የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።
2 ነገሥት 9:30 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጒርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቊልቊል መንገዱን ትመለከት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይኗን ተኳኵላ፣ ጠጕሯንም አሰማምራ በመስኮት ትመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ጊዜ ኢዩ ወደ ኢይዝራኤል ደረሰ፤ ኤልዛቤልም ይህን የሆነውን ነገር ሰምታ ዐይንዋን ተኳለች፤ ጠጉርዋንም ተሠርታ በቤተ መንግሥቱ ሰገነት ላይ በመስኮት አዘንብላ ቁልቁል መንገዱን ትመለከት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል ሄደ፤ ኤልዛቤልም ይህን በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዩም ወደ ኢይዝራኤል መጣ፤ ኤልዛቤልም በሰማች ጊዜ ዐይንዋን ተኳለች፤ ራስዋንም አስጌጠች፤ በመስኮትም ዘልቃ ትመለከት ነበር። |
የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።
ለጥፋት የተዳረግሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ቀይ ልብስ የለበስሽበት ምክንያት ምንድን ነው? ጌጣጌጥ ማድረግሽና ዐይንሽንስ መኳልሽ ለምንድነው? ውሽሞችሽ ጠልተውሽ ሊገድሉሽ ስለሚፈልጉ ውበትሽን የምትንከባከቢው በከንቱ ነው።
“ወንዶችን ከሩቅ አገር ጋብዘው እንዲያመጡላቸው ደጋግመው መልእክተኞችን ላኩ፤ የፈለጓቸውም ወንዶች መጡላቸው፤ ሁለቱ እኅትማማቾች ገላቸውን ታጠቡ፤ ዐይናቸውን ተኳሉ፤ ጌጣጌጦቻቸውንም አደረጉ፤
በሐዘንም መንሰቅሰቅህን ሰው አይስማህ፤ ለሟችዋ አታልቅስ፤ መጠምጠሚያህንም በራስህ ላይ አድርግ፤ ጫማህንም በእግርህ አጥልቅ፤ አፍህን አትሸፍን፤ የእዝን እንጀራ አትብላ።”
እስራኤላውያን በኢይዝራኤል ሸለቆ ውስጥ በሚገኘው ምንጭ አጠገብ ሰፍረው ሳሉ፥ ፍልስጥኤማውያን ወታደሮቻቸውን በአንድነት ሰብስበው በማምጣት በአፌቅ አሰለፉ፤