እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤
አሞጽ 8:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “አሞጽ ሆይ፤ ምን ታያለህ?” አለኝ። እኔም፣ “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልሁ። ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “በሕዝቤ በእስራኤል ላይ ፍጻሜ መጥቷል፤ ከእንግዲህም አልምራቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፦ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድነው?” አለኝ። እኔም፦ “የበጋ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት ነው” አልኩት። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቷል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ዳግመኛ አላልፋቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “አሞጽ ሆይ! የምታየው ምንድን ነው?” አለኝ። እኔም፥ “የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው” አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፥ “ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ ይቅር አልላቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አሞጽ ሆይ፥ የምታየው ምንድር ነው? አለኝ። እኔም፦ የቃርሚያ ፍሬ የሞላበት ዕንቅብ ነው አልሁት። እግዚአብሔርም አለኝ፦ ፍጻሜ በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መጥቶአል፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደግሞ አላልፋቸውም። |
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፦ “የሰውን ዘር ለማጥፋት ወስኛለሁ፤ ምድር በሰዎች የዐመፅ ሥራ ስለ ተሞላች ሰዎችን ከምድር ጋር አጠፋቸዋለሁ፤
ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ያለችው ሰማርያ በፍጥነት ክብርዋን ታጣለች፤ እርስዋም እንደሚረግፍ አበባና በበለስ ወራት መጀመሪያ በስለው በመገኘታቸው ተለቅመው እንደሚበሉ የበለስ ፍሬዎች ትሆናለች።
እኔም በዚህቹ በምጽጳ ከእናንተ ጋር ስለምኖር ባቢሎናውያን በሚመጡበት ጊዜ የእናንተ ወኪል ሆኜ እቆምላችኋለሁ፤ እናንተ ግን በምትኖሩባቸው መንደሮች ሁሉ የወይኑን ዘለላ፥ የወይራውን ዘይትና የሌላውን ተክል ፍሬ ሰብስባችሁ አከማቹ”
ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”
እኔ ልዑል እግዚአብሔር ስለዚህ ጉዳይ የምለውን ንገራቸው፤ ይህ ምሳሌ እዚሁ ላይ እንዲያበቃ አደርገዋለሁ፤ ዳግመኛም በእስራኤል አይነገርም፤ በዚህ ፈንታ ‘እነሆ ጊዜው ደርሶአል፤ የትንቢቱም ቃል ሁሉ ሊፈጸም ነው!’ ብለህ ንገራቸው።
እንግዲህ እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምነግርህ ይህ ነው፥ ‘በሰይፍ አደጋ የሚጥሉብህን ሰዎች አመጣለሁ፤ እነርሱ ሕዝብህንና እንስሶችህን ሁሉ ይፈጃሉ፤
እርሱም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል መሪዎች በየራሳቸው ጣዖት ቤት በጨለማ ሆነው እግዚአብሔር አያየንም! ምድሪቱንም ትቶአታል በማለት የሚያደርጉትን ታያለህን?” አለኝ።
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! ይህን ታያለህን? እነዚህ የይሁዳ ሕዝቦች በዚህ ስፍራ ያየኸውን አጸያፊ ነገር ሁሉ በመሥራትና በአገሪቱም ላይ ዐመፅ ማስፋፋቱ አልበቃ ብሎአቸው ወደዚህ ወደ ቤተ መቅደስ እንኳ ሳይቀር በቀጥታ መጥተው ይህን ሁሉ በማድረግ እኔን እንደገና ማስቈጣት ይፈልጋሉ፤ እንዴት እንደሚሰድቡኝና እኔን ለማስቈጣት የተቻላቸውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ተመልከት!
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሆነውን ነገር ሁሉ ታያለህን? የእስራኤል ሕዝብ በዚህ ስፍራ የሚፈጽሙትን አጸያፊ ነገር ተመልከት፤ በዚህ አድራጎታቸው ከተቀደሰው ስፍራዬ እንድርቅ አድርገውኛል፤ ከዚህም የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና ታያለህ።”
የቅጣት ቀን ደርሶአል፤ እስራኤላውያንም የበቀል ቀን መቃረቡን ይወቁ፤ በእናንተ በደልና ጥላቻ ምክንያት ነቢይን እንደ ሞኝ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያደረበትን ሰው እንደ ዕብድ ትቈጥሩታላችሁ።
እርሱም “አሞጽ ሆይ! የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ብሎ ጠየቀኝ። እኔም “ቱምቢ ነው” አልኩ። ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “በቱምቢ ተስተካክሎ እንዳልተሠራ ቅጽር ሕዝቤ እስራኤል ጠማሞች ሆነው ስለ ተገኙ ይህ ቱምቢ የእስራኤልን ጠማማነት ማሳያ ምሳሌ ነው፤ ሳልቀጣቸውም አላልፍም።
የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።
መልአኩም “ምን ታያለህ?” ብሎ ጠየቀኝ፤ እኔም “ርዝመቱ ዐሥር ሜትር፤ ስፋቱም አምስት ሜትር የሆነ፥ አንድ የተጠቀለለ የብራና መጽሐፍ በአየር ላይ ሲበር አያለሁ” አልኩት።