በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤
ዳንኤል 4:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ውሳኔውም የተላለፈው በቅዱሳን መላእክት ነው፤ ይህም የሆነው ልዑል እግዚአብሔር በምድር መንግሥታት ላይ ሥልጣን ያለው መሆኑን ሁሉም እንዲያውቅ ነው፤ ሥልጣኑንም ለፈቀደለት ሰው ይሰጠዋል፤ የተናቁትንም በሥልጣን ላይ ያስቀምጣቸዋል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ውሳኔው በመልእክተኞች ተገልጿል፤ ፍርዱም በቅዱሳኑ ተነግሯል፤ ይኸውም፣ ልዑል በሰዎች መንግሥታት ሁሉ ላይ እንደሚገዛና እነዚህንም መንግሥታት ለወደደው እንደሚሰጥ፣ ከሰዎችም የተናቁትን በላያቸው እንደሚሾም፣ ሕያዋን ሁሉ ያውቁ ዘንድ ነው።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልዑሉ በሰዎች መንግሥት ላይ እንዲሠለጥን፥ ለወደደውም እንዲሰጠው፥ ከሰውም የተዋረደውን እንዲሾምበት ሕያዋን ያውቁ ዘንድ ይህ ነገር የጠባቂዎች ትእዛዝ፥ ይህም ፍርድ የቅዱሳን ቃል ነው። |
በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር በማድረግ ሁለንተናውን ለኃጢአት አሳልፎ የሸጠ አክዓብን የሚምስል ማንም አልነበረም፤ ይህን ሁሉ ለማድረግ የተገደደው ሚስቱ ኤልዛቤል ወደ ክፋት ስለ መራችው ነው፤
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር “ማንን እልካለሁ? መልእክተኛ የሚሆንልንስ ማን ነው?” ሲል ሰማሁት፤ እኔም “እነሆ እኔ እሄዳለሁ! እኔን ላከኝ!” አልኩ።
በሕዝቦች መካከል እጅግ የከፉትን ወደዚህ አምጥቼ ቤቶቻችሁን እንዲወርሱ አደርጋለሁ፤ የኀያላንን ትዕቢት አጠፋለሁ፤ የተቀደሱ ቦታዎቻችሁንም ያረክሳሉ።
ራእዩን ያብራራልኝ የነበረውም መልአክ እንዲህ አለ፦ “ከእርሱ በኋላ አንድ የተናቀ ሰው ይነሣል፤ የንጉሥነት ክብር ግን አልተሰጠውም፤ ነገር ግን በድንገት መጥቶ በተንኰል የመንግሥቱን ሥልጣን ይይዛል።
እርሱ ጊዜያትንና ወራትን ያፈራርቃል፤ ነገሥታትን ወደ ዙፋን ያወጣል፤ ከዙፋንም ያወርዳል፤ ጥበብን ለጠቢባን፥ ዕውቀትንም ለአስተዋዮች የሚሰጥ እርሱ ነው።
ከሕዝብ መካከል ተለይተህ ትሰደዳለህ፤ ኑሮህም ከዱር አራዊት ጋር ይሆናል፤ ሰባት ዓመት እስኪያልፍ እንደ በሬ ሣር ትበላለህ፤ በሰማይ ጠል ትረሰርሳለህ፤ ይህም ሁሉ የሚደርስብህ ልዑል እግዚአብሔር በመንግሥታት ሁሉ ላይ ሥልጣን እንዳለውና መንግሥትንም ሁሉ ለወደደው ሰው እንደሚሰጥ እስከምትረዳ ድረስ ነው።
በልዑል እግዚአብሔር ላይ በመታበይ ይናገራል፤ የልዑል እግዚአብሔርንም ቅዱሳን ያስጨንቃል፤ የተቀደሱ በዓላትንና ሕጉን ለመለወጥ ያቅዳል፤ ቅዱሳኑም ለሦስት ዓመት ተኩል በእርሱ ሥልጣን ሥር ይሆናሉ።
ማንኛውም ሥልጣን የሚገኘው በእግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ሆነና አሁን ያሉትም ባለሥልጣኖች የተሾሙት በእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ ሰው ሁሉ ለበላይ ባለሥልጣን መታዘዝ አለበት።
እግዚአብሔር በዓለም ሰዎች ዘንድ አሉ ተብለው የሚታዩትን ነገሮች እንደሌሉ ለማድረግ በዓለም የተዋረደና የተናቀ ከንቱም መስሎ የሚታየውን ነገር መረጠ።
በምታደርገው ነገር ሁሉ አንዱን ከሌላው ሳታበላልጥ ወይም ለማንም ሳታዳላ ይህን ምክሬን ሁሉ እንድትፈጽም በእግዚአብሔርና በኢየሱስ ክርስቶስ በተመረጡትም መላእክት ፊት ዐደራ እልሃለሁ።
አራቱም እንስሶች እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች ነበሩአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ ሌሊትና ቀን፦ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ ሁሉን የሚችል ጌታ አምላክ፥ የነበረ፥ ያለና የሚመጣውም” ከማለት አያቋርጡም ነበር።
እርሱ ድኾችን ከትቢያ ምስኪኖችንም ከዐመድ ላይ ያነሣል፤ ወደ ልዑላንም ደረጃ ከፍ ያደርጋቸዋል፤ የክብርም ዙፋን ያወርሳቸዋል የምድርን መሠረቶች የሠራ እግዚአብሔር ነው፤ በእነርሱም ላይ ዓለምን የፈጠረ እርሱ ነው።