Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ናሆም 1:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር ቀናተኛ ተበቃይ አምላክ ነው፤ በኀይለኛ ቊጣውም፥ በጠላቶቹ ላይ መዓቱን ያወርዳል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር የሚበቀል፣ በመዓትም የተሞላ ነው። እግዚአብሔር ባላጋራዎቹን ይበቀላል፤ በጠላቶቹም ላይ ቍጣውን ያመጣል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ጌታ ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ ጌታ ተበቃይና መዓት የተሞላ ነው፤ ጌታ ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፤ ቁጣን ለጠላቶቹ ያቆያል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፣ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፣ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።

Ver Capítulo Copiar




ናሆም 1:2
42 Referencias Cruzadas  

“ለሕዝብዋ ስላለኝ ፍቅር ኢየሩሳሌምን መርዳት እፈልጋለሁ፤ በጠላቶችዋ ላይ እንድቈጣ ያደረገኝም ይኸው ስለ እርስዋ ያለኝ ፍቅር ነው።


እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።


እግዚአብሔር ሆይ! አንተ በቀልን የምትመልስ አምላክ ነህ፤ ስለዚህ ፍርድህን ግለጥ!


“እኔ እግዚአብሔር ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆንኩ ከእኔ በቀር ለሌሎች አማልክት አትስገዱ፤


ኢያሱም ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ቅዱስና ቀናተኛ አምላክ ስለ ሆነ፥ እናንተ እርሱን ማገልገል አትችሉም፤ የምትሠሩትን ዐመፅና ኃጢአት ሁሉ ይቅር አይልም፤


“በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ተገቢ ዋጋን እከፍላለሁ” ያለው ማን መሆኑን እናውቃለን፤ እንዲሁም “እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ይፈርዳል” ይላል ጌታ።


እግዚአብሔር እንደ ጀግና ወታደር ይወጣል፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጦርነትን ያውጃል፤ በጠላቶቹም ላይ ድልን ይጐናጸፋል።


አምላካችሁ እግዚአብሔር የሚባላ እሳት ነው፤ ቀናተኛ አምላክ ነው።


እንግዲህ ይህ ሁሉ እንዲህ ከሆነ ጌታ እርሱን በማምለክ የሚኖሩትን ሰዎች ከፈተና እንደሚያድናቸው፥ ኃጢአተኞችንም እንዴት እንደሚቀጣና ለፍርድ ቀንም እንዴት ጠብቆ እንደሚያቈያቸው ያውቃል ማለት ነው።


ወዳጆቼ ሆይ! ቊጣን ለእግዚአብሔር ተዉ እንጂ ራሳችሁ አትበቀሉ፤ “የምበቀልና የበቀልንም ብድራት የምከፍል እኔ ነኝ ይላል ጌታ እግዚአብሔር” ተብሎ ተጽፎአል።


ለእኔ አልታዘዝም ያሉትን መንግሥታት ሁሉ በታላቅ ቊጣዬ እበቀላቸዋለሁ።”


እግዚአብሔር ስለምድሪቱ ባለው ቅንአት፥ ለሕዝቡ ራራላቸው፤


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “አሁን ግን የያዕቆብ ልጆች ለሆኑት ለእስራኤል ሕዝብ ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ እንደገናም አበለጽጋቸዋለሁ፤ ቅዱስ ስሜም እንዳይሰደብ እከላከላለሁ።


በሩቅ ያሉት ታመው ይሞታሉ፤ በቅርብ ያሉትም በጦርነት ይገደላሉ፤ ከዚያ የሚተርፉትም በራብ ያልቃሉ፤ በዚህም ዐይነት ኀይል የተሞላበትን ቊጣዬን በእነርሱ ላይ እፈጽማለሁ።


እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”


ልጆችሽ በወጥመድ ውስጥ እንደ ተያዘ ድኩላ በየመንገዱ አደባባይ ተዝለፍልፈው ወድቀዋል፤ በእነርሱም ላይ የአምላክሽ የእግዚአብሔር ተግሣጽና ቊጣ ወርዶባቸዋል።


አንቺ ከእግዚአብሔር እጅ የሚያንገዳግደውን የቊጣውን ጽዋ በትልቅ ዋንጫ ጨልጠሽ የጠጣሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ንቂ፤ ተነሥተሽም ቁሚ!


በልቼ እጠግባለሁ ሲል እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ያወርድበታል። መዓቱንም በእርሱ ላይ ያዘንብበታል።


በእናንተ ላይ በቊጣ እነሣለሁ፤ በእናንተ ላይ የማመጣውንም ቅጣት ካለፈው ሰባት ጊዜ የበለጠ እንዲሆን አደርጋለሁ።


ባለሥልጣን ለአንተ መልካም እንዲያደርግ የተሾመ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነው፤ ባለሥልጣን ሰይፍ የታጠቀው በከንቱ ስላልሆነ ክፉ አድራጊ ከሆንክ ባለሥልጣንን ፍራ፤ እርሱ ክፉ አድራጊዎችን በመቅጣትና የእግዚአብሔርን በቀል በማሳየት እግዚአብሔርን ያገለግላል።


ስለዚህም መልአኩ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሚለውን ቃል እንዲህ ብለህ ዐውጅ አለኝ፥ “እኔ ለተቀደሰችው ከተማዬ ለኢየሩሳሌም ታላቅ ፍቅርና ብርቱ ቅናት አለኝ፤


ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ጎግ እስራኤልን በሚወርበት ጊዜ የእኔ ብርቱ ቊጣ ይነሣሣል፤


“ስለ እስራኤል ምድር ትንቢት ተናገር፥ ለሕዝቡም እንዲህ በላቸው፦ በተራሮቻችሁ፥ በኰረብቶቻችሁ፥ በወራጅ ውሃዎቻችሁና በሸለቆዎቻችሁ ላይ ሕዝቦች ባደረሱት ውርደት ምክንያት እኔ በኀይለኛ የቊጣ ቅናቴ እናገራለሁ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


ስለዚህ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ራርቼም አልተዋቸውም፤ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ወደ እኔ ቢጮኹም አላደምጣቸውም።”


“ቊጣዬ በእርሱ ላይ ይፈጸማል ኀይለኛ ቊጣዬንም በእነርሱ ላይ አውርጄ እረካለሁ ይህንንም ቊጣዬን በእነርሱ ላይ ባወረድኩ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅናቴ የተናገርኩ መሆኔን ያውቃሉ።


እግዚአብሔር ኀይለኛ ቊጣውን ገለጠ፤ የጽዮንን መሠረት የሚያጠፋ፥ የተቀጣጠለ እሳት የመሰለ መዓቱን አወረደ።


እግዚአብሔር አስፈሪ በሆነው ቊጣና መዓቱ ሕዝቡን እንደሚቀጣ የተናገረ በመሆኑ ምናልባት በመጸጸት ከክፉ ሥራቸው ወደ እግዚአብሔር ተመልሰው ይለምኑት ይሆናል።”


የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “ይህን በቊጣዬ ወይን የተሞላ ጽዋ ከእጄ ውሰድ እኔ ወደምልክህ ሕዝቦች ሄደህ ከእርሱ እንዲጠጡ አድርግ።


አንቺ፦ ‘እርሱ ዘወትር ይቈጣልን? ኀይለኛ ቊጣውስ ዘላቂ ነውን?’ ብለሽ ተናግረሻል፤ ነገር ግን የምትችዪውን ክፉ ሥራ ትሠሪያለሽ።”


እግዚአብሔር በኀይለኛ ቊጣው ለመበቀልና በሚንበለበለው እሳት ለመገሠጽ በእሳት ሆኖ ይመጣል፤ መንኲራኲሮችም እንደ ዐውሎ ነፋስ ናቸው።


ነገር ግን የሚጠሉትን በማጥፋት ይበቀላል፤ እነርሱንም ከመበቀል ፈጽሞ አይዘገይም።


በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የተነሡ ነቢያት በብዙ ሕዝብና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር እንደሚመጣ ትንቢት ተናግረዋል፤


በዚያን ቀን በእስራኤል ምድር ታላቅ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደሚሆን በቅናቴና በሚነድ ቊጣዬ ዐውጃለሁ።


ዘለዓለማዊ ፍቅሬንም እስከ ብዙ ሺህ ትውልድ እጠብቃለሁ፤ በደልን መተላለፍንና ኃጢአትን ሁሉ ይቅር እላለሁ፤ ነገር ግን እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ ስለ ወላጆቻቸው ኃጢአት ከመቅጣት አልገታም።”


“የካህኑ የአሮን የልጅ ልጅ የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ ባደረገው ነገር ምክንያት በእስራኤል ሕዝብ ላይ ያለኝ ቊጣ በርዶአል፤ ፊንሐስ ከእኔ በቀር ለሌላ አምላክ የሚሰግዱትን መታገሥ አልፈለገም፤ በቊጣዬ እስራኤልን ያላጠፋሁትም እርሱ ስለ እኔ ባሳየው ቅናት ነው።


በከተማይቱ ዙሪያ በማቅራራት ደንፉ! እነሆ ባቢሎን እጅዋን ሰጥታለች፤ ግንቦችዋ ተጥሰዋል፤ ቅጽሮችዋም ፈራርሰዋል፤ ባቢሎናውያንን እበቀላለሁ፤ እናንተም ተበቀሉአቸው፤ በሌሎች ላይ የፈጸሙትን ጭካኔ በእነርሱም ላይ ፈጽሙባቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios