ዘዳግም 32:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቊጣዬ እሳት ይቀጣጠላል፤ እስከ ሲኦል ጥልቀት ድረስ ይነዳል፤ ምድርንና ምርቱን ይበላል። ቃጠሎውም እስከ ተራራዎች መሠረት ድረስ ያቃጥላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቍጣዬ እሳት ተቀጣጥሏልና፤ እርሱ እስከ ሲኦል ዘልቆ ይነድዳል። ምድርን እስከ ሰብሏ ይበላል፤ የተራሮችንም መሠረት ያቀጣጥላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለች፤ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረትም ታነድዳለች።’” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሳት ከቁጣዬ ትነድዳለችና፥ 2 እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፥ 2 ምድርንም ከፍሬዋ ጋር ትበላለች፥ 2 የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች። |
ስለዚህም ርግማን ምድርን ያጠፋል፤ ሕዝቦችዋም በበደሉት በደል ተጠያቂዎች ይሆናሉ፤ ስለዚህ የምድር ነዋሪዎች ይደመሰሳሉ፤ የሚተርፉትም ጥቂቶች ናቸው።
ከብዙ ዘመናት በፊት የአሦር ንጉሠ ነገሥት የሚቃጠልበት ቦታ ተዘጋጅቶ ነበር፤ ያም ቦታ ሰፊና ጥልቅ ሆኖ ብዙ እንጨት ተከማችቶበት ነበር፤ እንደ ዲን ጅረት የሚፈሰው የእግዚአብሔር እስትንፋስ እሳቱን ያቀጣጥለዋል።
ተራራዎችና ኰረብቶች ሊናወጡና ሊፈርሱ ይችላሉ፤ እኔ ለአንቺ ያለኝ ፍቅር ግን ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ የሰላምንም የተስፋ ቃሌን ለዘለዓለም እጠብቅልሻለሁ፤” ይላል ለአንቺ የሚራራ እግዚአብሔር።
ቊጣዬ እንደ እሳት እንዲቀጣጠል ስላደረጋችሁ እርሱም ለዘለዓለም ስለሚነድ የሰጠኋችሁን ርስት ሁሉ እንድታጡና በማታውቁት አገር ጠላቶቻችሁን እንድታገለግሉ አደርጋለሁ።”
እናንተ የይሁዳ ሕዝብና የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ሆይ! የልባችሁን ክፋት ገርዛችሁ አእምሮአችሁን በማንጻት ሁለንተናችሁን ለእግዚአብሔር አስገዙ፤ ይህን ባታደርጉ ግን በክፉ ሥራችሁ ምክንያት ቊጣዬ እንደ እሳት ይነዳል፤ ቊጣዬም ከነደደ ማንም ሊያጠፋው አይችልም።”
ጌታ የእስራኤልን መኖሪያ ሁሉ ያለ ምሕረት አጠፋ፤ በቊጣውም የይሁዳን ሕዝብ ምሽግ አፈረሰ፤ መንግሥትዋንና ባለ ሥልጣኖቿን ወደ ምድር ጥሎ አዋረደ።
በኀይለኛ ቊጣው የእስራኤልን ኀይል ሁሉ አዳከመ፤ ጠላትም እያየ ለእነርሱ የሚሰጠውን ድጋፍ አቋርጦ፥ በያዕቆብም ዘር ላይ እንደሚንበለበል እሳት ቊጣውን አቀጣጠለ፤ ቊጣው ጐረቤቶቹንም ሁሉ አወደመ።
እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ በቀኝ እጁ የያዘውን በእኛ ላይ አነጣጠረ፤ በኢየሩሳሌም ከተማ የምንመካባቸውን ሁሉ ገደለ፤ ቊጣውንም እንደ እሳት አቀጣጠለ።
ነገር ግን በቊጣ ከስሩ ተነቅሎ ወደ ምድር ተጣለ። ከበረሓ የሚነሣ የምሥራቅ ነፋስ አደረቀው፤ ፍሬዎቹም ረገፉ፤ ብርቱ የሆኑት ቅርንጫፎቹም ደረቁ፤ እሳትም በላቸው።
“በኀይለኛ ቅናቴ በሌሎች ሕዝቦች ላይና በመላዋ ኤዶም ላይ እናገራለሁ፤ እነርሱ ደስታን በተመላ ስሜትና በፍጹም ንቀት መሰማሪያዋን ለመውረር ምድሬን ርስታቸው አደረጉት፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።
ይልቅስ ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ አለበለዚያ እግዚአብሔር የእስራኤልን ሕዝብ እንደ እሳት ሆኖ ያጋያቸዋል፤ የቤትኤልንም ኗሪዎች እሳት ይበላቸዋል፤ እሳቱን የሚያጠፋላቸውም አይገኝም።
ጌታ እግዚአብሔር የገለጠልኝ ሌላውም ራእይ ይህ ነው፤ እነሆ፥ ጌታ እግዚአብሔር የእሳት ቅጣት ፍርድ አስተላለፈ፤ እሳቱም ባሕሩን በልቶ ካደረቀው በኋላ ምድርን ማቃጠል ጀመረ።
በዚያን ጊዜ ሰም በእሳት እንደሚቀልጥና፥ ውሃም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ታች እንደሚወርድ እንዲሁም ተራራዎች ከእርሱ ሥር ይቀልጣሉ፤ ሸለቆዎችም ይከፈታሉ።
ተራራዎች አንተን አይተው በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ የዝናብም ጐርፍ ምድርን እየጠራረገ አለፈ፤ ውቅያኖስ ከፍተኛ ድምፅ አሰማ፤ ማዕበሉም ወደ ላይ ከፍ ከፍ አለ።
እግዚአብሔር ቊጣውን በሚገልጥበት በዚያን ቀን ሰዎችን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እንደ እሳት ባለው ቅናቱ ምድር ሁሉ ትጠፋለች፤ ይህም የሚሆነው በዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በድንገት የሚያልቁ ስለ ሆነ ነው።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ጥቂት ታገሡ፤ በእነርሱ ላይ የምፈርድበት ጊዜ ይመጣል፤ ሕዝቦችንና መንግሥታትን ሰብስቤ ኀይለኛ ቊጣዬን አወርድባቸዋለሁ፤ ከቊጣዬም ኀይለኛነት የተነሣ መላዋ ምድር ትጠፋለች።
ዐይንህም ኃጢአት እንድትሠራ ቢያስትህ አውጥተህ ወዲያ ጣለው! ሁለት ዐይን ኖሮህ ወደ ገሃነም እሳት ከምትጣል ይልቅ አንድ ዐይና ሆነህ ወደ ዘለዓለም ሕይወት መግባት ይሻልሃል።
እግዚአብሔር ለእንደዚህ ያለው ሰው ይቅርታ አያደርግም፤ ይልቁንም የእግዚአብሔር ቊጣና ቅናት በእርሱ ላይ እንደ እሳት ይነዳል፤ እግዚአብሔርም እንደዚህ ያለውን ሰው ፈጽሞ እስኪደመስሰው ድረስ በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት መቅሠፍቶች ሁሉ ይወርዱበታል።
ከሰማይ የሚገለጠውም በሚንበለበል እሳት ነው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የማያውቁትንና ለጌታችን ለኢየሱስ ወንጌል የማይታዘዙትን ይቀጣቸዋል።