ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ የጠላት ሠረገሎችና ፈረሰኞች ወደ እነርሱ ሲጠጉ አየሁ፤
1 ሳሙኤል 31:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን ግን ተከታትለው ስለ ደረሱባቸው ሦስቱን የሳኦልን ልጆች ዮናታንን፥ አቢናዳብንና ማልኪሹዓን ገደሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ሳኦልንና ልጆቹን አጥብቀው አሳደዷቸው፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፣ አሚናዳብንና ሜልኪሳን ገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን አጥብቀው ተከታተሉ፤ የሳኦልንም ልጆች ዮናታንን፥ አቢናዳብንና ማልኪሹዓን ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን ተከትለው አገኙአቸው። ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን፥ ሜልኪሳንም ገደሉአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ሳኦልንና ልጆቹን በእግር በእግራቸው ተከትለው አባረሩአቸው፥ ፍልስጥኤማውያንም የሳኦልን ልጆች ዮናታንንና አሚናዳብን ሜልኪሳንም ገደሉ። |
ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “እኔ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ነበርኩ፤ ሳኦል ጦሩን ተደግፎ ሳለ የጠላት ሠረገሎችና ፈረሰኞች ወደ እነርሱ ሲጠጉ አየሁ፤
ይኸውም ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ በፊቱ ታረዱ፤ ከዚህም በኋላ ናቡከደነፆር የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ አሳወረው፤ እጆቹንም በሰንሰለት አስሮ ወደ ባቢሎን ወሰደው።
ኔር ቂስን ወለደ፤ ቂስ ንጉሥ ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታን፥ ማልኪሹዓ፥ አቢናዳብና ኤሽባዓል ተብለው የሚጠሩትን አራት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤
እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እጅግ ቀናተኛ ስለ ሆንኩ ተቀርጾ የተሠራውን ማንኛውም ጣዖት አታምልክ፤ አትስገድለትም፤ እኔ የሚጠሉኝን ሁሉ እቀጣለሁ፤ ዘራቸውንም ሁሉ እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ እበቀላለሁ።
ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ መሸጉ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮችም ምሽግ በሚክማስ ነበር፤
ከእስራኤል ሕዝብ መካከል የተውጣጡ ሦስት ሺህ ሰዎችን መረጠ፤ ከእነርሱ መካከል ሁለቱን ሺህ በሚክማስና በቤትኤል በሚገኘው ኮረብታማ አገር ከእርሱ ጋር እንዲሆኑ መደበ፤ አንዱን ሺህ ሰዎች ደግሞ ከልጁ ከዮናታን ጋር በማሰለፍ በብንያም ነገድ ግዛት ውስጥ ጊብዓ ተብሎ ወደሚጠራው ኮረብታማ አገር ላከ፤ ከዚህ የተረፉትን ሌሎች ሰዎች ግን ወደየቤታቸው አሰናበተ።
በኤፍሬም ኮረብታዎች ተደብቀው የነበሩ ሌሎች እስራኤላውያንም ፍልስጥኤማውያን በሽሽት ላይ መሆናቸውን ሰሙ፤ ስለዚህም ከወገን ጦር ጋር ተባብረው ፍልስጥኤማውያንን ማሳደድ ጀመሩ፤
“አይዞህ አትፍራ፤ አባቴ ሳኦል በአንተ ላይ ጒዳት ማድረስ ከቶ አይችልም፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ እንደምትሆንና እኔም ከአንተ የምቀጥል ሁለተኛ ማዕርግ እንደሚኖረኝ አባቴ በደንብ ያውቃል።”
ስለዚህ እርሱ አንተንና እስራኤልን ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣችኋል፤ ነገ አንተና ልጆችህ እኔ ወዳለሁበት ቦታ ትመጣላችሁ፤ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ሠራዊት ለፍልስጥኤማውያን አሳልፎ ይሰጣል።”