ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
ኤፌሶን 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም ክርስቶስ በእምነት በልባችሁ እንዲኖርና እናንተም ሥር ሰዳችሁ በፍቅር የጸናችሁ እንድትሆኑ እጸልያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይኸውም በእምነት ክርስቶስ በልባችሁ እንዲያድር ነው። ደግሞም ሥር ሰድዳችሁ፣ በፍቅር ታንጻችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥር ሰዳችሁ፥ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በልባችሁ ውስጥ በፍቅር ሥር መሠረታችሁ የጸና ሲሆን ክርስቶስ በሃይማኖት በሰው ውስጥ ያድራልና። |
ከፍተኛውና ከሁሉ የላቀው፥ ለዘለዓለም የሚኖር ቅዱሱ እንዲህ ይላል፦ “እኔ በተቀደሰና በከፍተኛ ቦታ፥ እንዲሁም ልባቸው ከተሰበረና መንፈሳቸው ትሑት ከሆኑት ጋር እኖራለሁ፤ ይኸውም ትሑት መንፈሳቸውንና የተሰበረ ልባቸውን ለማደስ ነው።
እርሱ በጥልቅ ቆፍሮ ቤቱን በጽኑ አለት ላይ የመሠረተውን ሰው ይመስላል፤ ጐርፍ መጥቶ ያንን ቤት ገፋው፤ ነገር ግን በጽኑ መሠረት ላይ ስለ ተሠራ ሊያነቃንቀው አልቻለም።
ይህም የእውነት መንፈስ ነው፤ ዓለም ስለማያየውና ስለማያውቀው ሊቀበለው አይችልም፤ እናንተ ግን፥ እርሱ ከእናንተ ጋር ስለ ሆነና በውስጣችሁም ስላለ ታውቁታላችሁ።
እኔ የምለምነው እኔ በእነርሱ አንተም በእኔ እንደ ሆንክ እነርሱም በፍጹም አንድ እንዲሆኑ ነው፤ እንዲሁም እኔን እንደ ላክኸኝና እኔን በወደድከኝ መጠን እነርሱንም እንደ ወደድካቸው ዓለም እንዲያውቅ ነው።
በእምነታችሁ የጸናችሁ መሆናችሁን ለማረጋገጥ ራሳችሁን መርምሩ፤ ራሳችሁን ፈትኑ፤ ኢየሱስ ክርስቶስ በውስጣችሁ መሆኑን አልተገነዘባችሁምን? አለበለዚያ በፈተና ወድቃችኋል ማለት ነው፤
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።
እኔ ከክርስቶስ ጋር እንደ ተሰቀልኩ ያኽል ስለምቈጥር ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ይኖራል እንጂ እኔ ለራሴ ሕይወት የምኖር አይደለሁም፤ አሁንም በሥጋዊ አካሌ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በማመን በተገኘው ሕይወት ነው።
ይህም የሚሆነው ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በወንጌሉ ከተገኘው ተስፋ ሳትናወጡ በእምነት ጸንታችሁ ስትኖሩ ብቻ ነው፤ ይህም ወንጌል እናንተ የሰማችሁትና በዓለም ላይ ላሉት ሰዎች ሁሉ የተሰበከ ነው፤ እኔ ጳውሎስም አገልጋይ የሆንኩት ለዚሁ ወንጌል ነው።
እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር እናውቃለን፤ እናምናለንም። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፤ በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል፤ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
ልጆች ሆይ! እናንተ የእግዚአብሔር ናችሁ፤ በእናንተ ያለው መንፈስ በዓለም ካለው መንፈስ ይበልጣል። ስለዚህ ሐሰተኞች ነቢያትን አሸንፋችኋል።
እነሆ! እኔ በበር ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ሰምቶ በሩን ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ ገብቼ ከእርሱ ጋር እበላለሁ፤ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል፤