Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኤፌሶን 3:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ደግሞም የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱና ርዝመቱ፥ ከፍታውና ጥልቀቱ፥ ምን ያኽል መሆኑን ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ማስተዋል እንድትችሉና

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 የክርስቶስ ፍቅር ስፋቱ፣ ርዝመቱ፣ ከፍታውና ጥልቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ፣ ከቅዱሳን ሁሉ ጋራ የመገንዘብ ኀይልን እንድታገኙ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ስፋቱና ርዝመቱ፥ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ማስተዋል ላይ እንድትደርሱ፥ ከቅዱሳን ሁሉ ጋር፥ እጸልያለሁ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ስፋ​ቱና ርዝ​መቱ፥ ምጥ​ቀ​ቱና ጥል​ቀቱ ምን ያህል እንደ ሆነ ከቅ​ዱ​ሳን ሁሉ ጋር ለማ​ስ​ተ​ዋል ትችሉ ዘንድ፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18-19 ከቅዱሳን ሁሉ ጋር ስፋቱና ርዝመቱ ከፍታውም ጥልቅነቱም ምን ያህል መሆኑን ለማስተዋል፥ ከመታወቅም የሚያልፈውን የክርስቶስን ፍቅር ለማወቅ ትበረቱ ዘንድ፥ እስከ እግዚአብሔርም ፍጹም ሙላት ደርሳችሁ ትሞሉ ዘንድ።

Ver Capítulo Copiar




ኤፌሶን 3:18
28 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ አሁን ተነሥተህ ከኀያሉ ታቦትህ ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ና፤ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፥ ካህናትህ ደኅንነትን ይልበሱ፤ ታማኞችህም በበረከትህ ይደሰቱ፤


ነገር ግን እግዚአብሔር ለሚያከብሩት ሁሉ ፍቅሩን ለዘለዓለም ያሳያቸዋል፤ ቸርነቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይተላለፋል።


የቅዱሳን ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ የከበረ ነው።


ካህናትህ የጽድቅን ሥራ ይሥሩ! ታማኞችህ በደስታ ይዘምሩ!


የአንተ ዕውቀት እጅግ ጥልቅ ነው፤ እኔ ላስተውለው ከምችለው በላይ ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ፍጡሮችህ ሁሉ ያመሰግኑሃል፤ ሕዝቦችህም ሁሉ ያወድሱሃል።


ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ መንገዴ ከመንገዳችሁ፥ ሐሳቤም ከሐሳባችሁ እጅግ ከፍ ያለ ነው።


እናንተም ተራራውን በሁለት ከፍሎ እስከ አጻል በደረሰው በዚህ ሸለቆ ውስጥ አልፋችሁ ታመልጣላችሁ፤ በይሁዳ ንጉሥ በዖዝያ ዘመን ምድር በተናወጠች ጊዜ የቀድሞ አባቶቻችሁ በሸሹት ዐይነት ትሸሻላችሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬም ቅዱሳኑን አስከትሎ ይመጣል።


ሰው ሕይወቱን ስለ ወዳጆቹ አሳልፎ ከመስጠት የበለጠ ፍቅር የለውም።


እግዚአብሔር ሰዎችን የሚያጸድቅበትን መንገድ ባለማወቃቸው የራሳቸውን የጽድቅ መንገድ ተከተሉ እንጂ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አልተከተሉም።


ምእመናን ሁሉ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።


እኔ ከክርስቶስ ጋር እንደ ተሰቀልኩ ያኽል ስለምቈጥር ከእንግዲህ ወዲህ ክርስቶስ በእኔ ውስጥ ይኖራል እንጂ እኔ ለራሴ ሕይወት የምኖር አይደለሁም፤ አሁንም በሥጋዊ አካሌ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን አሳልፎ በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ በማመን በተገኘው ሕይወት ነው።


“በእንጨት ላይ ተሰቅሎ የሚሞት ሁሉ የተረገመ ነው” ተብሎ ስለ ተጻፈ ክርስቶስ ስለ እኛ እንደ ተረገመ ሰው ሆኖ ሕግ ከሚያስከትለው ርግማን ዋጀን።


ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር በሥራ ላይ የሚያውለው ዕቅድ በሰማይና በምድር ያሉት ፍጥረቶች ሁሉ ተጠቃለው በአንዱ በክርስቶስ ሥልጣን ሥር እንዲሆኑ ነው።


ስለዚህ በጌታ በኢየሱስ ስላላችሁ እምነትና ለቅዱሳንም ሁሉ ስላላችሁ ፍቅር ሰምቼ


ይህን ከሰው ዕውቀት በላይ የሆነውን የክርስቶስን ፍቅር እንድታውቁ በእግዚአብሔር ፍጹም ሙላት ለመሞላትም እንድትበቁ እጸልያለሁ።


በኢየሱስ ክርስቶስ ያላችሁን እምነትና ስለ ምእመናን ሁሉ ያላችሁን ፍቅር ሰምተናል።


የሃይማኖታችን ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ እርሱም እግዚአብሔር፦ “ሰው ሆኖ ተገለጠ፤ እውነተኛነቱ በመንፈስ ታወቀ፥ ለመላእክት ታየ፥ ለሕዝቦች ሁሉ ተሰበከ፥ በዓለም ያሉ ሰዎች አመኑበት፥ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ” የሚል ነው።


እኔ ድል ነሥቼ ከአባቴ ጋር በዙፋኑ ላይ እንደ ተቀመጥኩ እንዲሁም ድል የነሣ ከእኔ ጋር በዙፋኔ ላይ እንዲቀመጥ አደርገዋለሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos