ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
2 ሳሙኤል 15:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ አገር የኖርከውም ለአጭር ጊዜ ነው፤ ታዲያ አንተ ከእኔ ጋር የምትንከራተተው ስለምንድን ነው? እኔ የት እንደምሄድ እንኳ አላውቅም፤ ስለዚህ የአገርህን ሰዎች ይዘህ ተመለስ፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነተኛነቱን ይግለጥልህ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋራ እንድትንከራተት ላድርግ? በል አሁንም ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ በጎነትና ታማኝነትም ከአንተ ጋራ ይሁን” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የመጣኸውም ገና ትናንት ነው፤ ታዲያ የት እንደምሄድ የማላውቅ ሰው እንዴት ዛሬ ከእኛ ጋር እንድትንከራተት ላድርግ? ተነሥ ሰዎችህን ይዘህ ተመለስ፤ ታማኝነትና እውነተኛነትም ከአንተ ጋር ይሁን” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የመጣኸው ትናንት ነው፤ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፤ አንተ ግን ተመለስ፤ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር መልሳቸው፤ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የመጣኸው ትናንት ነው፥ ዛሬ ከእኛ ጋር ላዙርህን? እኔ ወደምሄድበት እሄዳለሁ፥ አንተ ግን ተመለስ፥ ወንድሞችህንም ከአንተ ጋር ውሰድ፥ እግዚአብሔርም ምሕረቱንና እውነቱን ያድርግልህ አለው። |
ዳዊት ወደ ያቤሽ ገለዓድ ሰዎች መልእክተኞችን ልኮ እንዲህ አላቸው፦ “እርሱን በመቅበር ለጌታችሁ ለሳኦል ቸርነትን ስላሳያችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ።
ስለዚህም ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ተከታዮቹ በሙሉ ወዲያውኑ ቀዒላን ለቀው ለመሄድ ተንቀሳቀሱ፤ ሳኦልም ዳዊት ከቀዒላ አምልጦ መሄዱን በሰማ ጊዜ የነበረውን ዕቅድ ተወ።