አሞጽ 8:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በእኩለ ቀን ፀሐይ እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ በቀትርም ምድሪቱን አጨልማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን፣ ፀሓይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ ምድርንም ደማቅ ብርሃን ሳለ በቀን አጨልማታለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚያም ቀን፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ “ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ቀኑም በብርሃን ሳለ ምድሩን አጨልማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር ይገባል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ብርሃንም በምድር ላይ በቀን ይጨልማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለሁ። |
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ሰባት ልጆችዋን ያጣችው እናት፥ በታላቅ ተስፋ መቊረጥ ከእስትንፋስዋ ጋር እየታገለች ነው፤ የቀኑ ብርሃን ወደ ጨለማ ተለውጦባታል፤ ውርደትና ኀፍረት ደርሰውባታል፤ ገና በሕይወት ያላችሁትንም ጠላቶቻችሁ እንዲገድሉአችሁ አደርጋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ተራራዎችን የሠራ፥ ነፋሶችን የፈጠረ፥ ያሰበውን ነገር ለሰው የሚገልጥ፥ የቀኑን ብርሃን ወደ ጨለማ የሚለውጥ፥ በምድር ከፍታዎች ላይ የሚራመድ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ነው።
“ፕሊያዲስ” የተባሉትን ሰባቱን ከዋክብትና “ኦርዮን” ተብለው የሚጠሩትን የከዋክብት ክምችትን የፈጠረ፥ ሌሊቱን ወደ ቀን፥ ቀኑንም ወደ ሌሊት የሚለውጥ፥ የባሕሩን ውሃ አዞ፥ በምድር ላይ እንዲፈስ የሚያደርግ፥ ኀያላንንና ምሽጎቻቸውን የሚደመስስ እርሱ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
ከዚህ በኋላ በጉ ስድስተኛውን ማኅተም በከፈተ ጊዜ ወደ እርሱ ተመለከትኩ፤ እነሆ ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይ እንደ ጥቊር የሐዘን ልብስ ጠቈረች፤ ጨረቃም በሙሉ እንደ ደም ቀላች፤
አራተኛው መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ አንድ ሦስተኛ፥ የጨረቃ አንድ ሦስተኛ፥ የኮከቦች አንድ ሦስተኛ ተመታ፤ ስለዚህ የእነርሱ አንድ ሦስተኛቸው ጨለመ፤ በዚህ ዐይነት የቀን አንድ ሦስተኛና የሌሊት አንድ ሦስተኛ ያለ ብርሃን ሆነ።