ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
2 ሳሙኤል 21:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት እነዚህን ሁሉ ለገባዖን ሰዎች አሳልፎ ሰጠ፤ እነርሱም በእግዚአብሔር ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፤ ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ እነርሱም የተገደሉት በጸደይ ወራት ማለቂያና በገብስ መከር መጀመሪያ ላይ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በእግዚአብሔር ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ የተገደሉትም በመከሩ ወራት የመጀመሪያ ቀኖች፣ የገብስ ዐጨዳ በተጀመረበት ዕለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ለገባዖናውያን አሳልፎ ሰጣቸው፤ እነርሱም ገድለው በኰረብታው ላይ በጌታ ፊት ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ሞቱ፤ የተገደሉትም እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፤ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሏቸው። ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፤ እህል በሚታጨድበትም ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለገባዖንም ሰዎች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት በተራራው ላይ ሰቀሉአቸው፥ ሰባቱም በአንድነት ወደቁ፥ እህል በሚታጨድበት ወራት በገብሱ መከር መጀመሪያ ተገደሉ። |
ስለዚህ ከሳኦል ዘሮች ሰባት ወንዶችን ለእኛ አሳልፈህ ስጠን፤ እኛም እነርሱን እግዚአብሔር መርጦ ባነገሠው በንጉሥ ሳኦል ከተማ በጊብዓ በእግዚአብሔር ፊት እንሰቅላቸዋለን” ሲሉ መለሱ። ንጉሥ ዳዊትም “እነርሱን አሳልፌ እሰጣችኋለሁ” አላቸው።
ታቦቱንም አምጥተው ዳዊት ባዘጋጀለት ድንኳን ውስጥ በተመደበለት ስፍራ አኖሩት፤ ከዚህም በኋላ ዳዊት የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነት መሥዋዕት ሁሉ ለእግዚአብሔር አቀረበ።
ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “በእስራኤል ላይ የነደደው ቊጣዬ ይበርድ ዘንድ የእስራኤልን መሪዎች ሁሉ ወስደህ በጠራራ ፀሐይ በሕዝብ ፊት ግደላቸው።”
እንግዲህ ናዖሚ ከሞአባዊት ምራትዋ ከሩት ጋር ከሞአብ አገር የተመለሰችው በዚህ ሁኔታ ነበር፤ እነርሱ ቤተልሔም በደረሱ ጊዜ የገብስ መከር የሚሰበሰብበት ወቅት መጀመሩ ነበር።
በዚህም ጊዜ ሳሙኤል “የአንተ ሰይፍ ብዙዎች እናቶችን ልጅ አልባ እንዳደረገቻቸው፥ የአንተም እናት ልጅ አልባ ሆና ትቀራለች” አለው። ከዚህም በኋላ በጌልገላ በሚገኘው በእግዚአብሔር መሠዊያ ፊት አጋግን ቈራርጦ ጣለው።