አባቶቼ በተቀበሩበት መቃብር መቀበር ስለምፈልግ በምሞትበት ጊዜ ከግብጽ አገር ወስደህ፥ እነርሱ በተቀበሩበት ስፍራ ቅበረኝ።” ዮሴፍም “እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው።
2 ሳሙኤል 19:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ እኔ አገልጋይህ ወደ ቤቴ ተመልሼ እንድሄድና በወላጆቼ መቃብር አጠገብ እንዳርፍ ፍቀድልኝ፤ እነሆ፥ ይህ ልጄ ኪምሀም ያገለግልሃል፤ ንጉሥ ሆይ! እርሱን ይዘኸው ሂድ፤ የወደድከውንም ለእርሱ አድርግለት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገዛ ከተማዬ ሞቼ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እቀበር ዘንድ፣ አገልጋይህን አሰናብተውና ይመለስ፤ ነገር ግን አገልጋይህ ከመዓም እነሆ፤ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋራ ይሻገር፤ ደስ ያለህንም ነገር አድርግለት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋይህ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ከንጉሡ ጋር ጥቂት መንገድ ይሄዳል፤ ነገር ግን ንጉሡ በዚህ ሁኔታ ወሮታ የሚመልስልኝ ለምንድን ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ባሪያህ ተመልሼ በከተማዬ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ እባክህ! ልሙት፤ ነገር ግን ባሪያህ ከመዓም ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይሻገር፤ በዐይኖችህ ፊት ደስ የሚያሰኝህንም ለእርሱ አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ባሪያህ ተመልሼ በከተማዬ በአባቴና በእናቴ መቃብር አጠገብ፥ እባክህ፥ ልሙት። ነገር ግን ባሪያህን ከመዓምን እይ፥ እርሱ ከጌታዬ ከንጉሡ ጋር ይለፍ፥ ደስ የሚያሰኝህንም ለእርሱ አድርግ። |
አባቶቼ በተቀበሩበት መቃብር መቀበር ስለምፈልግ በምሞትበት ጊዜ ከግብጽ አገር ወስደህ፥ እነርሱ በተቀበሩበት ስፍራ ቅበረኝ።” ዮሴፍም “እሺ እንዳልከኝ አደርጋለሁ” አለው።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
አስከሬኑን ወደ ከነዓን ወስደው ከመምሬ በስተምሥራቅ በምትገኘው በማክፌላ ዋሻ ቀበሩት፤ ይህም ዋሻ አብርሃም ለመቃብር ቦታ እንዲሆን ከሒታዊው ከዔፍሮን በገዛው እርሻ ውስጥ የሚገኝ ነው።
ደግሞም ንጉሡ ይህን ያኽል ታላቅ ወሮታ የሚከፍለኝ ለምንድን ነው? ነገር ግን የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻግሬ ከአንተ ጋር ጥቂት መንገድ ብቻ እሄዳለሁ።
ንጉሡም “እርሱን ይዤ እሄዳለሁ፤ እንዳደርግለት የምትፈልገውንም ሁሉ አደርግለታለሁ፤ ለአንተም ቢሆን የምትጠይቀውን ሁሉ እፈጽማለሁ” አለው።
ይህን በማድረግ ፈንታ እኔ በዚያ ምንም ዐይነት እህል ውሃ እንዳትቀምስ ወዳዘዝኩህ ቦታ ተመልሰህ በላህ፤ ይህንንም በማድረግህ ምክንያት ትገደላለህ፤ ሬሳህም በቤተሰብህ መቃብር አይቀበርም።’ ”
“ከወንድምህ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸሁ ጊዜ የቸርነት ሥራ ስላደረጉልኝ ለገለዓዳዊው ለባርዚላይ ልጆች ግን መልካም ነገር በማድረግ ተንከባከባቸው፤ በማዕድህም ከሚመገቡት መካከል ይሁኑ።
እነርሱም የባቢሎን ንጉሥ ገዢ አድርጎ የሾመውን ገዳልያንን እስማኤል ስለ ገደለው ባቢሎናውያን አደጋ ያደርሱብናል ብለው ፈርተው ነበር፤ ስለዚህም ከባቢሎናውያን ፊት ሸሽተው ወደ ግብጽ ለመኰብለል ተነሡ፤ በቤተልሔም አጠገብ ባለችው ጌሩት ኪምሀም ተብላ በምትጠራው ቦታ ዕረፍት አደረጉ።
“እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ደርሶአል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር በሰጣችሁ ተስፋ መሠረት ያደረገላችሁን መልካም ነገር ሁሉ ከእናንተ እያንዳንዱ በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ ያውቃል፤ እርሱ ከሰጣችሁ ተስፋ አንድም ሳይቀር ሁሉም ተፈጽሞአል።