Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሰቈቃወ 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ጠላትም በየመንገዱ መዘዋወር እንዳንችል በዐይነ ቊራኛ ይጠባበቀን ነበር፤ ዘመናችን ቀርቦአል፤ ዘመናችን አልቆአል፤ ፍጻሜውም ደርሶአል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ሰዎች እግር እግራችንን ተከታተሉን፤ ስለዚህ በመንገዳችን መሄድ አልቻልንም፤ መጨረሻችን ቀርቧል፤ ቀኖቻችንም ተቈጥረዋል፤ ፍጻሜያችን መጥቷልና።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጻዴ። በአደባባያችን እንዳንሄድ ፍለጋችንን ተከተሉ፥ ፍጻሜያችን ቀርቦአል፥ ዕድሜያችን አልቆአል፥ ፍጻሜያችን ደርሶአል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ጻዴ። ልጆ​ቻ​ች​ንን ወደ አደ​ባ​ባ​ያ​ችን እን​ዳ​ይ​ወጡ ከለ​ከ​ልን፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በት ጊዜ ደር​ሷ​ልና ዘመ​ና​ችን አለቀ፤ የም​ን​ጠ​ፋ​በ​ትም ጊዜ ቀረበ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ጻዴ። በአደባባያችን እንዳንሄድ ፍለጋችንን ተከተሉ፥ ፍጻሜያችን ቀርቦአል፥ ዕድሜያችን አልቆአል፥ ፍጻሜያችን ደርሶአል።

Ver Capítulo Copiar




ሰቈቃወ 4:18
16 Referencias Cruzadas  

ትዕቢት ቢሰማኝ እንደ አንበሳ አድነህ ትይዘኛለህ፤ እኔንም ለመጒዳት መላልሰህ ታደርጋለህ።


ሌሎችን በሐሰት የሚከስሱ በምድር ላይ ጸንተው አይኑሩ፤ ክፉ ነገር በጨካኞች ሰዎች ላይ ይድረስ፤ ይደምስሳቸውም።


እግዚአብሔርም “በትክክል አይተሃል፤ እኔም እንዲሁ ቃሌ እንዴት ተግባራዊ እንደሚሆን አተኵሬ እመለከታለሁ” አለኝ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ይህን ሕዝብ እንደ ዓሣ የሚያጠምዱና እንደ አውሬ የሚያድኑ ብዙ ሰዎችን እልካለሁ፤ በየተራራውና በየኰረብታው በቋጥኞች ውስጥ ባሉ ዋሻዎችም እያደኑ ይይዙአቸዋል።


ነገር ግን ከብንያም ቅጽር በር እንደ ደረስኩ የዘብ ጠባቂዎች አለቃ የሆነው ስሙ ዪሪያ ተብሎ የሚጠራ የሐናንያ የልጅ ልጅ የሆነው የሼሌምያ ልጅ “ከድተህ ወደ ባቢሎናውያን ልትሄድ ነው!” ብሎ አስቆመኝ።


ነቢያት ነን የሚሉት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፤ ካህናቱ በነቢያት ምክር ያስተዳድራሉ፤ ሕዝቡም ይህን ሁሉ አይቃወሙም፤ ታዲያ የዚህ ሁሉ ፍጻሜ በሚደርስበት ጊዜ ምን ይበጃችሁ ይሆን?”


ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”


“ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ጠላቶቼ እንደ ወፍ አጠመዱኝ።


“የሰው ልጅ ሆይ! እስራኤላውያን የአንተ ራእይና ትንቢት ‘ከብዙ ዘመን በኋላ የሚፈጸም ነው’ ብለው ይናገራሉ፤


እግዚአብሔርም “ይህ የምታየው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀኝ። እኔም “የጐመራ ፍሬ የሞላበት ቅርጫት አያለሁ” አልኩት። እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ “የሕዝቤ የእስራኤል ፍጻሜ ደርሶአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ እነርሱን ከመቅጣት አልመለስም።


እነሆ፥ የእስራኤል ንጉሥ ማንን ለመግደል እንደሚጥር ተመልከት! ማንንም እንደሚያሳድድ አስተውል! የሞተ ውሻን ወይስ ቁንጫን? ማንን እንደሚያሳድድ ተመልከት!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos