2 ቆሮንቶስ 10:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ለመመስገን የሚበቃው ጌታ ሲያመሰግነው ነው እንጂ ራሱን በራሱ ሲያመሰግን አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም ጌታ ራሱ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን በራሱ የሚያመሰግን ተቀባይነት አይኖረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ፥ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ያከበረው ብቻ ይከብራል እንጂ ራሱን የሚያከብር የተመረጠ አይደለም። |
እርሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ ራሳችሁን በሰው ፊት ጻድቅ ታስመስላላችሁ፤ እግዚአብሔር ግን ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ፊት ክብር ያለው መስሎ የሚታይ፥ በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ነው።”
“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል አዳምጡ፤ እናንተ ራሳችሁ እንደምታውቁት የናዝሬቱ የኢየሱስ ማንነት እግዚአብሔር በእናንተ መካከል በእርሱ አማካይነት በፈጸማቸው ታላላቅ ሥራዎች፥ ተአምራትና ምልክቶች ተረጋግጦአል።
እውነተኛ አይሁዳዊ በውስጥ አይሁዳዊ የሆነ ነው፤ እውነተኛ መገረዝ በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሆን የልብ መገረዝ ነው እንጂ በሕግ በተጻፈው መሠረት የሥጋ መገረዝ አይደለም። እንዲህ ዐይነቱም ሰው ምስጋናን የሚቀበለው ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።
ስለዚህ ጊዜው ሳይደርስ፥ ጌታ ለፍርድ ከመምጣቱ በፊት በማንም ላይ አትፍረዱ፤ እርሱ በሚመጣበት ጊዜ በጨለማ የተሰወረውን ምሥጢር ወደ ብርሃን ያወጣዋል፤ በሰዎች ልብ የተደበቀውን ሐሳብ ይገልጠዋል፤ በዚያን ጊዜ እያንዳንዱ ከእግዚአብሔር ተገቢውን ምስጋና ያገኛል።
ይሁን እንጂ ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንድ ሰዎች ጋር ራሳችንን ልናወዳድር ወይም ራሳችንን ልናነጻጽር አንደፍርም፤ እነርሱ ግን ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር በማመዛዘናቸውና ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር በማወዳደራቸው አስተዋዮች አይደሉም።
ክፉ ነገር እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ የምንጸልየውም ምንም እንኳ እኛ ብቁዎች ሆነን ሳንታይ ብንቀር እናንተ ዘወትር መልካም የሆነውን ነገር እንድታደርጉ ነው እንጂ የእኛን ብቃት ለማሳየት አይደለም።
እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የድጋፍ ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆን?
በልብ ባለው ሳይሆን በሚታየው ለሚመኩ መልስ ለመስጠት እንድትችሉ በእኛ ትመኩ ዘንድ ዕድል እንሰጣችኋለን እንጂ እንደገና እኛ ለእናንተ ራሳችንን አናመሰግንም።
የእውነትን ቃል በትክክል እንደሚያደርስና በሥራውም እንደማያፍር ሠራተኛ ሆነህ ራስህን በእግዚአብሔር ፊት ለማቅረብና ተቀባይነትን ለማግኘት ጥረት አድርግ።
ይህ ፈተና የሚደርስባችሁ የእምነታችሁን እውነተኛነት ለማረጋገጥ ነው፤ የሚጠፋ ወርቅ እንኳ በእሳት ይፈተናል፤ ከወርቅ ይልቅ የከበረ እምነታችሁ እንደዚሁ መፈተን አለበት፤ ይህም የተፈተነ እምነታችሁ ኢየሱስ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ ምስጋናን፥ ክብርንና ውዳሴን ያስገኝላችኋል።