ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
2 ቆሮንቶስ 6:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በንጽሕና፥ በዕውቀት፥ በትዕግሥት፥ በደግነት፥ በመንፈስ ቅዱስ በመመራትና ግብዝነት በሌለበት ፍቅር፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በንጽሕና፣ በዕውቀት፣ በትዕግሥት፣ በቸርነት፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ በእውነተኛ ፍቅር፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በንጽሕና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ በእውነተኛ ፍቅር፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በንጽሕናና በዕውቀት፥ በምክርና በመታገሥ፥ በቸርነትና በመንፈስ ቅዱስ፥ አድልዎ በሌለበት ፍቅር፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ |
ስለዚህም ሌሎች ሕዝቦች እንደሚያደርጉት ሕዝቤ አንተ ምን እንደምትናገር ለማዳመጥ ብቻ ይሰበሰባሉ፤ ነገር ግን የምትነግራቸውን ሁሉ አይፈጽሙም፤ የምትናገረውን ቃል የሚወዱት መስለው ይታያሉ፤ ነገር ግን ከበዝባዥነታቸው አይመለሱም፤
እንዲሁም በታላላቅ ተአምራትና በድንቅ ሥራዎች፥ በመንፈስ ቅዱስም ኀይል ከኢየሩሳሌምና ከአካባቢዋ ጀምሮ እስከ እልዋሪቆን ድረስ የክርስቶስን ወንጌል አስተምሬአለሁ።
ይህም፦ “የጌታን ሐሳብ ማን ሊያውቀው ይችላል? ሊመክረውስ የሚችል ማን ነው?” ተብሎ እንደ ተጻፈው ነው። እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን።
አንድ ሰው ወደ እናንተ መጥቶ እኛ የሰበክነውን ሳይሆን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክላችሁ ወይም እናንተ የተቀበላችሁትን መንፈስ ሳይሆን ሌላ መንፈስ ብትቀበሉ፥ ወይም የተቀበላችሁትን ወንጌል ሳይሆን ሌላ ወንጌል ብትቀበሉ፥ ዝም ብላችሁ ተሸነፋችሁ ማለት ነው።
ስለ እናንተ እንኳን ገንዘቤን ራሴንም አሳልፌ ብሰጥ እጅግ በጣም ደስ ይለኛል፤ ታዲያ፥ እኔ ይህን ያኽል አብዝቼ ስወዳችሁ እናንተ የምትወዱኝ እንዲህ በጥቂቱ ነውን?
ይህን መልእክት ከእናንተ ርቄ ሳለሁ የጻፍኩላችሁ በዚሁ ምክንያት ነው፤ በዚህ ዐይነት ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ ጌታም በሰጠኝ ሥልጣን አላስጨንቃችሁም፤ ጌታ ሥልጣን የሰጠኝ እናንተን ለማነጽ እንጂ እናንተን ለማፍረስ አይደለም።
እናንተ ይቅርታ ለምታደርጉለት ሰው እኔም ይቅርታ አደርግለታለሁ፤ ይቅር የምልለት በደል ካለ እኔ በክርስቶስ ፊት ይቅርታ የማደርግለት ስለ እናንተ ብዬ ነው።
በትልቅ ሐዘንና በልብ ጭንቀት፥ በብዙ እንባም ሆኜ የጻፍኩላችሁ በጣም የምወዳችሁ መሆኔን እንድታውቁ ብዬ ነው እንጂ ላሳዝናችሁ ብዬ አይደለም።
እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም።
“ብርሃን በጨለማ ውስጥ ይብራ!” ብሎ የተናገረ እግዚአብሔር በክርስቶስ መልክ የሚያበራውን የእግዚአብሔርን ክብር የማወቅ ብርሃን እንዲሰጠን ብርሃኑን በልባችን ውስጥ እንዲበራ አደረገ።
ማወቅ የምፈልገው ይህን ብቻ ነው፤ ለመሆኑ እናንተ መንፈስ ቅዱስን የተቀበላችሁት ሕግን በመፈጸም ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመን ነው?
እግዚአብሔር መንፈሱን የሚሰጣችሁና በእናንተ ዘንድ ተአምራትን የሚያደርገው ሕግን በመፈጸማችሁ ነውን? ወይስ የምሥራቹን ቃል ሰምታችሁ በማመናችሁ ነው?
ይልቅስ እርስ በርሳችሁ ደጎችና አዛኞች ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተም እርስ በርሳችሁ ይቅር ተባባሉ።
እግዚአብሔርም ለቅዱሳኑ ሊገልጥላቸው የፈቀደው ያለውን የዚህን ምሥጢር የክብር ብልጽግና በእናንተ በአሕዛብ መካከል ምን ያኽል ታላቅ መሆኑን ነው። ይህም ምሥጢር በተስፋ የምንጠባበቀው ክብር የሚገኝበት ክርስቶስ በእናንተ መካከል መሆኑ ነው።
እንግዲህ የእግዚአብሔር ምርጦችና ቅዱሳን፥ የተወደዳችሁም እንደ መሆናችሁ መጠን ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትሕትናን፥ ገርነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ።
በእናንተ በአማኞች መካከል በነበርንበት ጊዜ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ሕይወት እንደ ኖርን እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክር ነው፤
ነገር ግን ከእግዚአብሔር የሚገኘው ጥበብ በመጀመሪያ ንጹሕ ነው፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ ታዛዥ፥ ምሕረት አድራጊ፥ ጥሩ ፍሬ የሞላበት፥ አድልዎና ግብዝነት የሌለበት ነው።
እነዚህ ነቢያት ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤ ያገለገሉአችሁም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አሁን ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ ይህን ነገር መላእክት እንኳ ለማየት ይመኙት ነበር።
ለምእመናን ቅንነት የተሞላበት ፍቅር እንዲኖራችሁ ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችኋል፤ ስለዚህ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።
ስለዚህ እርስዋ “ልብህ ከእኔ ጋር ሳይሆን እንዴት እወድሻለሁ ትለኛለህ? ሦስት ጊዜ አታለልከኝ፤ እስከ አሁንም ይህን ሁሉ ብርታት ያገኘኸው ከምን እንደ ሆነ አልነገርከኝም” አለችው።