Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 28:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ያለችው ሰማርያ በፍጥነት ክብርዋን ታጣለች፤ እርስዋም እንደሚረግፍ አበባና በበለስ ወራት መጀመሪያ በስለው በመገኘታቸው ተለቅመው እንደሚበሉ የበለስ ፍሬዎች ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በረ​ዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረ​ገ​ፈች የክ​ብሩ ተስፋ አበባ አስ​ቀ​ድማ እን​ደ​ም​ት​በ​ስል በለስ ትሆ​ና​ለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይ​ቀ​በ​ላት ይበ​ላት ዘንድ ይፈ​ጥ​ናል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 28:4
12 Referencias Cruzadas  

ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ላለችው የሰማርያ ከተማ ወዮላት! መሪዎችዋ በመጠጥ የተሞሉ ሰካራሞች ናቸው ነገር ግን እነርሱ ደርቆ እንደሚረግፍ አበባ ይሆናሉ።


ልጁም ገና ‘አባባና እማማ’ ብሎ ለመጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ተመዝብሮ ይወሰዳል።”


የኤፍሬም ነገድ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ከፍ ብሎ በነበረበት ዘመን ሲናገር የሚሰሙት ሁሉ ይንቀጠቀጡ ነበር፤ በኋላ ግን ባዓል ለተባለ ጣዖት በመስገድ ኃጢአት ስለ ሠራ በሞት ተቀጣ።


በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም የእግዚአብሔር ቅጣት የሆነው የምሥራቁ ነፋስ ከምድረ በዳ ተነሥቶ ይመጣል፤ ምንጩ ይቆማል፤ ወንዙም ይደርቃል። ነፋሱም የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ገፎ ይወስድበታል።


እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልና የይሁዳ ሕዝብ ሆይ! እናንተን ምን ላድርጋችሁ? እናንተ ለእኔ ያላችሁ ፍቅር እንደ ማለዳ ጉምና እንደ ጠዋት ጤዛ ፈጥኖ ይጠፋል።


የእስራኤል ሕዝብ ነፋስ እንደ መታው፥ ሥሩ እንደ ደረቀና ማፍራት እንደማይችል ዛፍ ያለ ፍሬ ይቀራሉ፤ ልጆች ቢወልዱም እጅግ የሚወዱአቸውን ልጆቻቸውን እገድላለሁ።”


የመከር ፍሬ ተሰብስቦ የወይኑም ቃርሚያ ከተቃረመ በኋላ ሊበላ የሚፈልገውን የወይን ዘለላ እንደማያገኝ ሰው ስለ ሆንኩ ወዮልኝ! እኔ የምመኘውም አስቀድሞ የደረሰው የበለስ ፍሬ የለም።


ምሽግሽ ሁሉ ቀድሞ የደረሰ ፍሬ እንደ ተሸከመ የበለስ ዛፍ ይሆናል፤ እርሱ ተነቅንቆ ፍሬው በተራገፈ ጊዜ በበላተኛ አፍ ውስጥ ይወድቃል።


በክረምት ወራት ብርቱ ነፋስ የበለስን ዛፍ ሲያወዛውዝ ፍሬው ከዛፉ ላይ እንደሚረግፍ የሰማይ ኮከቦችም ረገፉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos