ዘዳግም 17:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያን ሰው ወይም ያቺን ሴት ከከተማ ወደ ውጪ አውጥተህ በድንጋይ ወግረህ ግደል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፣ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ክፉ ድርጊት የፈጸመውን ወንድ ወይም ሴት ወደ ከተማ ደጅ ወስደህ፥ ያን ሰው እስኪሞት ድረስ በድንጋይ ውገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ታወጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትመትዋቸዋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህን ክፉ ነገር የሠሩትን ያን ወንድ ወይም ያችን ሴት ወደ በርህ ታመጣቸዋለህ፥ እስኪሞቱም ድረስ በድንጋይ ትወግራቸዋለህ። |
“ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ብለህ ንገር፦ ከእናንተም ሆነ ወይም በመካከላችሁ ከሚኖሩት የውጪ አገር ተወላጆች ውስጥ፥ ማንም ሰው ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ባዕድ አምላክ ከልጆቹ አንዱን አሳልፎ ሰጥቶ ቢገኝ መላው የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው።
“ያን ሰው ከሰፈር አውጣ፤ ሲሳደብ የሰማው ሰው ሁሉ ያ ሰው በደል የሠራ መሆኑን ለመመስከር እያንዳንዱ እጁን በዚያ ሰው ራስ ላይ ይጫን፤ ከዚያም በኋላ መላው የእስራኤል ሕዝብ በድንጋይ ወግሮ ይግደለው፤
የእግዚአብሔርን ስም የሚሰድብ ይገደል፤ ማኅበረሰቡ ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ እስራኤላዊም ሆነ መጻተኛ የእግዚአብሔርን ስም ሲሰድብ ይገደል።
በባርነት ከኖራችሁባት ከግብጽ ምድር ነጻ በማውጣት በአዳናችሁ በእግዚአብሔር ላይ እንድታምፁ የሚያደርጋችሁን ሕልም አላሚ ወይም ነቢይ ነኝ ባዩን ሁሉ ግደሉ፤ እንደዚህ ያለው ሰው ጸንታችሁ እንድትኖሩበት እግዚአብሔር አምላካችሁ ካዘዛችሁ መንገድ ሊለያችሁ ያቀደ ነው፤ ስለዚህ እናንተ ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
የከተማይቱም ሰዎች ሁሉ በድንጋይ ወግረው ይግደሉት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ታስወግዳላችሁ፤ በእስራኤልም የሚኖር ሁሉ ይህን ሁኔታ ሰምቶ ይፈራል።
በአባትዋ ቤት እያለች አሳፋሪ የሆነውን የዝሙት ሥራ በእስራኤል መካከል ስለ ሠራች ወደ አባትዋ ቤት ደጃፍ ይውሰዱአት፤ በዚያም እርስዋ የምትኖርበት ከተማ ሰዎች በድንጋይ ወግረው ይግደሉአት፤ በዚህም ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ሁለቱንም ከከተማይቱ ወደ ውጪ አውጥታችሁ በድንጋይ ወግራችሁ ግደሉ፤ ልጃገረዲቱ መሞት የሚገባት ሰው ሊሰማ በሚችልበት ከተማ ውስጥ እያለች ርዳታ እንዲደረግላት የጩኸት ድምፅ ባለማሰማትዋ ነው፤ ሰውየውም የሚሞትበት ምክንያት ለሌላ ሰው ከታጨች ልጃገረድ ጋር በመተኛት ሕግን በማፍረሱ ነው፤ በዚህ ዐይነት ይህን ክፉ ነገር ከመካከላችሁ አስወግዱ።
ኢያሱም “ይህን ሁሉ መከራ በእኛ ላይ ያመጣህብን ስለምንድን ነው? እነሆ! በአንተም ላይ ዛሬ እግዚአብሔር መከራን ያመጣብሃል!” አለው። ከዚህ በኋላ ሕዝቡ ሁሉ ዓካንን በድንጋይ ወግረው ገደሉት፤ ቤተሰቡንም በድንጋይ ወግረው ንብረቱን ሁሉ አቃጠሉ፤
ኢዮአስ ግን በቊጣ ተነሣሥተው በእርሱ ላይ የመጡትን ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ለበዓል ትሟገታላችሁን? እርሱንስ ታድኑታላችሁን? ለእርሱ የሚሟገትለት ሁሉ እስከ ነገ ጧት ይገደላል፤ እርሱ አምላክ ከሆነ መሠዊያውን ካፈረሰው ሰው ጋር ለራሱ እስቲ ይሟገት!”