንዲህም አልኳቸው፦ ‘እያንዳንዳችሁ የምታተኲሩባቸውን አጸያፊ ምስሎች አስወግዱ፤ በግብጽ ጣዖቶችም ራሳችሁን አታርክሱ፤ ይህን የተናገርኩ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ።’
ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁን ግን የያዕቆብ ልጆች ለሆኑት ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እንደገናም አበለጽጋቸዋለሁ፤ ቅዱስ ስሜም እንዳይሰደብ እከላከላለሁ።
እርሱም የሰው እጅ የሚመስል ነገር ወደ እኔ ዘርግቶ የራስ ጠጒሬን ያዘ፤ በዚሁ ራእይ የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ሰማይ አነሣኝና ወደ ኢየሩሳሌም አደረሰኝ። በሰሜን በኩል ወደ ውስጠኛው አደባባይ በሚያስገባው ቅጽር በር አሳልፎ የእግዚአብሔርን ቅናት የሚቀሰቅስን የጣዖት ምስል ወዳለበት ስፍራ አደረሰኝ።
እግዚአብሔር የይሁዳን ንጉሥ ኢዮአቄምንና የቤተ መቅደሱንም ንዋያተ ቅድሳት በከፊል ለናቡከደነፆር አሳልፎ ሰጣቸው፤ ንጉሡም ንዋያተ ቅድሳቱን በባቢሎን ባሉት የጣዖት አማልክቱ ቤተ መቅደስ ውስጥ አኖረ።
እኔ ራሴ በዚያ ሰውና በመላ ቤተሰቡ እንዲሁም ለእኔ ታማኝ ባለመሆን ለሞሌክ በመስገድ ከእርሱ ጋር በሚተባበሩት ሁሉ ላይ መዓቴን አመጣለሁ፤ ከዚያም በኋላ ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋቸዋለሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “ትሰግዱላቸው ዘንድ ማናቸውንም ዐይነት ጣዖቶች አትሥሩ፤ እንዲሁም ምስል ወይም ሐውልት ወይም የተቀረጸ የድንጋይ ዐምድ አታቁሙ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤
‘እግዚአብሔር በቶሎ አይቈጣም፤ ምሕረቱና ፍቅሩ የበዛ ነው፤ ኃጢአትንና ዐመፃን ይቅር ይላል፤ ነገር ግን እስከ ሦስት ከዚያም እስከ አራት ትውልድ ድረስ ልጆችንና የልጅ ልጆችን ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት እቀጣለሁ’ እንዳልከው፥
ልጆቻችሁም በእናንተ አለማመን ምክንያት ከእናንተ የመጨረሻው በድን በምድረ በዳ እስኪወድቅ ድረስ አርባ ዓመት ሙሉ ጽኑ መከራ እየተቀበሉ በዚህ ምድረ በዳ ይንከራተታሉ፤
“የካህኑ የአሮን የልጅ ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባደረገው ነገር ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያለኝ ቊጣ በርዶአል፤ ፊንሐስ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሰግዱትን መታገሥ አልፈለገም፤ በቊጣዬ እስራኤልን ያላጠፋሁትም እርሱ ስለ እኔ ባሳየው ቅናት ነው።
ደቀ መዛሙርቱ ኢየሱስን “መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ የተወለደው በማን ኃጢአት ነው? በራሱ ኃጢአት ነውን ወይስ በወላጆቹ?” ሲሉ ጠየቁት።
የሰውን ስም የሚያጠፉ፥ እግዚአብሔርን የሚጠሉ፥ ሰውን የሚያዋርዱ፥ ትዕቢተኞች፥ ትምክሕተኞች፥ ክፋትን ለማድረግ ዘዴ የሚፈልጉ፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥
እውነተኛ ባልሆኑ አማልክት አስቀንተውኛል፤ ዋጋቢስ በሆኑ ጣዖቶቻቸው አስቈጥተውኛል፤ በተናቀ ሕዝብ አስቀናቸዋለሁ፤ በማያስተውል ሕዝብ አስቈጣቸዋለሁ።
እኔ አምላክህ እግዚአብሔር፥ እኔን ትተው ሌሎች አማልክትን የሚያመልኩትን ሰዎች፥ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች፥ እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ የምበቀል ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ እነዚያን የተቀረጹ ምስሎች አትስገድላቸው፤ አታምልካቸውም።
ባዕዳን አማልክትን ብታመልኩ በመካከላችሁ የሚገኘውን የአምላካችሁን ቊጣ ታስነሣላችሁ፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ ከምድር ገጽ ጠራርጎ ያጠፋችኋል፤
እናንተ ከዳተኞች! ዓለምን የሚወድ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑን አታውቁምን? እንግዲህ ዓለምን የሚወድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት መሆኑ ነው።
ስለዚህ አምላካችሁ እግዚአብሔር የሰጣችሁን ቃል ኪዳን በማፍረስ ወደ ሌሎች አማልክት ሄዳችሁ ብታመልኩአቸውና ብትሰግዱላቸው እግዚአብሔርን ታስቈጣላችሁ፤ ከሰጣችሁም መልካም ምድር በፍጥነት ትጠፋላችሁ።”
በመካከላችሁ ከቀሩት ሕዝቦች ጋር ከቶ አትተባበሩ፤ የአማልክታቸውንም ስም አትጥሩ፤ በእነርሱም አትማሉ፤ ለእነርሱም አገልጋዮች አትሁኑ፤ አትስገዱላቸውም።
ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስና ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፥ እናንተ እርሱን ማገልገል አትችሉም፤ የምትሠሩትን ዐመፅና ኃጢአት ሁሉ ይቅር አይልም፤
ነገር ግን መሪ በሚሞትበት ጊዜ ሁሉ ተመልሰው ሌሎች አማልክትን በመከተል፥ ለእነርሱም በመስገድና እነርሱንም በማምለክ ከአባቶቻቸው የከፋ በደል ይፈጽሙ ነበር፤ መጥፎ ድርጊታቸውንና ልበ ደንዳና መሆናቸውን አልተዉም።