2 ሳሙኤል 23:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት በዚያን ጊዜ በተመሸገ ኮረብታ ላይ ነበር፤ ከፍልስጥኤማውያን ሠራዊት አንድ ቡድን ቤተልሔምን በመውረር ያዘ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሰራዊት በቤተ ልሔም ነበረ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያ ጊዜ ዳዊት በምሽግ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ሠራዊት በቤተልሔም ነበረ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያ ጊዜም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፤ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያ ጊዜም ዳዊት በምሽጉ ውስጥ ነበረ፥ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በዚያ ጊዜ በቤተ ልሔም ነበረ። |
ዳዊት በእስራኤል ላይ መንገሡን ፍልስጥኤማውያን ሰሙ፤ ስለዚህም ሠራዊታቸው ዳዊትን ለመማረክ ገሥግሦ ሄደ፤ ዳዊት የእነርሱን መምጣት በሰማ ጊዜ ወደ ተመሸገ ስፍራ ወረደ፤
ከዚያም አልፈህ የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር ወደሚገኝበት ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ እግዚአብሔር ኮረብታ ትመጣለህ፤ ወደ ከተማይቱም መግቢያ በር በምትደርስበትም ጊዜ በኮረብታው ላይ መሥዋዕት አቅርበው የሚመለሱ የነቢያትን ጉባኤ ታገኛለህ፤ እነርሱም በገና እየደረደሩ፥ ከበሮ እየመቱ፥ ዋሽንት እየነፉ፥ በመሰንቆ ዜማ ሲዘምሩና ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ትንቢት ሲናገሩ ታገኛቸዋለህ።
ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ድል እንዳደረገ እስራኤላውያን ሰሙ፤ እስራኤላውያንም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የተጠሉ መሆናቸውን ዐወቁ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ከሳኦል ጋር የሚሰለፉ መሆናቸውን ለመግለጥ በጌልገላ ተሰበሰቡ።
ዮናታን ጋሻ ጃግሬ የሆነውን ወጣት “ና ወደ እነዚያ ወደ አልተገረዙት ወገኖች የጦር ሰፈር እንሻገር እግዚአብሔር ይረዳን ይሆናል፤ በብዙም ሆነ በጥቂት እግዚአብሔር ማዳን አይሳነውም” አለው።
ዳዊት ከጋት ከተማ ሸሽቶ በዐዱላም ከተማ አጠገብ ወደሚገኝው ወደ አንድ ዋሻ ሄደ፤ ወንድሞቹና ሌሎቹም ቤተሰቦቹ ይህን በሰሙ ጊዜ ወደዚያ ሄደው ከእርሱ ጋር ተቀላቀሉ፤