Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 በእግዚአብሔር ዘንድ ትክክልና መልካም የሆነውን ሁሉ አድርግ፤ ይህን ብታደርግ ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ ይከናወንልሃል፤ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶችህ በገባውም ተስፋ ቃል መሠረት መልካሚቱን ምድር ትወርሳለህ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 መልካም እንዲሆንልህና እግዚአብሔር ለአባቶችህ በመሐላ እንድትወርሳት፣ በእግዚአብሔር ፊት ተስፋ የሰጣቸውን መልካሚቱን ምድር ገብተህ ቀናና መልካም የሆነውን አድርግ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 መልካም እንዲሆንልህ፥ ጌታም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርሷን እንድትወርስ በጌታ ፊት ትክክልና መልካሙን አድርግ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 መል​ካ​ምም ይሆ​ን​ልህ ዘንድ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለአ​ባ​ቶ​ችህ ወደ ማለ​ላ​ቸው ወደ መል​ካ​ሚቱ ምድር ገብ​ተህ እር​ስ​ዋን ትወ​ርስ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቅኑ​ንና መል​ካ​ሙን አድ​ርግ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18-19 መልካምም ይሆንልህ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም ለአባቶችህ ወደ ማለላቸው ወደ መልካሚቱ ምድር ገብተህ እርስዋን ትወርስ ዘንድ፥ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ ጠላቶችህን ሁሉ ከፊትህ ያወጣልህ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ፊት ቅኑንና መልካሙን አድርግ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 6:18
23 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር አምላካችሁ ለዘለዓለም እንድትኖሩባት በሚያወርሳችሁ ምድር ለረጅም ዘመን ትኖሩ ዘንድ ለእናንተና ከእናንተም በኋላ ለልጆቻችሁ መልካም እንዲሆንላቸው እኔ ዛሬ የማዛችሁን ሕጉንና ትእዛዞቹን ጠብቁ።”


ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ መልካም ይሆንልህ ዘንድ ደምን አትብላ፤ ይህንንም በማድረግህ እግዚአብሔርን ደስ ታሰኛለህ።


መልካሙንና ደስ የሚያሰኘውን ፍጹም የሆነውንም የእግዚአብሔርን ፈቃድ ማወቅ እንድትችሉ አእምሮአችሁን በማደስ ሕይወታችሁ ይለወጥ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉት።


ሁልጊዜ በዚህ ዐይነት ቢያስቡማ እንዴት መልካም ነበር! ሁልጊዜ ቢያከብሩኝና ትእዛዞቼንም ሁሉ ቢፈጽሙ ሁሉ ነገር ለእነርሱና ለዘሮቻቸው ለዘለዓለም በመልካም ሁኔታ በተከናወነላቸው ነበር።


የላከኝ ከእኔ ጋር ነው፤ ዘወትር የማደርገው እርሱን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ስለ ሆነ ብቻዬን አልተወኝም።”


ክፉም ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ በእርሱ ይኖራል።


ጥበብ ያላቸው እነዚህን ነገሮች ይረዳሉ፤ አስተዋዮችም ያውቋቸዋል፤ የእግዚአብሔር መንገድ ትክክል ነው፤ ጻድቃን ይሄዱበታል፤ ኃጢአተኞች ግን ይሰናከሉበታል።


የሠራውን ኃጢአት ሁሉ ይቅር እልለታለሁ፤ እውነተኛና ትክክለኛ የሆነውን ሥራ በመሥራቱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል።


አንድን ክፉ ሰው በእርግጥ እንደሚሞት ባስታውቀውና እርሱ ግን ኃጢአት መሥራቱን ትቶ ሕጋዊና ትክክለኛ የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥


እንዲሁም ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራት ትቶ ፍትሓዊና ትክክለኛ ሥራ ቢሠራ ሕይወቱን ያድናል፤


“ክፉ ሰው ኃጢአት መሥራትን ትቶ ሕጌን ቢጠብቅ፥ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር ቢያደርግ፥ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም፤


“ሰው ጻድቅ፥ ፍትሓዊና ትክክለኛ ቢሆን፥


ሁሉ ነገር ስለሚሳካላቸውና የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ስለሚያገኙ ጻድቃንን የተባረካችሁ ናችሁ በሉአቸው።


እንዲሁም አገልጋይህ በእነርሱ ይመከራል፤ እነርሱንም በመጠበቅ ታላቅ ዋጋ ያገኛል።


ዛሬ እኔ የሰጠሁህን ትእዛዞች ብትጠብቅና እርሱ ከአንተ የሚፈልገውንም ሁሉ ብታደርግ ይህ ተስፋ በእርግጥ ይፈጸምልሃል።


ለአንተና ከአንተም በኋላ ለልጆችህ ለዘለዓለም መልካም ይሆንላችሁ ዘንድ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች ሁሉ በጥንቃቄ ጠብቅ፤ ይህንንም ስታደርግ በአምላክህ በእግዚአብሔር ፊት መልካምና ቅን ነገርን ማድረግህ ነው።


“እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ።


ሁሉ ነገር በመልካም ሁኔታ እንዲከናወንላችሁ፥ በምትወርሱአትም ምድር ለረጅም ዘመናት እንድትኖሩ፥ እግዚአብሔር ያዘዛችሁን ሁሉ ፈጽሙ።


እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”


“ ‘ታዲያ ልጁ በአባቱ ኃጢአት ምክንያት ያልተቀጣው ስለምንድን ነው?’ ትሉ ይሆናል፤ ልጁ ትክክልና መልካም የሆነውን ነገር አድርጎአል፤ ሕጌን አክብሮአል፤ ስለዚህ እርሱ በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፤


ይህንንም የምታደርገው ጌታ በሰጠህ ተስፋ መሠረት ጠላቶችህን ሁሉ በማባረር ነው።


“አምላክ ሆይ! በታማኝነትና በሙሉ ልብ እንዳገለገልኩህ፥ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር እንዳደረግሁ አስታውስ፤” ምርር ብሎም አለቀሰ።


“እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ በገባላቸው የተሰፋ ቃል መሠረት አንተ ያልገነባሃቸው ታላላቅና የሚያማምሩ ከተሞች ያሉበትን ምድር ይሰጥሃል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios