Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ኢሳይያስ 28:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በረ​ዥም ተራራ ራስ ላይ ያለች የረ​ገ​ፈች የክ​ብሩ ተስፋ አበባ አስ​ቀ​ድማ እን​ደ​ም​ት​በ​ስል በለስ ትሆ​ና​ለች፤ ሰውም ባያት ጊዜ በእጁ ሳይ​ቀ​በ​ላት ይበ​ላት ዘንድ ይፈ​ጥ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 በለምለሙ ሸለቆ ዐናት ላይ ጕብ ብላ፣ የክብሩ ውበት የሆነች ጠውላጋ አበባ፣ ከመከር በፊት እንደ ደረሰች፣ ሰውም ድንገት አይቶ እንደሚቀጥፋት ወዲያውኑም እንደሚውጣት በለስ ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 በለምለሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ያያት ሁሉ እጁን ሰዶ ይበላታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ያለችው ሰማርያ በፍጥነት ክብርዋን ታጣለች፤ እርስዋም እንደሚረግፍ አበባና በበለስ ወራት መጀመሪያ በስለው በመገኘታቸው ተለቅመው እንደሚበሉ የበለስ ፍሬዎች ትሆናለች።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 28:4
12 Referencias Cruzadas  

ለኤ​ፍ​ሬም ምን​ደ​ኞች ትዕ​ቢት አክ​ሊል፥ ያለ ወይን ጠጅ ለሰ​ከሩ፥ በወ​ፍ​ራም ተራራ ራስ ላይ ላለ​ችም ለረ​ገ​ፈች ለክ​ብር ጌጥ አበባ ወዮ!


ሕፃኑ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን መጥ​ራት ሳያ​ውቅ የደ​ማ​ስ​ቆን ሀብ​ትና የሰ​ማ​ር​ያን ምርኮ በአ​ሦር ንጉሥ ፊት ይወ​ስ​ዳ​ልና።”


ኤፍ​ሬም እንደ ተና​ገረ በእ​ስ​ራ​ኤል ሥር​ዐ​ቱን ወሰደ፤ ለበ​ዓ​ልም አደ​ረ​ገው፤ ሞተም።


ከወ​ን​ድ​ሞቹ መካ​ከል ይለ​ያል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ድረ በዳ የሚ​ያ​ቃ​ጥል ነፋ​ስን ያመ​ጣል፤ ሥሩን ያደ​ር​ቃል፤ ምን​ጩ​ንም ያነ​ጥ​ፋል፤ ምድ​ርን ያደ​ር​ቃል፤ የተ​ወ​ደዱ ዕቃ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ያጠ​ፋል።


“ምሕ​ረ​ታ​ችሁ እንደ ማለዳ ደመና፥ በማ​ለ​ዳም እን​ደ​ሚ​ያ​ልፍ ጠል ነውና ኤፍ​ሬም ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ? ይሁዳ ሆይ! ምን ላድ​ር​ግ​ልህ?


ኤፍ​ሬም ታመመ፤ ሥሩም ደረቀ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ፍሬ አያ​ፈ​ራም፤ ደግ​ሞም ቢወ​ልዱ የተ​ወ​ደ​ደ​ውን የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ እገ​ድ​ላ​ለሁ።


የዛፍ ፍሬና የወይን ፍሬ ከተለቀሙ በኋላ እንደ ቀረው ቃርሚያ ሆኛለሁና ወዮልኝ! መብል የሚሆን ዘለላ፥ ነፍሴም የተመኘችው በመጀመሪያ የበሰለው በለስ የለም።


አምባሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፣ ቢወዛወዝ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃል።


በለስም በብርቱ ነፋስ ተናውጣ ቃርያዋን ፍሬ እንደምትጥል የሰማይ ከዋክብት ወደ ምድር ወደቁ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos