“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።
ዘዳግም 7:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ አንተን ይወድሃል፤ ይባርክህማል፤ ስለዚህም በቊጥር ትበዛለህ፤ የምትወልዳቸው ልጆች ይባረካሉ፤ የምድርህም ፍሬ ይባረካል፤ ስለዚህም ብዙ እህል፥ ወይንና የወይራ ዘይት ታገኛለህ፤ ከዚህም ጋር ብዙ የከብትና የበግ መንጋ ያበዛልሃል፤ ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ ተስፋ በሰጠው ምድር ላይ ይህን ሁሉ በረከት ይሰጥሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይወድድሃል፤ ይባርክሃል፤ ያበዛሃልም። ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የማሕፀንህን ፍሬ፣ የምድርህን ሰብል፣ እህልህን፣ አዲሱን ወይንና ዘይት፤ የከብት መንጋህን ጥጆች፣ የበግና የፍየል መንጋህን ግልገሎች ይባርካል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ እንዲሁም የምድርህንም ፍሬ፥ እህልና ወይንህን፥ ዘይትህንም፥ በከብትም ብዛት በበግም መንጋ አብዝቶ ይባርክልሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይወድድህማል፤ ይባርክህማል፤ ያባዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ፥ የመሬትህንም ፍሬ፥ እህልህን፥ ወይንህንም፥ ዘይትህንም፥ የከብትህንም ብዛት፥ የበግህንም መንጋ ይባርክልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይወድድህማል፥ ይባርክህማል፥ ያበዛህማል፤ ይሰጥህም ዘንድ ለአባቶችህ በማለላቸው ምድር የሆድህን ፍሬ የመሬትህንም ፍሬ፥ እህልህን ወይንህንም ዘይትህንም፥ የከብትህንም ብዛት የበግህንም መንጋ ይባርክልሃል። |
“ቃል ኪዳንህንና ዘለዓለማዊ ፍቅርህን የምትጠብቅ፥ ታላቁ፥ ኀያሉና አስፈሪው አምላካችን ሆይ! በእኛ፥ በንጉሦቻችን፥ በመሪዎቻችን፥ በካህኖቻችን፥ በነቢዮቻችን፥ በቅድመ አያቶቻችን፥ እንዲሁም በሕዝብህ ሁሉ ላይ፥ ከአሦር ነገሥታት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ፥ የደረሰውን መከራ ሁሉ አስብ።
እርሱ አንተን የሚፈራህ እርሱንና ልጆቹን፥ ያለውንም ንብረት ሁሉ በደኅና ስለ ጠበቅህለት፥ የሚሠራውንም ሁሉ ስለ ባረክህለትና ብዙ የከብት መንጋ ስለ ሰጠኸው አይደለምን?
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።
እርሱም፦ ፍሬዋን በየወቅቱ እንደምትሰጥ፥ ቅጠሏም እንደማይረግፍ፥ በፈሳሽ ውሃ ዳር እንደ ተተከለች ዛፍ ይሆናል፤ የሚሠራውም ሥራ ሁሉ ይሳካለታል።
“እኔን የሚወደኝ ትእዛዜን የሚቀበልና በሥራ ላይ የሚያውለው ነው፤ እኔንም የሚወደኝን አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ፤ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”
እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”
እግዚአብሔር ከአስፈሪ ቊጣው ተመልሶ ምሕረት ያደርግልህ ዘንድ እንዲወድም ከተወሰነው ሀብት አንዳችም ለራስህ አታስቀር፤ ይህን ብታደርግ ለአባቶችህ በመሐላ በገባው ቃል ኪዳን መሠረት ቊጥርህን ያበዛዋል።
“ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ብትታዘዝና ዛሬ እኔ የምሰጥህንም ትእዛዞች ሁሉ በታማኝነት ብትጠብቅ፥ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤
እግዚአብሔር ለአንተ ይሰጥህ ዘንድ ለቀድሞ አባቶችህ በማለላቸው ምድር ብዙ ልጆችን፥ ብዙ የቀንድ ከብትና የተትረፈረፈ የእርሻን ሰብል ይሰጥሃል፤
በዚህም ዐይነት የቀድሞ አባቶችህ የነበሩበትን ምድር እንደገና ትወርሳለህ፤ እርሱም ከቀድሞ አባቶችህ ይበልጥ ባለጸጋና ቊጥርህ የበዛ እንድትሆን ያደርጋል።
“እግዚአብሔር እናንተን የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከሌሎች ሕዝቦች ይበልጥ ብዙዎች በመሆናችሁ አይደለም፤ ይልቁንም እናንተ በምድር ላይ ከሁሉ በቊጥር ያነሳችሁ ሕዝብ ነበራችሁ።