በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
ዘዳግም 6:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በገባላቸው የተሰፋ ቃል መሠረት አንተ ያልገነባሃቸው ታላላቅና የሚያማምሩ ከተሞች ያሉበትን ምድር ይሰጥሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይሥሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ሲያስገባህ፣ በዚያም ያልሠራሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞችን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ጌታ አምላክህ ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ፥ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደ ማለላቸው ምድር ባስገባህ ጊዜ፥ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ፥ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ፤ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ለአንተ ሊሰጣት ለአባቶችህ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ባገባህ ጊዜ፤ ያልሠራሃቸውንም ታላቅና መልካም ከተሞች፥ |
በዚያን ዕለት እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ በማለት ቃል ኪዳን ገባለት፦ “ከግብጽ ወንዝ ጀምሮ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ ያለውን ምድር ሁሉ ለዘሮችህ እሰጣለሁ፤
እዚሁ ኑር፤ እኔም ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እባርክሃለሁም፤ ይህን ምድር ለአንተና ለዘርህ እሰጣለሁ፤ በዚህ ዐይነት ለአባትህ ለአብርሃም የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤
እግዚአብሔርም በአጠገቡ ቆሞ እንዲህ አለው፤ “እኔ የአባትህ የአብርሃምና የይስሐቅ አምላክ እግዚአብሔር ነኝ፤ ለአንተና ለትውልድህ እንዲሆን ይህን የተኛህበትን ምድር እሰጥሃለሁ፤
የተመሸጉ ከተሞችንና፥ ለም የሆነችውን ምድር፤ በመልካም ነገር ሁሉ የተሟሉ ቤቶችን፥ የውሃ ጒድጐዶችንና የወይን ተክል ቦታዎችን የወይራና ብዙ የፍሬ ዛፎችን ወረሱ፤ በልተው በመጥገብም ሰውነታቸውን አወፈሩ፤ በቸርነትህ በሰጠሃቸው መልካም ነገር ሁሉ ተደሰቱ።
እነሆ፥ ምድሪቱ በፊታችሁ ናት፤ እኔ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻችሁ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ፥ እንዲሁም ለዘሮቻቸው ላወርሳቸው የተስፋ ቃል የገባሁላቸውን ምድር ሄዳችሁ ውረሱ።’ ”
ለቀድሞ አባቶቻቸው በመሐላ ቃል ኪዳን በገባሁላቸው መሠረት በማርና በወተት ወደ በለጸገችው ምድር አስገባቸዋለሁ፤ በዚያም በልተው በጠገቡና በወፈሩ ጊዜ እኔን ይተዋሉ፤ ቃል ኪዳኔንም አፍርሰው ሌሎች አማልክትን ያመልካሉ።
በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንልሃል፤ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ በገባውም ተስፋ ቃል መሠረት መልካሚቱን ምድር ትወርሳለህ፤
“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! አድምጥ፤ ከአንተ የሚበልጡትንና በኀይልም ብርቱ የሆኑትን የአሕዛብ ምድርና ቅጽሮቻቸው እስከ ሰማይ የደረሱ ታላላቅ ከተሞቻቸውን ለመውረስ ትገባ ዘንድ ዛሬ ዮርዳኖስን ትሻገራለህ።
እናንተ በማረስ ያልደከማችሁበትን የለማ ምድርና ያልሠራችኋቸውንም ከተሞች መኖሪያ አድርጌ ሰጠኋችሁ፤ እነሆ፥ አሁን ያልተከላችሁትን የወይን ተክልና ያልደከማችሁበትን የወይራ ዛፍ ፍሬ እየተመገባችሁ ትኖራላችሁ።’ ”