በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
መክብብ 3:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም “ሁሉ ነገር የሚፈጸምበት ጊዜ ስላለው እግዚአብሔር በዐመፀኞችም ሆነ በቅኖች ላይ ይፈርዳል” ብዬ አሰብኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በልቤ፣ “ለማንኛውም ድርጊት፣ ለማንኛውም ተግባር ጊዜ ስላለው፣ አምላክ ጻድቁንና ኀጢአተኛውን ወደ ፍርድ ያመጣቸዋል” ብዬ አሰብሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በልቤ፦ ለማንኛውም ነገርና ለማንኛውም ሥራ ጊዜ አለውና በጻድቅና በክፉ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም በልቤ፥ “በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቁና በኀጢአተኛው ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል” አልሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔም በልቤ፦ በዚያ ለነገር ሁሉና ለሥራ ሁሉ ጊዜ አለውና በጻድቅና በኃጢአተኛ ላይ እግዚአብሔር ይፈርዳል አልሁ። |
በደል ያልሠሩትን ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር ታጠፋለህ ብዬ አላስብም፤ ይህንን እንደማታደርገው አምናለሁ፤ ይህንንማ ካደረግህ ደጋግ ሰዎች ከኃጢአተኞች ጋር መቀጣታቸው ነው፤ ይህ ከቶ አይሆንም! የዓለም ሁሉ ፈራጅ በትክክል መፍረድ ይገባው የለምን?”
እኔማ በልቤ “ከእኔ በፊት ኢየሩሳሌምን ከገዙት ሁሉ ይበልጥ ታላቅና የጥበብ ሰው ሆኛለሁ፤ የጥበብንና የዕውቀትን ምንነት መርምሬ አጥንቻለሁ” ብዬ ነበር፤
ወጣት ሆይ! ወጣትነት እጅግ ግሩም ስለ ሆነ በወጣትነትህ ዘመን ደስ ይበልህ፤ በልብህም ሐሤት አድርግ፤ ዐይንህ የሚያየውንና ልብህ የሚመኘውን ሁሉ ፈጽም፤ ሆኖም ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንደሚያመጣህ ዕወቅ።
“ጊዜው ሲደርስ የግብጽ ንጉሥ በሶርያ ንጉሥ ላይ አደጋ ይጥልበታል፤ ሆኖም የሶርያ ንጉሥ በሠረገሎች፥ በፈረሶችና በመርከቦች በመጠቀም በብርቱ ጦርነት ይቋቋመዋል፤ እንደ ጐርፍ ውሃ በመጠራረግ ብዙ አገሮችን ይወራል።
እንደገናም እንዲህ አለኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ መጽሐፉን ዘግተህ አሽገው፤ የትንቢቱንም ቃል በምሥጢር ያዝ፤ በዚያን ጊዜ ሰዎች ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ይራወጣሉ፤ ምርምርና ዕውቀትም ይበዛል።”
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰልኝ፦ “ዳንኤል ሆይ! የዓለም መጨረሻ እስከሚሆንበት ጊዜ ድረስ ቃሉ የትንቢቱም ቃል ምሥጢር ሆኖ ስለሚጠበቅ እንግዲህ አንተ ሂድ።
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
እያንዳንዱ በምድራዊ ሕይወቱ ላደረገው ክፉም ሆነ ደግ ነገር እንደየሥራው ዋጋውን ለመቀበል ሁላችንም በክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት መቅረብ አለብን።
አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”