ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ዘዳግም 18:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በወንድሞቻቸው በእስራኤላውያን መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ርስታቸው ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በወንድሞቻቸው መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ በሰጣቸው ተስፋ መሠረት ጌታ ርስታቸው ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በወንድሞቻቸውም መካከል ርስት አይኖራቸውም፤ እርሱ እንደ ተናገራቸው ርስታቸው እግዚአብሔር ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በወንድሞቻቸውም መካከል ርስት አይሆንላቸውም፤ እርሱ እንደተናገራቸው ርስታቸው እግዚአብሔር ነው። |
ከዚህ በኋላ አብራም ራእይ አየ፤ እግዚአብሔርም “አብራም፥ አትፍራ፤ እንደ ጋሻ ሆኜ ከአደጋ ሁሉ እጠብቅሃለሁ፤ ታላቅ በረከትም እሰጥሃለሁ” ሲል ሰማው።
ጌታችንና አምላካችን ሆይ! አንተ እንደ ፀሐይና እንደ ጋሻ ነህ፤ በቸርነትና በክብር ትጠብቀናለህ፤ ደግ ለሚሠሩ ሰዎች ማናቸውንም መልካም ነገር አትከለክላቸውም።
እናንተ ግን “የእግዚአብሔር ካህናትና የአምላካችን አገልጋዮች” ተብላችሁ ትጠራላችሁ። በሕዝቦች ሀብት ትደሰታላችሁ፤ በብልጽግናቸውም ትከብራላችሁ።
እግዚአብሔር አሮንን እንዲህ አለው፦ “ለትውልድ የሚተላለፍ ምንም ዐይነት ርስት አትቀበልም፤ ከእስራኤልም ምድር የትኛውም ክፍል ለአንተ አይሆንም፤ እኔ እግዚአብሔር ራሴ ለአንተ ርስትህ ነኝ።”
ነገር ግን መሠዊያውንና ከመጋረጃው በስተውስጥ በኩል ያለውን ቅድስተ ቅዱሳኑን የሚመለከተውን የክህነት አገልግሎት የምትፈጽሙ አንተና ልጆችህ ብቻ ናችሁ፤ የክህነትን አገልግሎት ዕድል ፈንታ አድርጌ ስለ ሰጠኋችሁ ይህ ሁሉ ኀላፊነት የእናንተ ነው፤ ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ወደዚያ ቢቀርብ ይሞታል።”
የሌዊ ነገድ ከሌሎቹ ወንድሞቹ ጋር ርስት እንዲኖረው ያልተደረገበትም ምክንያት ይኸው ነው፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ አስቀድሞ እንደ ተናገረ ካህናት ሆነው የማገልገልን መብት በማግኘታቸው ራሱ እግዚአብሔር ለሌዋውያን ርስታቸው ነው።)
ሙሴ ለሌዊ ነገድ የርስት ድርሻ አልሰጠም፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር በመሠዊያ ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ ከሚቀርበው መባ የሚያገኙት ድርሻ እንደ ርስት ሆኖ ተመድቦላቸዋል።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚያስደንቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችኹ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።