ኤፌሶን 2:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መጥቶም ለእናንተ ርቃችሁ ለነበራችሁትና ቀርበው ለነበሩት ለአይሁድም የሰላምን የምሥራች ቃል ሰበከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተ፣ ቀርበው ለነበሩትም ለእነርሱ ሰላምን ሰበከ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን ሰበከ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጥቶም፤ ቀርበን ለነበርነው ሰላምን፥ ርቃችሁ ለነበራችሁት ለእናንተም ሰላምን ሰጠን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ |
በተራሮች ላይ ስለ ሰላምና ስለ መዳን የሚናገር፥ መልካም ዜናንም የሚያበሥር፥ “አምላክሽ ይነግሣል!” ብሎ ለጽዮን የሚነግራት የመልክተኛ እግሩ ምንኛ ድንቅ ነው!
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፤ “ዐሥር የብር መሐለቅ ያላት ሴት ከዐሥሩ አንዱ መሐለቅ ቢጠፋባት መብራት አብርታ፥ ቤትዋን ጠርጋ የጠፋባትን መሐለቅ እስክታገኝ ድረስ በጥንቃቄ አትፈልገውምን?
እግዚአብሔር ለእስራኤል ሕዝብ ቃሉን መላኩ የታወቀ ነው፤ በሁሉ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ሰላምን እየሰበከ የመጣውም ለእነርሱ ነው።
እግዚአብሔር ሰዎችን በእኛ አማካይነት ስለሚጠራ እኛ የክርስቶስ እንደራሴዎች ነን፤ ስለዚህ “ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ!” ብለን በክርስቶስ ስም እንለምናችኋለን።
“እኛ በምንለምነው ጊዜ ሁሉ አምላካችን እግዚአብሔር ለእኛ ቅርብ እንደሆነው፥ የየትኛው ሌላ ታላቅ ሕዝብ ነው አምላኩ ለእርሱ ቅርብ የሆነለት?