አብራም ከዶርላዖሜርና ከእነርሱ ጋር አብረው የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፥ የሰዶም ንጉሥ “የንጉሥ ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው በሻዌህ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ፤
ዘፀአት 18:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ሙሴ ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ራሱን ዝቅ አድርጎ እጅ በመንሣት ሳመው፤ ስለ ግል ጤንነታቸው ተጠያይቀው ወደ ሙሴ ድንኳን ገቡ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሙሴ ዐማቱን ሊቀበለው ወጣ፤ ዝቅ ብሎ እጅ በመንሣትም ሳመው፤ ከዚያም ሰላምታ ተለዋውጠው ወደ ድንኳኑ ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፤ እጅ ነሣው፤ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ሰላምታ ተሰጣጡ፤ ወደ ድንኳኑም ገቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ። |
አብራም ከዶርላዖሜርና ከእነርሱ ጋር አብረው የነበሩትን ነገሥታት ድል አድርጎ ሲመለስ፥ የሰዶም ንጉሥ “የንጉሥ ሸለቆ” እየተባለ በሚጠራው በሻዌህ ሸለቆ ሊቀበለው ወጣ፤
ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤
በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥
ላባም የእኅቱ ልጅ ያዕቆብ መምጣቱን በሰማ ጊዜ ሊቀበለው ፈጥኖ ሄደ፤ ዐቅፎ ከሳመውም በኋላ ወደ ቤት አመጣው፤ ያዕቆብ የሆነውን ሁሉ ለላባ ነገረው፤
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤
የእስራኤል ሕዝብ በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ ሙሴ ድንኳኑን ከሰፈሩ ራቅ ባለ ቦታ ይተክለው ነበር፤ እርሱም “ድንኳን” ተብሎ ተጠራ፤ እግዚአብሔርን መጠየቅ የሚፈልግ ሁሉ ወደዚያ ይሄድ ነበር።
በዚያኑ ጊዜ እግዚአብሔር አሮንን “ከሙሴ ጋር ለመገናኘት ወደ በረሓው ሂድ” አለው። እርሱም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ሄደ፤ በዚያም ሙሴን አግኝቶ ሳመው።
በሮም ያሉ ምእመናን ስለ እኛ በሰሙ ጊዜ እስከ አፍዮስ ገበያና “ሦስት ማደሪያዎች” እስከሚባለው ቦታ ድረስ ሊቀበሉን መጡ፤ ጳውሎስ እነርሱን ባየ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገነና ተጽናና።
ዮፍታሔ በምጽጳ ወዳለው ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ሴት ልጁ አታሞ ይዛ እየጨፈረች ልትቀበለው ወጣች፤ ያለ እርስዋም ሌላ ወንድ ወይም ሴት ልጅ አልነበረውም።
እነዚህንም ዐሥር የአይብ ጥፍጥፎች ለሻለቃው የጦር አዛዥ ስጠው፤ ወንድሞችህም እንዴት እንዳሉ በዐይንህ አይተህ የደኅንነታቸውን መረጃ አምጣልኝ።