Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ቆሮንቶስ 10:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ፥ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ምክንያቱም ጌታ ራሱ የሚያመሰግነው እንጂ፣ ራሱን በራሱ የሚያመሰግን ተቀባይነት አይኖረውም።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሰው ለመመስገን የሚበቃው ጌታ ሲያመሰግነው ነው እንጂ ራሱን በራሱ ሲያመሰግን አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያከ​በ​ረው ብቻ ይከ​ብ​ራል እንጂ ራሱን የሚ​ያ​ከ​ብር የተ​መ​ረጠ አይ​ደ​ለም።

Ver Capítulo Copiar




2 ቆሮንቶስ 10:18
21 Referencias Cruzadas  

ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፥ ልቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።


የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት የቀናች ትመስለዋለች፥ ጌታ ግን ልብን ይመዝናል።


ሌላ ያመስግንህ እንጂ ከአንተ አፍ አይውጣ፥ ባዕድ ሰው እንጂ ከንፈርህ አይሁን።


እንዲህም አላቸው “ራሳችሁን በሰው ፊት የምታጸድቁ እናንተ ናችሁ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ልባችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ፊት ርኩሰት ነውና።


ከእግዚአብሔር ክብር ይልቅ የሰውን ክብር ወደዋልና።


“የእስራኤል ሰዎች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁት፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ በእርሱ በኩል ባደረገው ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ፤


እንደዚህ አድርጎ ክርስቶስን የሚያገልግል እግዚአብሔርን ደስ ያሰኛል፤ በሰውም ዘንድ የተመሰገነ ነው።


በክርስቶስ መሆኑ ተፈትኖ ለተመሰገነው ለአፕሊን ሰላምታ አቅርቡልኝ። የአሪስቶቡሉ ቤተሰብ ለሆኑት ሰላምታ አቅርቡልኝ።


ነገር ግን በስውር አይሁዳዊ የሆነ አይሁዳዊ ነው፤ መገረዝም በመንፈስ የሆነ የልብ መገረዝ ነው እንጂ በፊደል አይደለም፤ ምስጋናውም ከእግዚአብሔር ነው እንጂ ከሰው አይደለም።


ትክክል የሆኑት እነማን እንደ ሆኑ ተለይተው እንዲታወቁ በመካከላችሁ መለያየት መኖሩ ግድ ነውና።


ስለዚህም፥ በጨለማ የተሰወረውን ወደ ብርሃን የሚያወጣ ደግሞም የልብን ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ፥ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤ በዚያን ጊዜም እያንዳንዱ ምስጋናው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል።


ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን መቁጠር ወይም ራሳችንን ማስተያየት አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ እርስ በራሳቸው ሲያመዛዝኑ፥ እርስ በራሳቸውም ሲተያዩ፥ አስተዋይ አይደሉም።


ክፉ ነገርንም ከቶ እንዳታደርጉ ወደ እግዚአብሔር እንጸልያለን፤ እኛ የበቃን ሆነን እንድንታይ አይደለም፤ ነገር ግን እኛ ምንም የማንበቃ እንኳን ብንሆን፥ እናንተ መልካሙን እንድታደርጉ ነው።


እንደገና ራሳችንን ልናመሰግን እንጀምራለንን? ወይስ አንዳንዶች እንደሚያደርጉት ለእናንተ ወይም ከእናንተ የተጻፈ የምስጋና ደብዳቤ ያስፈልገን ይሆንን?


በልብ ሳይሆን በውጫዊ ነገር ለሚመኩ፥ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት ልንሰጣችሁ እንጂ በእናንተ ፊት መልሰን ራሳችንን ለማመስገን ፈልገን አይደለም።


ነገር ግን እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች በሁሉም መንገድ ራሳችንን እንሰጣለን፤ በታላቅ ጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥


የእውነትን ቃል በትክክለኛው መንገድ እየገለጥህ፥ የሚያፍርበት ነገር እንደሌለው ሠራተኛ፥ ለእግዚአብሔር ብቁ ተደርገህ ራስህን ለማቅረብ የተቻለህን ሁሉ ጣር።


በዚህም በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos