Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ነገሥት 4:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃ ገዦች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡ የቅርብ አማካሪ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዓዛርያስ የተባለው የናታን ልጅ፦ የክፍላተ ሀገር ገዢዎች የበላይ ኀላፊ፤ የናታን ልጅ ካህኑ ዛቡድ፦ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የና​ታ​ንም ልጅ ኦርኒያ የሹ​ሞች አለቃ ነበረ፤ የና​ታ​ንም ልጅ ዘባት የን​ጉሡ አማ​ካ​ሪና ወዳጅ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 የናታንም ልጅ ዓዛርያስ የሹሞች አለቃ ነበረ፤ የናታንም ልጅ ዛቡድ የንጉሡ አማካሪና ወዳጅ ነበረ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ነገሥት 4:5
17 Referencias Cruzadas  

“ይዲድያ” የሚል ስም እንዲያወጣለት ነቢዩ ናታንን አዘዘው፤ ይህም “በእግዚአብሔር የተወደደ” ማለት ነው።


ስለዚህም የዳዊት ወዳጅ ሑሻይ ወደ ከተማይቱ ተመለሰ፤ አቤሴሎምም ወዲያውኑ እዚያ ደረሰ።


የዳዊት ታማኝ ወዳጅ ሑሻይ አቤሴሎምን ባገኘው ጊዜ “ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ረጅም ዕድሜ ለንጉሡ! ይሁን!” እያለ ጮኸ።


እንዲሁም የያዒር ከተማ ተወላጅ የሆነው ዒራ ከዳዊት ካህናት አንዱ ነበር።


በኢየሩሳሌምም የተወለዱት ልጆች፥ ሻሙዓ፥ ሾባብ፥ ናታን፥ ሰሎሞን፥


ከዚህም በኋላ ንጉሡ ነቢዩ ናታንን “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል!” አለው።


የዮዳሄ ልጅ በናያ የዳዊት ክብር ዘብ አዛዥ ነበር፤ የዳዊትም ልጆች አማካሪዎቹ ነበሩ።


አሒሻር የተባለው፦ የቤተ መንግሥት አገልጋዮች ኀላፊ፤ አዶኒራም የተባለው የዓብዳ ልጅ፦ የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ ነበሩ።


ሰሎሞን በመላው እስራኤል ዐሥራ ሁለት የክፍላተ ሀገር ገዢዎችን ሾመ፤ የእነርሱም ተግባር ከየግዛታቸው ለንጉሡና ለንጉሡ ቤተሰብ ቀለብ የሚሆነውን ነገር ሁሉ ማቅረብ ነበር፤ እያንዳንዳቸውም በዓመት ውስጥ ለአንድ ወር ቀለብ የማቅረብ ግዴታ ነበረባቸው።


አኪጦፌል የንጉሡ አማካሪ ሲሆን፥ አርካዊው ሑሻይ የንጉሡ ወዳጅ ነበር፤


የልብ ንጽሕናንና መልካም ንግግርን የሚወድ ሰው በንጉሥ ዘንድ የተወደደ ይሆናል።


ኢየሱስ ይወደው የነበረው፥ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ በኢየሱስ ጐን ተቀምጦ ነበር።


በቅዱስ መጽሐፍ “አብርሃም እግዚአብሔርን አመነ፤ እምነቱም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት” የተባለው ቃል ተፈጸመ፤ በዚህ ሁኔታ አብርሃም የእግዚአብሔር ወዳጅ ተባለ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos