Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 6:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ዳዊትም እንዲህ ሲል መለሰላት፦ “እኔ ያሸበሸብኩት የሕዝቡ የእስራኤል መሪ ያደርገኝ ዘንድ በአባትሽና በቤተሰቡ ፈንታ ለመረጠኝ እግዚአብሔር ክብር ነው፤ አሁንም ቢሆን እርሱን ለማክበር ከመጨፈር አልገታም፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ከአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በእግዚአብሔር ፊት አሸብሽቤአለሁ፤ አሁንም አሸበሽባለሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ዳዊትም ሜልኮልን እንዲህ አላት፤ “አዎን ያሸበሸብኩት በጌታ ፊት ነው፤ በአባትሽና በቤቱ ካሉት ሁሉ አስበልጦ በጌታ ሕዝብ በእስራኤል ላይ ገዥ አድርጎ በመረጠኝ በጌታ ፊት አሁንም እጨፍራለሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ዳዊ​ትም ሜል​ኮ​ልን፥ “በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ዘም​ሬ​አ​ለሁ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝብ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአ​ባ​ት​ሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመ​ረ​ጠኝ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​መ​ሰ​ገነ ይሁን፤ ስለ​ዚ​ህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጫ​ወ​ታ​ለሁ፤ እዘ​ም​ራ​ለ​ሁም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ዳዊትም ሜልኮልን፦ በእግዚአብሔር ፊት ዘፍኛለሁ፥ በእግዚአብሔር ሕዝብ በእስራኤል ላይ አለቃ እሆን ዘንድ ከአባትሽና ከቤቱ ሁሉ ይልቅ የመረጠኝ እግዚአብሔር የተባረከ ይሁን ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት እጫወታለሁ።

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 6:21
15 Referencias Cruzadas  

ከአሁን በፊት ሳኦል የእኛ ንጉሥ በነበረ ጊዜ እንኳ በጦርነት እስራኤልን የምትመራ አንተ ነበርክ፤ እንዲሁም ሕዝቡን እስራኤልን እንድትመራና በእስራኤልም ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር ቃል ገብቶልሃል።”


ዳዊት ከበፍታ የተሠራ ሽርጥ በወገቡ ዙሪያ ታጥቆ እግዚአብሔርን በማክበር በሙሉ ኀይሉ ያሸበሽብ ነበር፤


ታቦቱን ይዘው ወደ ከተማ በሚገቡበት ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ተመለከተች፤ ንጉሡ ዳዊት እየዘለለ ሲያሸበሽብ አይታም በልብዋ ናቀችው፤


ከዚህም የባሰ ራሴን አዋርዳለሁ፤ ለአንቺ እንደሚመስልሽ በዐይንሽ ፊት የተናቅሁ ብሆንም በእነርሱ ፊት ራስህን አዋረድክ ብለሽ በተናገርሽባቸው ልጃገረዶች ዘንድ እጅግ የተከበርኩ እሆናለሁ!”


ዳዊትና እስራኤላውያን ሁሉ የበገና፥ የመሰንቆ፥ የከበሮ፥ የጸናጽልና የቃጭል ድምፅ እያሰሙ ለእግዚአብሔር ክብር በመዘመር በሙሉ ኀይላቸው ያሸበሽቡ ነበር።


“ስለዚህም ለአገልጋዬ ለዳዊት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘እኔ አንተን የበግ መንጋ ከምትጠብቅበት መስክ አንሥቼ የሕዝቤ የእስራኤል መሪ አደረግኹህ፤


ታቦቱ ወደ ከተማይቱ በመግባት ላይ ሳለ የሳኦል ልጅ ሜልኮል ንጉሥ ዳዊት በደስታ ሲያሸበሽብና ሲዘል በመስኮት ተመለከተች፤ በልብዋም ናቀችው።


ሳኦልንም ከሻረው በኋላ ዳዊትን አነገሠላቸው፤ እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲመሰክር፦ ‘እንደ ፍላጎቴ የሚሆንልኝን፤ ፈቃዴንም የሚፈጽመውን፥ የእሴይን ልጅ ዳዊትን አገኘሁ’ ብሎአል።


እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ ወይም ማናቸውንም ነገር ስታደርጉ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉ።


አሁን ግን መንግሥትህ ዘላቂ አይሆንም፤ እግዚአብሔር እንደ ልቡ የሚሆንለትን ሰው መርጦአል፤ እግዚአብሔር የሰጠህን ትእዛዝ ስላልጠበቅህ እርሱን በሕዝቡ ላይ መሪ ይሆን ዘንድ ቀብቶታል።”


ሳሙኤልም ሳኦልን እንዲህ አለው፤ “ዛሬ እግዚአብሔር የእስራኤልን መንግሥት ቀዶ ከእጅህ በመውሰድ ለተሻለ ለሌላ ሰው ሰጥቶታል፤


እግዚአብሔር ሳሙኤልን እንዲህ አለው፤ “ከንጉሥነት ስለ ሻርኩት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ድረስ ነው? እኔ እርሱ በእስራኤል ላይ ንጉሥ ሆኖ ይኖር ዘንድ አልፈልገውም። ይልቅስ የወይራ ዘይት በቀንድ ሞልተህ በመያዝ በቤተልሔም ወደሚኖረው እሴይ ተብሎ ወደሚጠራው ሰው ዘንድ ሂድ፤ እኔ ከእርሱ ልጆች መካከል አንዱን ንጉሥ እንዲሆን መርጬአለሁ።”


ስለዚህም እሴይ ልኮ አስጠራው፤ እርሱ ቀይ፥ መልከ መልካምና ዐይኖቹ የሚያበሩ ጤናማ ወጣት ነበር፤ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን “የመረጥኩት ሰው ይህ ነውና ተነሥተህ እርሱን ቀባው!” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos