Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዕብራውያን 11:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከደካማነት ወደ ብርቱነት ተለወጡ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የወራሪ ጠላትን ወታደሮች አባረሩ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 የእሳትን ኀይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው በረቱ፤ በጦርነት ኀያል ሆኑ፤ ባዕዳን ወታደሮችን አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 የእሳትን ኃይል አጠፉ፤ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፤ ከድካማቸው ብርቱ ሆኑ፤ በጦርነት ኀይለኞች ሆኑ፤ የባዕድ ወራሪዎችን አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 የእ​ሳት ኀይ​ልን አጠፉ፤ ከሰ​ይፍ ስለት አመ​ለጡ፤ ከድ​ካ​ማ​ቸው በረቱ፤ በጦ​ር​ነት ኀይ​ለ​ኞች ሆኑ፤ የባ​ዕድ ጭፍ​ሮ​ች​ንም አባ​ረሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 የአንበሶችን አፍ ዘጉ፥ የእሳትን ኃይል አጠፉ፥ ከሰይፍ ስለት አመለጡ፥ ከድካማቸው በረቱ፥ በጦርነት ኃይለኞች ሆኑ፥ የባዕድ ጭፍሮችን አባረሩ።

Ver Capítulo Copiar




ዕብራውያን 11:34
36 Referencias Cruzadas  

ኤልያስ ያደረገውን ሁሉና የበዓልንም ነቢያት በሙሉ በሞት እንዴት እንደ ቀጣ ንጉሥ አክዓብ ለሚስቱ ለኤልዛቤል ነገራት፤


ኤልያስም ስለ ፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ከአገልጋዩ ጋር በይሁዳ ወደምትገኘው ወደ ቤርሳቤህ ከተማ ሄደ። አገልጋዩንም በዚያ ተወው፤


በኤልሳዕ ኀላፊነት ሥር የነበሩት የነቢያት ጉባኤ አባላት፥ “የምንኖርበት ስፍራ ጠባብ ነው፤


ወዲያውኑም ኤልሳዕን ይዞ የሚመጣ መልእክተኛ ላከ። በዚህም ጊዜ ኤልሳዕ ሊጐበኙት ከመጡ ጥቂት ሽማግሌዎች ጋር በቤት ውስጥ ነበር፤ የንጉሡ መልእክተኛ ከመድረሱም በፊት ኤልሳዕ ሽማግሌዎቹን “ያ ነፍሰ ገዳይ እኔን ለማስገደል አንድ ሰው ልኮአል! እነሆ፥ እርሱ እዚህ በሚደርስበት ጊዜ በሩን ዝጉ፤ ወደ ውስጥም እንዲገባ አትፍቀዱለት፤ ንጉሡም እርሱን ተከትሎ መጥቶ በኋላው ይገኛል” አላቸው።


ኢዮብ ለሦስቱ ወዳጆቹ ከጸለየ በኋላ እግዚአብሔር እንደገና እንዲበለጽግ አደረገው፤ ዱሮ ከነበረውም ይበልጥ እጥፍ አድርጎ ሰጠው።


በራብ ዘመን በሕይወት ያኖርሃል። በጦርነትም ጊዜ ከሞት ያድንሃል።


እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አምልጠናል፤ ወጥመዱ ተሰበረ፤ እኛም ነጻ ወጣን።


አንተ ለነገሥታት ድልን ታጐናጽፋለህ፤ አገልጋይህን ዳዊትንም ከስለታም ሰይፍ ትታደገዋለህ።


እግዚአብሔር የለቅሶዬን ጩኸት ሰምቶአል፤ ስለዚህ እናንተ ክፉ አድራጊዎች ከእኔ ወዲያ ራቁ!


ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጐርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን ብልጽግና ወደ መላበት ወደ ሰፊ ቦታ አመጣኸን።


እንዲሁም “የአባቴ አምላክ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ በግብጽ ንጉሥም እጅ እንዳልገደል አዳነኝ” በማለት ሁለተኛውን ልጁን ኤሊዔዘር ብሎ ሰይሞት ነበር።


በውሃ ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፤ በወንዞች መካከል በምታልፉበት ጊዜ አያሰጥሙአችሁም፤ በእሳትም ውስጥ በምታልፉበት ጊዜ አያቃጥላችሁም፤ ነበልባሉም ዐመድ አያደርጋችሁም።


እኔ ግን የሳፋን ልጅ አሒቃም ይከላከልልኝ ስለ ነበር ይገድሉኝ ዘንድ ለሕዝቡ ተላልፌ አልተሰጠሁም።


ከእነርሱም ብዙዎች በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሌሎችም ተማርከው ወደየአገሩ ይወሰዳሉ። የአሕዛብ ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።”


ወዳጆች ሆይ! እንደ እሳት በሚፈትን መከራ ውስጥ ስትገኙ ያልተለመደ እንግዳ ነገር እንደ ደረሰባችሁ አድርጋችሁ አትደነቁ፤


ወዲያውም ብርቱ አደጋ ጥሎባቸው ከእነርሱ ብዙዎችን ገደለ፤ ከዚህም በኋላ ሄዶ ዔጣም ተብላ በምትጠራ ስፍራ በዋሻ ውስጥ ተቀመጠ።


“መትቼ ከግድግዳ ጋር አጣብቀዋለሁ!” ብሎ በልቡ አሰበ፤ ከዚህም በኋላ ጦሩን በዳዊት ላይ ሁለት ጊዜ ወረወረ፤ ዳዊት ግን ሁለቴም ዞር እያለ አመለጠ።


ሳኦል ዳዊትን ወግቶ ከግድግዳው ጋር ሊያጣብቀው በማሰብ ጦሩን ወረወረበት፤ ዳዊት ግን ዞር በማለቱ ጦሩ በግድግዳ ላይ ተተከለ፤ ዳዊትም ከዚያ ሸሽቶ አመለጠ።


ከዚህ በኋላ ዳዊት በራማ ከምትገኘው ከናዮት በመሸሽ ወደ ዮናታን ሄዶ “ከቶ ምን አደረግሁ? ምንስ ወንጀል ፈጸምኩ? አባትህ ለመግደል የሚፈልገኝስ ምን በድየው ነው?” ሲል ጠየቀው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos