ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ስንዴ በአውድማ ላይ እንደሚወቃ እናንተም ተወቅታችሁ ነበር፤ አሁን ግን የሠራዊት ጌታ፥ የእስራኤል አምላክ፥ የሰማሁትን የምሥራች ቃል ገለጥሁላችሁ።
አሞጽ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንበሳ ሲያገሣ ሰምቶ የማይፈራ ማን አለ? ጌታ እግዚአብሔር ምሥጢሩን ሲገልጥለት ትንቢት የማይናገር ማን አለ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንበሳ አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንበሳው አገሣ፥ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፥ ትንቢት የማይናገር ማን ነው? |
ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ስንዴ በአውድማ ላይ እንደሚወቃ እናንተም ተወቅታችሁ ነበር፤ አሁን ግን የሠራዊት ጌታ፥ የእስራኤል አምላክ፥ የሰማሁትን የምሥራች ቃል ገለጥሁላችሁ።
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “አንበሳ በገደለው እንስሳ ላይ በሚያገሣበት ጊዜ እረኞች ተጠራርተው የቱንም ያኽል ቢጮኹ የእነርሱ ጩኸት ምንም እንደማያስፈራው እኔም የሠራዊት አምላክ የጽዮንን ተራራና ኰረብቶቿን ለመከላከል የሚያግደኝ የለም።
ነገር ግን “ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አላስታውስም፤ በስሙም አልናገርም” በምልበት ጊዜ፥ ከእርሱ የተሰጠኝ የትንቢት ቃል በውስጤ እንደ እሳት ይነዳል፤ በውስጤ ሰውሬ ልይዘው ብሞክርም፤ አፍኜ ላስቀረው አይቻለኝም።
እኔም ኤርምያስ ለመሪዎቹና ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አልኩ፦ “በዚህች ከተማና በዚህ ቤተ መቅደስ ላይ ይህን እናንተ የሰማችሁትን ቃል እንዳውጅ የላከኝ እግዚአብሔር ነው።
“ይህ በሚሆንበት ጊዜ የእስራኤልን ሕዝብ አበረታለሁ፤ አንተም ሕዝቅኤል ሆይ! ሰዎች ሊያደምጡህ በሚችሉበት ቦታ ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ እንድትናገር አደርግሃለሁ፤ በዚህም ሁኔታ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።”
አሞጽ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ ሆኖ እንደሚያገሣ አንበሳ የሚያስፈራ ድምፁን ያሰማል፤ ቃሉም ከኢየሩሳሌም ያስተጋባል፤ እረኞች መንጋ የሚያሰማሩበት መስክ ይጠወልጋል፤ በቀርሜሎስ ተራራ የሚገኘውም ልምላሜ ይደርቃል።”
አንበሳ በደን ውስጥ ዐድኖ የሚበላውን ሳያገኝ በከንቱ ያገሣልን? የአንበሳ ደቦልስ አንዳች ነገር ዐድኖ ሳይዝ በሚኖርበት ቦታ ድምፁን ያሰማልን?
በዚያን ጊዜ ከሽማግሌዎቹ አንዱ “አታልቅስ፤ እነሆ ከይሁዳ ነገድ የሆነው ከዳዊት የትውልድ ሐረግ የተነሣ አንበሳ ድል ነሥቶአል፤ እርሱ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍና ሰባቱን ማኅተሞች መክፈት ይችላል” አለኝ።