Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 17:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ሆኖም በዚህ ሁኔታ በሞት መቀጣት የሚገባው ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች በእርሱ ላይ ከመሰከሩበት በኋላ ነው፤ ምስክሩ አንድ ብቻ ከሆነ ግን ያ ሰው አይገደል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ሞት የሚገባው ሰው፣ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ሞት የሚገባው ሰው፥ በሁለት ወይም በሦስት ሰዎች ምስክርነት ይገደል፤ ነገር ግን በአንድ ሰው ምስክርነት ብቻ ማንም ሰው አይገደል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 በሁ​ለት ወይም በሦ​ስት ምስ​ክ​ሮች ሞት የሚ​ገ​ባ​ቸው ይገ​ደሉ፤ በአ​ንድ ምስ​ክር ግን አይ​ገ​ደሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች አፍ ሞት የሚገባው ይገደል፤ በአንድ ምስክር አፍ አይገደል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 17:6
8 Referencias Cruzadas  

“በግድያ ወንጀል የተከሰሰ ማንኛውም ሰው የሞት ፍርድ ሊበየንበት የሚችለው ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የሆኑ ሰዎች የመሰከሩበት እንደ ሆነ ነው፤ የአንድ ሰው ምስክርነት ግን ለግድያ ወንጀል የተከሰሰውን ሰው ሊያስጠይቀው አይችልም።


የሙሴን ሕግ የጣሰ ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ከመሰከሩበት ያለ ምሕረት በሞት ይቀጣል።


ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ካልመሰከሩበት በቀር በቤተ ክርስቲያን ሽማግሌ ላይ የሚቀርበውን ክስ አትቀበል።


ባይሰማህ ግን የሁለት ወይም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ስለሚጸና ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ይዘህ ወደ እርሱ ሂድ።


“የአንድን ሰው ወንጀለኛነት ለማረጋገጥ አንድ ምስክር ብቻ አይበቃም፤ አንድ ሰው ወንጀለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ሁለት ወይም ሦስት ምስክሮች ያስፈልጋሉ።


እንግዲህ ወደ እናንተ ስመጣ ይህ ሦስተኛዬ ነው፤ መቼም ሁሉ ነገር የሚረጋገጠው በሁለት ወይም በሦስት ምስክሮች ነው።


“በሕጋችን መሠረት አንድ ሰው የክስ መልስ አስቀድሞ ሳይሰማለትና ምን እንዳደረገ ሳይታወቅ ይፈረድበታልን?” አላቸው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios