በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤላውያን ድል መመታታቸውን በተገነዘቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእስራኤላውያን ተገዢዎች ሆኑ፤ ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።
2 ሳሙኤል 8:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ በግዛታቸው ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያንም ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ገበሩለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን እንዲቀዳጅ አደረገው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም የደማስቆ ክፍል በሆነው የሶርያውያን ግዛት የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ። ሶርያውያን ተገዙለት፤ ገበሩለትም። ጌታም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፤ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ ግብርም አመጡለት፤ እግዚአብሔርም ዳዊትን በሄደበት ሁሉ ጠበቀው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በደማስቆ ሶርያ ጭፍሮች አኖረ፥ ሶርያውያንም ለዳዊት ገባሮች ሆኑ፥ ግብርም አመጡለት፥ እግዚአብሔርም ዳዊት በሄደበት ሁሉ ድልን ሰጠው። |
በሀዳድዔዜር ሥልጣን ሥር የነበሩት ነገሥታት በእስራኤላውያን ድል መመታታቸውን በተገነዘቡ ጊዜ ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው የእስራኤላውያን ተገዢዎች ሆኑ፤ ከዚያም በኋላ ሶርያውያን ዳግመኛ ዐሞናውያንን ለመርዳት ፈሩ።
እነሆ፥ አሁን አድርጉ፤ ደግሞም እግዚአብሔር ‘በአገልጋዬ በዳዊት አማካይነት ሕዝቤን እስራኤልን ከፍልስጥኤማውያንና ከሌሎቹም ጠላቶቻቸው እጅ በመታደግ አድናለሁ’ ሲል ተናግሮ እንደ ነበር አስታውሱ።”
በሄድክበት ስፍራ ሁሉ እኔ ከአንተ ጋር ነበርኩ፤ ወደፊትም በተራመድህ መጠን ጠላቶችህን ድል አደረግሁልህ፤ ገና ደግሞ በዓለም እንደ ታወቁት ታላላቅ መሪዎች ዝነኛ አደርግሃለሁ።
በመላው ኤዶም ብዙ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የእርሱ ተገዢዎች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሄደበት ስፍራ ሁሉ ድልን ሰጠው።
ቀጥሎም ንጉሥ ዳዊት ሞአባውያንን ድል አደረገ፤ እስረኞቹ በመሬት ላይ እንዲጋደሙ አድርጎ ከየሦስቱ ሰዎች ሁለት ሁለቱ በሞት እንዲቀጡ አደረገ። ስለዚህም ሞአባውያን የእርሱ ተገዢዎች በመሆን ይገብሩለት ነበር።
የሰሎሞንም ግዛት ከኤፍራጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ፍልስጥኤም ግዛት፥ ከዚያም አልፎ እስከ ግብጽ ወሰን ያለውን አገር ሁሉ ያጠቃልል ነበር፤ የእነዚህም አገሮች ሕዝቦች በጠቅላላ ሰሎሞን በነበረበት ዘመን ሁሉ ለእርሱ ተገዢዎች ሆነው ይገብሩለት ነበር።
ዳግማዊ ኢዮርብዓም ያደረገው ሌላው ነገር ሁሉ፥ በጦርነት ላይ ያሳየው ጀግንነት፥ እንዲሁም የይሁዳ ግዛት የነበሩት ደማስቆና ሐማት ለእስራኤል እንዲመለሱ ያደረገበት ታሪካዊ ዝክረ ነገር ሁሉ በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጽሐፍ ተመዝግቦ ይገኛል።
ስለዚህም እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ሆኖ ስለሚረዳው የሚሠራው ሁሉ በተቃና ሁኔታ ይከናወንለት ነበር፤ ሕዝቅያስ በአሦር ንጉሠ ነገሥት ላይ ዐምፆ ለእርሱ መገዛትን አሻፈረኝ አለ።
በመላው የኤዶም ግዛት ውስጥ የጦር ሰፈሮችን አቋቋመ፤ በዚያም የሚኖሩ ሰዎች የንጉሥ ዳዊት ገባሮች ሆኑ፤ እግዚአብሔር ዳዊትን በሁሉ ስፍራ ድል አድራጊ አደረገው።
በተመሸጉት የይሁዳ ከተሞችና በየገጠሩ ሁሉ እንዲሁም አባቱ ንጉሥ አሳ ድል አድርጎ በያዛቸው በኤፍሬም ግዛት ባሉት ከተሞች ሁሉ ወታደሮቹን አሰፈረ፤
ዮናታን ጌባዕ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ በፍልስጥኤማውያን ላይ አደጋ ጣለ፤ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ይህን ወሬ ሰሙ፤ ሳኦልም መልእክተኞችን ልኮ በሀገሩ ሁሉ እምቢልታ በማስነፋት ዕብራውያን ለጦርነት ጠራ።
አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን የጦር መሣሪያ የሚሸከምለትን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን “ወደ ፍልስጥኤማውያን የጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ነገር ግን ዮናታን ይህን ጉዳይ ለአባቱ እንኳ አልነገረውም፤
በገጠር የነበሩ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ተሸበሩ፤ አደጋ ጣዮችና በሰፈር የነበሩ ወታደሮችም ሁሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እግዚአብሔር በላከባቸውም አስጨናቂ ሽብር መሬት ተንቀጠቀጠች።
ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።