ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፥ አታገልግሉአቸው፤ አትስገዱላቸውም፤ በእጃችሁ ለሠራችኋቸው ጣዖቶች በመስገድ እግዚአብሔርን ለቊጣ አታነሣሡ፤ ይህን ትእዛዝ ብትጠብቁ እርሱ አይቀጣችሁም።’
ዘዳግም 8:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር አምላክህን ብትረሳና ትሰግድላቸውና ታገለግላቸውም ዘንድ ወደ ባዕዳን አማልክት ፊትህን ብትመልስ፥ በእርግጥ የምትጠፋ መሆንህን ዛሬውኑ አስጠነቅቅሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህን እግዚአብሔርን ብትረሳና ሌሎችን አማልክት ብትከተል፣ ብታመልክና ለእነርሱ ብትሰግድላቸው በርግጥ እንደምትጠፉ ዛሬ እመሰክርባችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ አምላክህንም ብትረሳና፥ ባዕዳን አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፉ ዛሬውኑ አበክሬ አስጠነቅቅሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህንም እግዚአብሔርን ፈጽሞ ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል፥ ብታመልካቸውም፥ ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬውኑ ሰማይንና ምድርን አስመሰክርብሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህንም እግዚአብሔርን ብትረሳ፥ ሌሎችንም አማልክት ብትከተል ብታመልካቸውም ብትሰግድላቸውም፥ ፈጽሞ እንድትጠፉ እኔ ዛሬውኑ እመሰክርባችኋለሁ። |
ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፥ አታገልግሉአቸው፤ አትስገዱላቸውም፤ በእጃችሁ ለሠራችኋቸው ጣዖቶች በመስገድ እግዚአብሔርን ለቊጣ አታነሣሡ፤ ይህን ትእዛዝ ብትጠብቁ እርሱ አይቀጣችሁም።’
መጻተኞችን፥ እናትና አባት የሞቱባቸውን ልጆችና፥ ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በመጨቈን አትበዝብዙ፤ በዚህች ምድር የሚኖሩ ንጹሓን የሆኑ ሰዎችን በግፍ አትግደሉ፤ እንዳትጠፉም ለሐሰተኞች አማልክት አትስገዱ።
በነገሠም በመጀመሪያው ዓመት እኔ ዳንኤል ቅዱሳት መጻሕፍትን እየተመለከትኩ እግዚአብሔር ለነቢዩ ለኤርምያስ በነገረው መሠረት ኢየሩሳሌም ፍርስራሽ ሆና የምትቈይባት ዘመን ሰባ ዓመት መሆኑን ዐወቅሁ።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የአሕዛብ “መንግሥታትን አጠፋሁ፤ ምሽጎቻቸውን አፈራረስኩ፤ መንገዶቻቸውን ማንም የማይተላለፍባቸው ባዶ አድርጌአቸዋለሁ፤ ከተሞቻቸውን ሕዝብ የሌለባቸው፥ ማንም የማይኖርባቸው ባድማ አድርጌአቸዋለሁ።
ለቀድሞ አባቶቻቸው በመሐላ ቃል ኪዳን በገባሁላቸው መሠረት በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ምድር አስገባቸዋለሁ፤ በዚያም በልተው በጠገቡና በወፈሩ ጊዜ እኔን ይተዋሉ፤ ቃል ኪዳኔንም አፍርሰው ሌሎች አማልክትን ያመልካሉ።
ይህን ብታደርጉ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትወርስዋት ምድር ረጅም ጊዜ እንደማትኖሩባትና በፍጹም እንደምትደመሰሱ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን ምስክር አድርጌ እነግራችኋለሁ።
አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።