በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤
2 ሳሙኤል 15:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊት የማምለኪያ ስፍራ ወዳለበት ወደ ኮረብታው ጫፍ በደረሰ ጊዜ ታማኝ ጓደኛው የሆነው አርካዊው ሑሻይ ልብሱን ቀዶና በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊትም ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክበት ወደ ተራራው ጫፍ ሲደርስ፣ አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት ሕዝቡ እግዚአብሔርን ወደሚያመልክበት ወደ ተራራው ጫፍ በደረሰ ጊዜ፥ አርካዊው ሑሻይ ልብሱን ቀዶ ትቢያ በራሱ ላይ ነስንሶ ሊያገኘው መጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ መጣ፤ ወዳጁ ኵሲም ልብሱን ቀደደ፤ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም ለእግዚአብሔር ወደ ሰገደበት ወደ ተራራው ራስ በመጣ ጊዜ፥ አርካዊው ኩሲ ልብሱን ቀድዶ በራሱም ላይ ትቢያ ነስንሶ ሊገናኘው መጣ። |
በሦስተኛው ቀን አንድ ወጣት ከሳኦል ሰፈር መጣ፤ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤ ወደ ዳዊትም ቀርቦ በአክብሮት ወደ መሬት ለጥ ብሎ እጅ ነሣ፤
ዳዊትም ሐዘኑን በመግለጥ ጫማ ሳያደርግ ራሱን ተከናንቦ የደብረ ዘይትን አቀበት እያለቀሰ ወጣ፤ የተከተሉትም ሁሉ ደግሞ ራሳቸውን ተከናንበው ያለቅሱ ነበር።
ዳዊት ከኮረብታው ጫፍ ባሻገር ገና ጥቂት እንደ ሄደ ጺባ ተብሎ የሚጠራው የመፊቦሼት አገልጋይ በድንገት አገኘው፤ እርሱም ሁለት መቶ ሙልሙል ዳቦ፥ አንድ መቶ የዘቢብ ጥፍጥፍ፥ አንድ መቶ እስር ፍራፍሬና በወይን ጠጅ የተሞላ አንድ አቁማዳ የተጫኑ ሁለት አህዮች ይነዳ ነበር፤
ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ከሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።
ነገዱ ከብንያም ወገን የሆነ አንድ ሰው ከጦር ሜዳ ተነሥቶ በመገሥገሥ በዚያኑ ዕለት ሴሎ ደረሰ፤ ሐዘኑንም ለማሳወቅ ልብሱን ቀዶ በራሱ ላይ ትቢያ ነስንሶ ነበር፤