Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ሳሙኤል 21:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ይሁን እንጂ ዳዊት የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን ወሰደ፤ እንዲሁም የሳኦል ልጅ ሜራብ የመሖላን ተወላጅ ለሆነው ለባርዚላይ ልጅ ለዐድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጨምሮ ወሰደ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ነገር ግን ንጉሡ፣ የኢዮሄል ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን፤ የሳኦል ልጅ ሜሮብ ለመሓላታዊው ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደችለትን ዐምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ነገር ግን ንጉሡ የአያ ልጅ ሪጽፋ ለሳኦል የወለደቻቸውን ሁለቱን ወንዶች ልጆች አርሞኒንና መፊቦሼትን፤ የሳኦል ልጅ ሜራብ ለመሖላታዊው ለባርዚላይ ልጅ ለአድሪኤል የወለደችለትን አምስት ወንዶች ልጆች ጭምር ወሰደ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ንጉ​ሡም ለሳ​ኦል የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የኢ​ዮ​ሄ​ልን ልጅ የሩ​ጻ​ፋን ሁለ​ቱን ልጆች ሄር​ሞ​ን​ስ​ቴ​ንና ሜም​ፌ​ቡ​ስ​ቴን፥ ለመ​ሓ​ላ​ታ​ዊ​ውም ለቤ​ር​ዜሊ ልጅ ለኤ​ስ​ድራ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸ​ውን የሳ​ኦ​ልን ልጅ የሜ​ሮ​ብን አም​ስ​ቱን ልጆች ወሰደ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ንጉሡም ለሳኦል የወለደቻቸውን የኢዮሄል ልጅ የሪጽፋን ሁለቱን ልጆች ሄርሞንንና ሜምፊቦስቴን ለመሓላታዊውም ለቤርዜሊ ልጅ ለኤስድሪኤል የወለደቻቸውን የሳኦልን ልጅ የሜሮብን አምስቱን ልጆች ወሰደ፥

Ver Capítulo Copiar




2 ሳሙኤል 21:8
4 Referencias Cruzadas  

ሳኦል የአያ ልጅ የሆነች ሪጽፋ የምትባል ቁባት ነበረችው፤ ኢያቡስቴ አበኔርን “ለምን ከአባቴ ቁባት ጋር ተገናኘህ” አለው።


የኒምሺን ልጅ ኢዩንም ቀብተህ በእስራኤል ላይ አንግሠው፤ የአቤል መሖላ ተወላጅ የሆነውን የዮሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕንም ቀብተህ በአንተ እግር ነቢይ እንዲሆን አድርገው።


የሳኦልም ወንዶች ልጆች ዮናታን፥ ይሽዊና ማልኪሹዓ ተብለው ይጠሩ ነበር፤ ታላቋ ሴት ልጁም ሜራብ ስትሆን፥ ታናሽዋ ሜልኮል ትባል ነበር፤


ነገር ግን ሜራብ ለዳዊት የምትዳርበት ጊዜ ሲደርስ ከመሖላ ለመጣውና ዓድሪኤል ተብሎ ለሚጠራ ለአንድ ሌላ ሰው ተዳረች።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos