ብዙዎች ነጥረውና ጠርተው በመውጣት ነውር የሌለባቸው ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን ምንም ስለማያስተውሉ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ የማስተዋል ችሎታ የሚኖራቸው ጠቢባን ብቻ ናቸው።
ዳንኤል 11:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕዝቡ መካከል ያሉ ጠቢባን ሕዝቡን በማስተማር ዕውቀት እንዲያገኝ ያደርጋሉ፤ ነገር ግን ለጥቂት ጊዜ ለእሳት ቃጠሎና ለሰይፍ ስለት የተጋለጡ ይሆናሉ፤ ሀብታቸውንም ተዘርፈው ይታሰራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለጊዜው በሰይፍ ቢወድቁም፣ ቢቃጠሉም፣ ቢማረኩና ቢዘረፉም፣ ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብዙዎችን ያስተምራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕዝቡም መካከል ያሉ ጥበበኞች ብዙ ሰዎችን ያስተምራሉ፥ ነገር ግን በሰይፍና በእሳት ነበልባል በምርኮና በመበዝበዝ ብዙ ዘመን ይወድቃሉ። |
ብዙዎች ነጥረውና ጠርተው በመውጣት ነውር የሌለባቸው ይሆናሉ፤ ክፉዎች ግን ምንም ስለማያስተውሉ በክፋት ላይ ክፋት እየጨመሩ ይሄዳሉ፤ የማስተዋል ችሎታ የሚኖራቸው ጠቢባን ብቻ ናቸው።
ሰው የገዛ ወንድሙን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ እንዲሁም አባት የገዛ ልጁን ለሞት አሳልፎ ይሰጣል፤ ልጆችም በወላጆቻቸው ላይ በጠላትነት ይነሣሉ፤ ለሞትም አሳልፈው ይሰጡአቸዋል።
ኢየሱስም “በእርግጥ እኔ የምጠጣውን የመከራ ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ ነገር ግን ሰዎችን በቀኜና በግራዬ እንዲቀመጡ የማደርገው እኔ አይደለሁም፤ ይህ ቦታ የሚሰጠው አባቴ ላዘጋጀላቸው ሰዎች ነው።”
ባገኘውም ጊዜ ወደ አንጾኪያ አመጣው፤ ሁለቱም አንድ ዓመት ሙሉ ከቤተ ክርስቲያን ጋር በአንድነት ሆነው ብዙ ሰዎችን አስተማሩ፤ ደቀ መዛሙርትም ለመጀመሪያ ጊዜ በአንጾኪያ “ክርስቲያን” ተብለው ተጠሩ።
ጳውሎስና በርናባስ በደርቤ ወንጌልን አስተምረው ብዙ ሰዎችን አማኞች ካደረጉ በኋላ በልስጥራና በኢቆንዮን አልፈው በጵስድያ ወደምትገኘው አንጾኪያ ሄዱ።
እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት ተፈርዶባቸው ወደሚገደሉበት ቦታ ከሚወሰዱት ሰዎች መካከል የመጨረሻዎቹ ያደረገን ይመስለኛል፤ ከዚህም የተነሣ በዓለም ሁሉ በመላእክትም ሆነ በሰዎች ፊት እንደ ትርኢት ሆነን እንታያለን፤
ይህን መከራ የምቀበለውም በዚህ ምክንያት ነው፤ ነገር ግን ማንን እንዳመንኩ ስለማውቅ አላፍርበትም፤ የተሰጠኝንም ዐደራ እስከዚያ ቀን ድረስ መጠበቅ እንደምችል ተረድቼአለሁ።
የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከደካማነት ወደ ብርቱነት ተለወጡ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የወራሪ ጠላትን ወታደሮች አባረሩ፤
በኢየሱስ ክርስቶስ የመከራውና የመንግሥቱ እንዲሁ የትዕግሥቱ ከእናንተ ጋር ተካፋይ የሆንኩ እኔ ወንድማችሁ ዮሐንስ በእግዚአብሔር ቃልና በኢየሱስ ምስክርነት ምክንያት ታስሬ ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርኩ፤
አንተ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ስፍራ መኖርህን ዐውቃለሁ፤ ይሁን እንጂ ስሜን አጥብቀህ ይዘሃል፤ በእኔ ላይ ያለህን እምነት አልካድክም፤ ታማኝ ምስክሬ የነበረው አንቲጳስ ሰይጣን በሚኖርበት በእናንተ ከተማ በተገደለ ጊዜ እንኳ በእኔ ማመንህን አልተውክም።
እኔም “ጌታ ሆይ፥ አንተ ታውቃለህ” አልኩት። እርሱም እንዲህ አለኝ፤ “እነዚህ ታላቁን መከራ አልፈው የመጡ ናቸው፤ ልብሳቸውንም በበጉ ደም አጥበው ነጭ አድርገውታል፤