2 ሳሙኤል 2:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም አበኔር ኢያቡስቴን በገለዓድ ግዛቶች፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም ይኸውም በመላው እስራኤል ላይ እንዲነግሥ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱንም በገለዓድ፣ በአሴር፣ በኢይዝራኤል፣ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ ላይ አነገሠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንም በገለዓድ ላይ፥ በአሴር፥ በኢይዝራኤል፥ በኤፍሬምና በብንያም እንዲሁም በእስራኤል ሁሉ አነገሠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በገለዓድና በታሲሪ፥ በኢይዝራኤልም፥ በኤፍሬምም፥ በብንያምም፥ በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በገለዓድና በአሹራውያን በኢይዝራኤልም በኤፍሬምም በብንያምም በእስራኤልም ሁሉ ላይ አነገሠው። |
የአሴር ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸው በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤
ይኸው ድንበር በምዕራብ በኩል ከታፑሐ ተነሥቶ እስከ ቃና ወንዝ ይደርስና መጨረሻው የሜድትራኒያን ባሕር ይሆናል፤ ለኤፍሬም ነገድ በየወገኑ ርስት ሆኖ የተሰጠው ምድር ይህ ነበር።
ይህ የዮሴፍ በኲር ልጅ የነበረው የምናሴ ነገድ ድርሻ የሚከተለው ነው። የምናሴ በኲር ልጅ የገለዓድ አባት ማኪር የጦር ጀግና ስለ ነበረ ገለዓድና ባሳን በርስትነት ተሰጠው።
የሮቤል፥ የጋድና የምናሴ ነገድ እኩሌታ በከነዓን ምድር በሚገኘው በሴሎ ካሉት ከእስራኤላውያን ዘንድ ተነሥተው በሙሴ አማካይነት በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ተሰጣቸው ምድር ወደ ገለዓድ ተመለሱ።
እስራኤላውያን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ሳሉ፥ ፍልስጥኤማውያን ወታደሮቻቸውን በአንድነት ሰብስበው በማምጣት በአፌቅ አሰለፉ፤