ዘዳግም 17:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህ ወደሚሰጥህ ምድር በመግባት ምድሩን ወርሰህ ከተደላደልክ በኋላ በዙሪያዬ እንዳሉት ሕዝቦች ንጉሥ ላንግሥ ብትል፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፣ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፣ “በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፣ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ” ብትል፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ወደሚሰጥህ ምድር ስትገባ፥ በምትወርሳትና በምትቀመጥባት ምድር፥ ‘በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ፥ እኔም በላዬ ንጉሥ ላንግሥ’ ብትል፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾማለሁ ብትል፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር ወደሚሰጥህ ምድር በገባህ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በተቀመጥህባትም ጊዜ፦ በዙሪያዬ እንዳሉት አሕዛብ ሁሉ በላዬ ንጉሥ አነግሣለሁ ስትል፥ |
“እግዚአብሔር አምላክህ ልትወርሳት ወደምትገባባት ምድር በሚያመጣህ ጊዜ በፊትህ ያሉትን ብዙ ሕዝቦች ያስወግድልሃል፤ እነርሱም ከአንተ በብዛትና በኀይል የሚበልጡት ሰባት የአሕዛብ ነገዶች ሒታውያን፥ ጌርጌሳውያን፥ አሞራውያን፥ ከነዓናውያን፥ ፈሪዛውያን፥ ሒዋውያንና ኢያቡሳውያን ተብለው የሚጠሩት ናቸው።
ስለዚህ እግዚአብሔር ለቀድሞ አባቶቻቸው ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል የገባላቸውን ምድር ሁሉ ለእስራኤላውያን ሰጠ። ምድሪቱንም ከወረሱ በኋላ በዚያ ተደላድለው ኖሩ፤
ዛሬ ግን ከመከራችሁና ከጭንቀታችሁ ያዳናችሁን አምላካችሁን ትታችኋል፤ እናንተም፦ ‘አይሆንም ንጉሥ አንግሥልን’ አላችሁት። አላችሁት። ስለዚህ አሁን በየነገዳችሁና በየወገናችሁ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቅረቡ”።
ሳሙኤልም ለሕዝቡ፥ ለአንድ ንጉሥ ሊደረግለት የሚገባውን ሥርዓት አስረዳቸው፤ ያንንም በመጽሐፍ ጽፎ በእግዚአብሔር ፊት አስቀመጠው፤ ከዚያም በኋላ ሕዝቡን ሁሉ ወደየቤቱ አሰናበተ፤
ሳሙኤልንም እንዲህ አሉት፤ “እንዳንሞት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን፤ ሌላውን ኃጢአት ሁሉ ከመሥራት አልፈን ንጉሥ እንዲያነግሥልን በመጠየቃችን በደለኞች መሆናችንን አሁን ተገንዝበናል።”
እንዲህም ሲል ገለጠላቸው፤ “ንጉሣችሁ የሚያደርግባችሁ ነገር ይህ ነው፦ ልጆቻችሁን ወስዶ ሠረገለኞችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ አንዳንዶቹም በሠረገሎቹም ፊት የሚሮጡ ያደርጋቸዋል፤