Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




1 ቆሮንቶስ 8:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋ የሆነ እንደ ሆነ፥ እርግጥ ነው “ሁላችንም ዕውቀት አለን፤” ይሁን እንጂ ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋ ደግሞ ይህን እላለሁ፤ ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን እናውቃለን። ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋ “ሁላችንም ዕውቀት እንዳለን፤” እናውቃለን። ዕውቀት ያስታብያል፤ ፍቅር ግን ያንጻል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለጣ​ዖ​ታት ስለ​ሚ​ሠዉ መሥ​ዋ​ዕ​ቶች ሁላ​ች​ንም ዕው​ቀት እን​ዳ​ለን እና​ው​ቃ​ለን፤ ዕው​ቀት ያስ​ታ​ብ​ያል፤ ፍቅር ግን ያን​ጻል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለጣዖት ስለ ተሠዋ ሥጋም፥ ሁላችን እውቀት እንዳለን እናውቃለን። እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል።

Ver Capítulo Copiar




1 ቆሮንቶስ 8:1
35 Referencias Cruzadas  

ነገር ግን ይህን የሚያውቁ፥ ሁሉም አይደሉም፤ አንዳንዶች እስከ አሁን ድረስ ጣዖትን ማምለክ ስለ ለመዱ ሥጋን የሚበሉት ለጣዖት እንደ ተሠዋ አድርገው ነው፤ ስለዚህ ኅሊናቸው ደካማ በመሆኑ ይረክሳሉ።


ስለዚህ ማንኛውንም ነገር የሚበላ ሰው የማይበላውን ሰው አይንቀፈው፤ የማይበላውም በሚበላው ሰው ላይ አይፍረድ፤ እርሱንም እግዚአብሔር ተቀብሎታልና።


ራሳቸውን ብልኆችና ጥበበኞች አድርገው ለሚቈጥሩ ወዮላቸው!


ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።


ስለዚህ ለጣዖት የተሠዋውን ሥጋ ስለ መብላት የሆነ እንደ ሆነ ጣዖት ሕይወት የሌለው እንደ ሆነና ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።


“ዕውቀት አለኝ” ብሎ የሚያስብ ሰው ቢኖር የሚገባውን ያኽል ገና አላወቀም።


ወንድሞቼ ሆይ! በደግነት የተሞላችሁ፥ በዕውቀት የበለጸጋችሁና እያንዳንዳችሁም ሌላውን ለመምከር የምትችሉ መሆናችሁን ተረድቼአለሁ።


የተለያዩት የሰውነት ክፍሎች የሚገጣጠሙት በክርስቶስ ነው፤ አካልም በሙሉ የተያያዘው በመገጣጠሚያዎቹ ነው፤ ስለዚህ እያንዳንዱ የአካል ክፍል የተመደበለትን ተግባር በሚገባ ሲያከናውን አካል በሙሉ ያድጋል፤ በፍቅርም ይታነጻል።


ወደ ልቡናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትም አትሥሩ፤ በእናንተ መካከል አንዳንዶች እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉ። ይህንንም የምለው እንድታፍሩ ብዬ ነው።


ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ ብትጠበቁ መልካም ታደርጋላችሁ፤ ደኅና ሁኑ።”


“በክፋትሽ ተዝናናሽ፤ ‘ማንም አያየኝም’ አልሽ፤ ጥበብሽና ዕውቀትሽ አባከኑሽ፤ በልብሽም ‘ማንም እንደኔ ያለ የለም’ አልሽ።


እነዚያም ሴቶች ለሞአብ ጣዖት የተሠዋውን መሥዋዕት እንዲመገቡ ጋበዙአቸው፤ እስራኤላውያንም የመሥዋዕቱን ምግብ በልተው ፔዖር በሚባለው ተራራ ላይ ለሚገኘው በዓል ለተባለውም ጣዖት ሰገዱ፤


ነገር ግን አንድ ሰው “ይህ ሥጋ ለጣዖት የተሠዋ ነው” ቢላችሁ ይህን በነገራችሁ ሰው ምክንያትና በኅሊናም ምክንያት ሥጋውን አትብሉ።


ከአሕዛብ ወገን ያመኑት ግን ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብ አትብሉ፤ ደምም አትብሉ፤ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ’ የሚለውን ውሳኔ የያዘ ደብዳቤ ጽፈን ልከንላቸዋል።”


ታዲያ፥ አባቶቻችንም ሆኑ እኛ ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በአማኞች ጫንቃ ላይ በመጫን ለምን አሁን እግዚአብሔርን ትፈታተኑታላችሁ?


ነገር ግን አንድ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ይኸውም ‘ነቢይት ነኝ’ የምትለዋን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለህ ታግሠሃታል፤ እርስዋ አገልጋዮቼ እንዲሴስኑና ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉ በማስተማር አሳስታቸዋለች።


በአጉል ትሕትናና መላእክትን በማምለክ የሚመካ ማንም ሰው ያለ ዋጋ እንዳያስቀራችሁ ተጠንቀቁ፤ እንዲህ ዐይነቱ ሰው ስለሚያየው ራእይ እየተመጻደቀ ከንቱና ሥጋዊ በሆነ አስተሳሰብ ይታበያል።


ወንድሞቼ ሆይ! ለክፉ ነገር ሕፃናት ሁኑ እንጂ በአስተሳሰባችሁስ እንደ ሕፃናት አትሁኑ፤ ይልቁንም በአስተሳሰባችሁ የበሰላችሁ ሁኑ።


እንግዲህ መመካታችሁ መልካም አይደለም፤ ትንሽ እርሾ ሊጡን ሁሉ እንደሚያቦካው ታውቁ የለምን?


ታዲያ፥ እንዲህ ያለ አሳፋሪ ነገር በመካከላችሁ እያለ ለምን ትታበያላችሁ? ይልቅስ በዚህ ነገር ማዘን አይገባችሁምን? እንዲህ ዐይነቱን ሥራ የፈጸመውን ሰው ከመካከላችሁ አስወግዱ።


ነገር ግን ከእናንተ አንዳንዶቹ እኔ እናንተን ለመጐብኘት የማልመጣ መስሎአቸው በትዕቢት ተሞልተዋል።


እኛ ስለ ክርስቶስ ብለን ሞኞች ሆነናል፤ እናንተ ግን በክርስቶስ ጥበበኞች ሆናችኋል፤ እንዲሁም እኛ ደካሞች ሆነናል፤ እናንተ ግን ብርቱዎች ሆናችኋል፤ እናንተ የተከበራችሁ ሆናችኋል፤ እኛ ግን የተዋረድን ሆነናል።


በሁሉ ነገር በንግግርም ሆነ በዕውቀት በክርስቶስ በልጽጋችኋል።


እንግዲህ ይህ እምነትህ በአንተና በእግዚአብሔር መካከል ይሁን፤ ትክክል ነው ብሎ የሚያምንበትን ነገር ሲያደርግ ኅሊናው የማይወቅሰው ሰው የተመሰገነ ነው።


አንድን ነገር ርኩስ ነው ብሎ ለሚያስብ ሰው ያ ነገር ለእርሱ ርኩስ ይሆንበታል እንጂ ማንኛውም ነገር በራሱ ርኩስ እንዳልሆነ እኔ በጌታ ኢየሱስ ዐውቄ አረጋግጣለሁ።


ታዲያ፥ አንተ በወንድምህ ላይ ለምን ትፈርዳለህ? ወይስ ወንድምህን ለምን ትንቀዋለህ? ሁላችንም በእግዚአብሔር የፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለን።


እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማምታችሁ ኑሩ፤ ራሳችሁን ከፍ ከማድረግ ይልቅ ትዕቢትን አስወግዳችሁ ከድኾች ጋር በአንድነት ኑሩ፤ በራሳችሁ ዐዋቂዎች ነን አትበሉ።


ወንድሞቼ ሆይ! “ዐዋቂዎች ነን” ብላችሁ አትመኩ፤ የምነግራችሁ አንድ ምሥጢር አለ፤ ይኸውም የእስራኤላውያን እምቢተኛነት ለዘለቄታው ሳይሆን አሕዛብ ሁሉ በሙላት ወደ እግዚአብሔር እስኪመጡ ድረስ መሆኑን ነው።


ስለዚህ ሰላም የሚገኝበትንና እርስ በርሳችን የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።


ወንድሞች ሆይ! እናንተን ለመጥቀም ብዬ በዚህ ጉዳይ እኔንና አጵሎስን እንደ ምሳሌ አድርጌ ተናገርኩ፤ ይህንንም ያደረግኹት “ከተጻፈው አትለፍ” የሚለውን ምክር ትርጒሙን ከእኛ እንድትማሩ ብዬ ነው፤ ስለዚህ በአንድ ሰው መመካት ሌላውን ሰው ግን መናቅ አይገባችሁም።


ይህንንም የምላችሁ አስተዋዮች በመሆናችሁ ነው፤ ስለዚህ እኔ የምናገረውን እናንተ ራሳችሁ ፍረዱ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios